VOA

VOA


የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።


በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።


ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ (በዓለን ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ) ፥ " ፍጥነቱ አሁን እየጨመረ ስለሆነ በዚህ ወር መጨረሻ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 30 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና የምግብ ሸቀጦች ወደ ትግራይ ይደርሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። እቅዳችን በሰኔ ወር መጨረሻ 100 ሺህ ቶን ምግብ ለማድረስ ነው " ብለዋል።


በሌላ በኩል ፤ የረድኤት ድርጅቶች አፋርን ጨምሮ በአጎራባችን ክልሎች ቀውሶች እየተባባሱ በመሆናቸው እጅ እያጠራቸው ፤ የእርዳታ ክምችታቸውም እየተመናመነ መሆኑን ጠቁመዋል።


ሰይድ ሞሃመድ (የዓለም አቀፉ ህፃናት አድን ድርጅት የአፋር ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዋና ኃላፊ) ፥ " ማህበረሰቡ ድብርብርብ ሸክም ነው የገጠመው ፤ የመጀመሪያው በርካታ የውሃ አቅርቦት እና ሌሎችም መሰረታዊ አገልግሎት ተቋማትን ስራ ያስተጓጎለው ያቋረጠው ግጭት በዚህ ላይ ድርቅ ሌላው ፈተና ነው። ላለፉት በርካታ አመታት አፋር በተከታታይ በድርቅ ሲጠቃ ነው የቆየው ፤ ስለሆነም ድርቁ ለአፋር ማህበረሰብ ሌላ ፈተና ነው ማለት ይቻላል " ብለዋል።


የዩክሬን ጦርነት እና ሌሎችም በዓለም ዙሪያ የታዩት ቀውሶች የለጋሾችን የረድዔት አቅም እየቀነሰው መሆኑ የታገለፀ ሲሆን WFP በሚቀጥለው 6 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚያስፈልገው የእርዳታ አቅርቦት የ522 ሚሊዮን ዶላር እጥረት እንደሚያጋጥመው ገልጿል።


ከዚህ ውስጥ 220 ሚሊዮን ዶላር ትግራይን ጨምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ለሚሰራው የረድኤት ስራ የሚውል ነው።


" ያለን ክምችት በጣም በፍጥነት እያለቀ ነው። ስለዚህ ስጋታችን ይህን አውንታዊ ድባብ ፈጥረን እነኚህን መተላለፊያዎች ከፍተን መልሰን ማቆም ሊኖርብን ነው እናም ሁሉ ነገር ከሚያዚያ በፊት ወደነበረው ስፍራ ሊመለስ ነው " ብለዋል።


የረድኤት ሰራተኞች እንደሚሉት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ድጋፍ በማድረስ በኩል ፍጥነታቸውን እየቀነሱ አይደለም ፤ WFP እንደሚለውም ወደ ትግራይ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከደረሰው የሚልቅ የምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እያመሩ ናቸው።


አሁን ላይ እያየለ የመጣውን የረሃብ አደጋ ለመታደግ ተጨማሪ እርዳታ ወደ ተጎዱት አካባቢዎች እየደረሰ ነው።


@TIKVAHETHIOPIA

Report Page