Used nile insur17

Used nile insur17


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር-002/2012

ኩባንያው ሊያስወግዳቸው የሚፈልጋቸውን

የቶነር ካርትሪጅ ፤
ጋዜጣና መፅሄት፤
ምንጣፍ፤
ጎማ፤ ባትሪ፣ የመኪና መለዋወጫ ፤
የካፍቴሪያ ዕቃዎች ፤
የኮምፒተርና ተዛማጅ ዕቃዎች ፤
የጠረጴዛ ጣውላዎች፤እና የመሳሰሉትን በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች በቀረበው መሠረት መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ ውን የማይመለስ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ሠነዱን ከዚህ በታች ከተቀመጠው አድራሻ በመውሰድ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ስለሆነም ተጫራቾች

በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተገለፀው መሠረት ለሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የሚያቀርቡትን ዋጋ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለየዓይነቱ በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተገለፀው መሠረት በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ሠነድ (CPO) ብቻ አብሮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ዕቃዎቹን ጐተራ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመመልከትና ለዚህ ዓላማ የተዘጋጀውን ቅጽ ያለ ክፍያ ከኩባንያው ሃብት ሥራ አመራር መምሪያ 3ኛ ፎቅ በመውሰድ የተ.እ.ታክስን ጨምሮ የግዥ ዋጋቸውን እስከ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 3 ፡00 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከታች በተጠቀሰው አ ድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸውል።
ጨረታው በዕለቱ ግ ንቦት 25 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 3 ፡15 ሰዓት ተጫ ራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ውጤቱ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ ክፍያውን በማጠናቀቅ ዕቃውን ተረክበው ማውጣት አለባቸው። ይህ ባይሆን ጨረታውን በፈቃዳቸው እንደሰረዙት ተቆጥሮ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፣ ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ. ማ ዋና መ/ ቤት / ጉተራ /

ሃብት ሥራ አመራር መምሪያ /3 ኛ ፎቅ/

ስልክ ቁጥር 0114-42-60-00

የመሣ. ቁ 12836

አዲስ አበባ



Posted: ሪፖርተር ግንቦት 17 ቀን 2012
Deadline: June 2, 2020


© walia tender

Report Page