VOA

VOA


#SNNPRS #GurageZone


" ሰዎች ለምን የክልልነት ጥያቄ ትደግፋላችሁ በሚል እየታሰሩ ናቸው " - ነዋሪዎች


" ህዝቦችን ለማጋጫት ስራ የሚሰሩ አካላት አሉ በዚህ ምክንያት የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጭምር በቁጥጥር ስር ውለዋል " - የደቡብ ክልል ፖሊስ


በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።


እየታሰሩ ከሚገኙት መካከል በዞን ደረጃ በኃላፊነት ቦታ ያሉ ጭምር መሆናቸው ተጠቁሟል።


ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ አቶ በላቸው ገብረማርያን የተባሉ በግብርና ስራ የሚተዳደሩ የዞኑ ነዋሪ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ 13 ሰዎች እንደታሰሩ ከነዚህ ውስጥ ልጃቸውም እንደሙገኝበት ገልፀዋል። እሳቸውንም ፖሊስ እያፈላለገ መሆኑን አመልክተዋል።


እስሩ እየተካሄደ ያለው ለምን " የክልልነት ጥያቄ ትደግፋላችሁ " በሚል እንደሆነ አንዳችም ወንጀል እንዳልተፈፀመ ተናግረዋል።


የደቡብ ክልል ፖሊስ ምን ይላል ?


የደቡብ ክልል ፖሊስ የዞን ስራ ኃላፊዎች ጨምሮ ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎች መታሰራቸውን የደቡብ ክልል ፖሊስ አረጋግጧል።


የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ ለሬድዮ ጣቢያው ተከታዩን ቃል ሰጥተዋል ፦


" የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች አሉ ውሳኔያቸው ደግሞ ለሁለት በመሆን በአብላጫ በምክር ቤት የተወሰነው ውሳኔ እንዳለ ሆኖ በየወረዳ ምክር ቤቶቻቸው ላይ የተወሰነ ውሳኔ አለ።


ስለዚህ የዞኑ አመራር ሁሉንም አካባቢ በአግባቡ መምራት ያልቻለበት ሁኔታና አካባቢው ላይ ፅንፈኞች ያልሆነ ወሬ እየነዙ እና ምስራቅ ጉራጌ፣ የምእራብ ጉራጌ በሚል ክፍፍል እየፈጠሩ በውስጣቸው ያለውን አብሮ የሚኖረውን ብሄር የቀቤና፣ የማረቆ የሌላም እንደዚህ በብሄሮች መካከል ልዩነት እየፈጠሩ ግጭት የሚቀሰቅሱ አካላት አሉ።


... ማንም ሰው ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ በአግባቡ በስርዓት መጠየቅ መነጋገር፣ መወያየት፣ መወሰን መብቱ ነው ነገር ግን ተቀጥረው ህዝቦችን ለማጋጫት ስራ የሚሰሩ አካላት አሉ በዚህ ምክንያት ነው የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች ጭምር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ምርመራ እየተጣራባቸው ነው። አሁን በአካባቢው የተለየ የፀጥታ ችግር የለም "


ከወልቂጤ ከተማ ቃላቸውን የሰጡ አንድ ነዋሪ ደግሞ ወንድማቸው ለወቅታዊ ጉዳይ ስብሰባ ተብሎ ተጠርቶ መታሰሩን ገልፀዋል።


ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች የሚታሰሩ ሰዎች ወደማይታወቅ ቦታ እየተወሰዱ መሆናቸውን ቢገልፁም የክልሉ ፖሊስ ትክክል አይደለም በህጋዊ መንገድ የተያየዙ በዛው በወልቂጤ ከተማ በተጠርጣሪ ማቆያ ውስጥ ናቸድ የትም አልተወሰዱም፤ ነገር ለማጋነን ካልተፈለገ በስተቀር ሲል ለቪኦኤ ሬድዮ ገልጿል።


በደቡብ ክልል ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች በየምክር ቤቶቻቸው ተሰብስበው መንግስት በስቀመጠው የክላስተር አደረጃጀት ከሳምንታት በፊት ውሳኔ አሳልፈው ፤ ለፌዴሬሽን ምክር ቤትም አቅርበው ነበር።


በዚህ ውሳኔ ከሁሉም የጉራጌ ዞን ብቸኛ በመሆን የዘመናት የህዝብ ጥያቄ የሆነው የክልልነት ጥያቄ ይመለስ ክላስተር አንደግፍም የሚል ውሳኔ አሳልፏል።


ከዚህ ውሳኔ በኃላ በዛው ያሉ ወረዳዎች አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠው ክላድተር እንደግፋለን የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።


በደቡብ ክልል ያሉ 6 ዞኖች እና 5 ልዩ ወረዳዎች ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ የህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ እየተጠበቀ ነው።

Report Page