Vi sale merhabete1

Vi sale merhabete1

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የገ/ኢ/ትብብር መምሪያ የመርሀቤቴ ወረዳ/ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት

የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማና ከነመዳሪ እንዲሁም በተራድኦ በጀት
የጽሕፈት መሣሪያዎች በግልጽ ጨረታ አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
የሞሉት ዋጋ ከ200,000 ሺ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
የጨረታ ሰነዱን በብር 50 ( ሃምሳ ብር ብቻ) ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15 ኛው ቀን 11 ፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት የካላንደር ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 05 መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍ ያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤታችን የውስጥ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በመ/ወ/ገ/ኢ/ትብብር ዋና ጽ/ቤት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው የሚከፈተው በ16 ኛው ቀን በ3 ፡00 ሰዓት ታሽጐ በ3 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡-011-13-20-136/005 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም ሕዝባዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

በሰሜን ሸዋ ዞን ያገ/ ኢ/ ትብብር መምሪያ ያመርሀቤቴ ወረዳ/ ገ/ ኢ/ትብብር ጽ/ ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 27ቀን 2012

Deadline: June 19, 2020


© walia tender

Report Page