Used diredawa rev1

Used diredawa rev1

Walia Tender

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 0031/2012

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው ውርስ ሆነው በድሬደዋ መጋዘን የሚገኙ ብዛት 1801 ካርቶን ሻማ ሰኔ 1/2012 ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ለሚሸጠው እቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴውን ያሳወቀበት የቅርብ ጊዜ የተሰጠውን የምስክር ወቀት እና መለያ ቁጥሩን የሚያቀርብ መሆኑን ይጠበቅበታል።

በዚሁ መሠረት፡

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ግቢ ነው፡፡
ተጫራቾች እቃዎቹ በሚኙበት በድሬዳዋ መጋዘን ተገኝተው ማየት የሚገባ ሲሆን ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቄ አይሆንም።
ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ነው።
ለሽያጭ የቀረበው እቃ ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት።
ተጫራቾች ለሚጫረታቸው እቃዎች ለጨረታው ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ 100,000 (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በማሰራት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ማንኛውም በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራች ለምዝገባ ሲቀርብ ከላይ የተጠቀሱትን ለምዝገባ የሚያስፈልጉትን መረጃዎች ከሲፒኦ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።
ጨረታው ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ . ም ከጠዋቱ 2 ፡ 00 ሰዓት ጀምሮ ምዝገባ የሚጀምር ሲሆን ምዝገባው እንደተጠናቀቀ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ላጋር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ይካሄዳል።
በጨረታ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ በ3 ቀን ውስጥ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ከሆነ ያስያዘው ሲፒኦ ከሽያጩ ጋር የሚታሰብ ይሆናል።
በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ውጤቱ ለመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ቀርቦ እስከሚፀድቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃ አሸናፊ ለመሆኑ በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን ማንሳት ይኖርበታል። ይህንን ባያደርግ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ያለምንም ተጨማሪ ማስጠንቀቂያ ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
ማንኛውም የጨረታ አሸናፊ በጨረታ የያዛውን እቃ ወደ ሌላ አካባቢ ይዞ ለመጓዝ የመንገድ ደብዳቤ እንዲጻፍለት የጠየቀ እንደሆነ የሚጻፍለት ደብዳቤ የንግድ ፈቃዱን ባወጣበት አካባቢ ወይም ተከራይቶ የሚጠቀምበት መጋዘን በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ሕጋዊ ማስረጃ ሲያቀርብ እቃውን ከተረከበበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የ3 /ሦስት ተከታታይ ቀናቶች ብቻ ሚያገለግል የመንገድ ደብዳቤ ይሰጠዋል።
ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 025-1-12-49-28 መደወል ይቻላል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: July 10, 2020


© walia tender

Report Page