Used lideta 1

Used lideta 1

Walia Tender

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ



በልደታ ክፍለ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች
አገልግሎት የሰጡ የመኪና መለዋወጫዎች
ያገለገሉ ጎማዎች


ተጫራቾች የጨረታ ማ ስከበሪያ ብር 50.00/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ የሰነዱ መሽጫ ቦታ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ቢሮ ቁጥር 102 ነው፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ 6ተኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዋጋ የሞሉትን ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበ ት በአስረኛዉ ቀን በ 8:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 8:30 ላይ በክፍለ ከተማው በፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ ቤት ጠቅላላ አገልግሎት 6 ተኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች የገንዘብ መጠኑን በቁጥርና በአሃዝ መፃፍ ይጠበቅባቸዋል
የዘገየ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ላይ ተቀባይነት የለውም
ከፍተኛው ጨረታ በመነሻነት በተያዘው ዋጋ ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ኮሚቴው ከፍተኛውን የጨረታ ዋጋ ሊቀበል ይችላል፡፡
ጨረታ የወጣውን እቃዎች ሰነድ መግዛቱ ከተረጋገጠ በኋላ ደረሰኙን በማሳየት የንብረቱ ዝርዝር የሚገኝበት ቦታ በልደታ ክ/ከተማ ጎማ ቁጠባ ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ እና ዛገዌ ህንጻ ጎን በሚገኘው 6ኛ ፎቅ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላል
አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ከ/ክፍለ ከተማው ግቢ በ 2 ቀን ውስጥ ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡
በተጠቀሰው ቀን ማንሳት ካልተቻለ ባደረበት ቀንብር 500 እየጨመረ የሚሄድና ከ5 ቀን በኋላ ንብረቱ ይወረሳል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ

በልደታ ክ/ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ ቤት መጠየቅ ይችላሉ የመስሪያ ቤቱ ስልክ ቁጥር 0118548855

የልደታ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው

ሀብት ልማት ጽ/ ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር

ጠቅላላ አገልግሎት ደጋፊ የስራ ሂደት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 29 ቀን 2012

Deadline: June 15, 2020


© walia tender

Report Page