VI SL CMP FR VU TX BU PR በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ
Walia Tenderየግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት በግሼ ወረዳ ውስጥ ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ጥቅል ግዥ
ሎት 1.የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣
ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያ፣
ሎት 3 የኮምፒውተር ቀለምና የፎቶ ኮፒ ቀለም፣
ሎት 4.ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣
ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃ፣
ሎት 6 አላቂ የጽዳት እቃ፣
ሎት 7 የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ፣
ሎት 8 የተዘጋጁ ልብሶችና ብትን ጨርቅ፣
ሎት 9 ጫማዎችና የቆዳ ውጤቶቸ
ሎት 10.የስፖርት ማቴሪያል፣
ሎት 11 የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣
ሎት 12 የተለያዩ ህትመቶች
በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ አግባብ ያለው ህጋዊ ንግድ ስራ ፍቃድ ያለው/ያላት፡፡
- 2የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው፡፡
- ለተሽከርካሪ መለዋወጫ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200.000/ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር -4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በግልፅ የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ሎት1 ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ለሎት 2 ብር 50/ሃምሳ ብር/ ሎት3 ብር 40/አርባ ብር/ሎት 4.ብር 50/ሃምሳ ብር/ ሎት 5 30/ሰላሳ ብር ሎት 6, 30/ሰላሳ ብር ሎት 7.ብር 50/ሃምሳ ብር/ሎት 8.ብር 40/አርባ ብር/ ሎት 9.ብር 30/ሰላሳ ብር/ ሎት 10.ብር 20/ሃያ ብር/ሎት1 ብር 50/ሃምሳ ብር/ ሎት 12.ብር 20/ሃያ ብር ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 መግዛትና ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 ፐርሰንት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሆኖ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ከባንክ የተረጋገጠ Letter of credit ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የእለት ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ለየብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለተጫረቱበት ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 1% ሲያሲዙ በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት በግዥ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 16 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና በመሙላት እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት አለበቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 06 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል ተጫራቶች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው አካል ውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሎት መሆኑ ይታወቅ ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0338119866/0338990102 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ከላይ ያልተገጸ ካለ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የህዝብ በአላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
__________________
Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 10፣2013
Deadline:በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00
__________________
© walia tender