Used jinka1

Used jinka1

Walia Tender

ያገለገሉ ዕቃዎች የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ


በኢትዮጵያ ኮንስትራከሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ኮንስትራከሽን ዘርፍ የጂንካ መንደር መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት

በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የወዳደቁ ብረቶች ፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ጎማዎች ፣ የተለያየ አምፔር ያላቸው ባትሪዎች ፣ የተለያየ አሮጌ መለዋወጫዎች፣ ባዶ የአስፓልት የዘይት በርሜሎች ፣ አሮጌ ቆርቆሮዎች ፣ ብረታ ብረትና የብረት ውጤቶች፣ የካምፕ እቃዎች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችና ገመዶች ፣ ለመሽጥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተጫራቶችን ይጋበዛል፡፡

ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጉርድ ሾላ መንገድ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 200 ሜትር ገባ ብሎ ሉሲ አካዳሚ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ባለው ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100 ( አንድ መቶ ብር ) የኢትዮጵያ ብር በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታው አሽናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛጎም አቅራቢ ክፍት ነው፣ የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው።

አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን በጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን በ28/9/2012 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ነው፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 28 /9/ 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ጊቢ በሚገኘው የጥቅል ግዥ ቡድን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጨረታ መጠን ከ8,000 ብር ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 28/9 ቀን 2012 ዓም ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ::
ስልክ ቁጥር፡- 09-11-88-59-95 ፣ 09-04-83-02-24 ፣09-38-97-05-54

የጂንካ መንደር መንገድ ዲዛይንና ግንባታ ፕሮጀክት


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 19 ቀን 2012

Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page