Used2 metec

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኮ/ ሎ/ ሰ/ ማ/001A/2012
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) በስሩ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተከማቹ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ባለበት ሁኔታና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው፣ በዘርፉ የተሰማሩበት የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በዘመኑ የታደሰ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
የነዋሪነት መታወቂያ ካርድ ኦሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣
የጨረታ የሚያስፈልጉ ቅጾችን ንፋስ ስልክ ፖሉ ቴክኒክ ኮሌጅ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 27 ኮርፖሬት ፋይናንስና ኢንቨስትመንት በመቅረብ ዝርዝር መረጃ የያዘ የተ ራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ከዚህ በታች በተመለከተው መሠረት የማይመለስ ብር በመክፈል በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፤
ሎት 1 የተለያዩ የመኪና ተሽከርካሪ ወንበር ብር 200
ሎት 2 የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች ብር 200
ሎት 3 የተለያዩ ኤሌክትሪክ እቃዎች ብር 200
ሎት 4 የተለያዩ የቧንቧ እቃዎች ቫልብ ፣ የእጅ መታጠቢያ የሳሙና ማስቀመጫ የሻወርና የመፀዳጃ ቤት እቃዎች ብር 100
ሎት 5 የተለያዩ አይነት የቧንቧ እቃዎች ብር 100
ሎት 6 የተለያዩ የTee upvc እቃዎች እና ኤልቦ/ELBOW} ብር 200
ሎት 7ቲስ TS Reducing Socket ብር 100
ሎት 8 ፖይፕ ዩፕቪሲ PPE UPVC ብር 200
ሎት 9 የተለያዩ መፍቻዎች/ WRENCH/ ብር 200
ሎት10 የተለያዩ መፍቻ ማያያዣ /SOCKET) ፣ ምእዛኝ (TRY SQUARE) እና ብሎን ማጥበቂያ /SPANNER/ ብር 100
ሎት 11 መቁረጫ (CUTTER እና አራት ማዕዘን መዶሻ (HAMMER) ብር 200
ሎት 12 የተለያዩ የግንባታ መሳሪያዎች DIFF TOOLS ብር 200
ሎት 13 የተለያዩ የወላለቁ እና የተሰባበሩ የእንጨት ውጤቶች ብር 200
ሎት 14 የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች ብር 200
ሎት 15 የቢሮ ፈርኒቸሮች ብር 200
ሎት 1 6 ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች ብር 200
ሎት 17 ላፕ ቶፕ ኮምፒዩተሮች ብር 200
ሎት 18 ብስክሌት ብር 100
6. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ሰነዶች በሙግዛት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን በሰነድ ላይ በተጠቀሱት ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
7. ንብረቶቹን ለማጓጓዝ፣ የጭነት ወይም የሌሎች ተያያዥ ወጪዎች በገዥው የሚሸፈን ይሆናል፣
8. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ከሎት 1 እስከ ሎት 18 ድረስ ለተጠቀሱት የተለያዩ ዕቃዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 2 በ100 (2%) የጨረታ ማስ ከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሠነድ ጋር በማያያዝ ሳጥን ውስጥ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
9. የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነድ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል። በእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን የ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ያልያስያዘና በሠ ነደ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ወዲያውኑ ውድቅ ይደረጋል።
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ5 ፡00 ሰዓት ተጫራ ቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በንፋስ ስልክ በሚገኘው ሎጀስቲክስ እና ሰፕላይ ማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። እንዲሁም ተጫራቾቹ በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት ኢያስተጓጉልም፣
11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀሳቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻለ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፣
12. ኮርፖሬሽኑ ሳወጣው ጨረታ ሰነድ ላይ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃሎ በመከፈል ንብረቱን በአንድ ወር ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
14.ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡ - 09 11 16 80 55 ፣ 0912 08 0974 እና 0912 83 24 69 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፣
15 ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፣
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 05 ቀን 2012
Deadline: June 1, 2020
© walia tender