Vic ANRS 2

Vic ANRS 2


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ፣ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት እና UIIDP 2012 በጀት ዓመት

የመኪና ጎማዎችን

ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አውጥቶ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
የግዥው መጠን ብር 200000,00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የመኪና ጎማዎችን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

በዚህ የጨረታማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች
በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 28 ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋ ገጠ ቼክ፤ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገንዘብ ያዥ ጋር በመምጣት ማስያዝ እና ደረሰኙን ኦርጅናል ማስገባት አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ /ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጊቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከተማ ልማት ቤቶችና የኮንስትራክሽን ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16 ኛ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረ ስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582266180/0583205000 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡



በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 23 ቀን 2012

Deadline: June 15, 2020


© walia tender


Report Page