Used civil2

Used civil2


የጨረታ ማስታወቂያ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ጄኤስአይ ፣ሲሲ.ኤፍ.ዲ. ፈረንሳይ ካቶሊክ ኮሚዩኒቲ፣ ኤልተርን ፎር አፍሪካ፣ ዲኬት ፣ሲኤንኤፍኤ. እና ሜዲሲን ሳንስ ፍሬነቸርስ ስፔን የተባሉ ድርጅቶች ሲገለገሉባቸው የነበሩ

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን፤
ላፕቶፖች፣
ጀነሬተሮች፣
በርሜሎች እና
የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-

ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በወጣ ከ5ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ፒያሳ ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንጻ በኤጀንሲው መኪና ማቋሚያ ቦታ ፣ ሰባተኛ ፎቅ ፣ጉርድ ሾላ ሱናርማ (ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና አጠቃቀም ማህበር) የተከራየው ግቢ መኪና መቋሚያ እና ቃሊቲ ከማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ በስተቀኝ በሚያስገባው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ኒያላ ኢንሹራንስ የተጎዱ መኪኖች ማቆያ ፊት ለፊት በሚያስገባው መንገድ 200ሜ.ገባ ብሎ በሚገኘው ኤጀንሲው በተከራየው መጋዘን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 7፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤
ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመ ቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በጸደቀ በ 3 (ሦስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል ፡፡
ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ኣዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ በሚገኘው የኤጀንሲው ዋና መ/ቤት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት (10) ለዕቃ እና ለተሽከርካሪ አስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ በአስረኛው ቀን (10) እና በአስራ አምስተኛ ቀን የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኢ ለኤጀንሲው ገቢ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ከኤጀንሲው ግዢና ፋይናንስ የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለቤትና ለቢሮ እቃዎች የማይመለስ 100 ብር/ አንድ መቶ ብር/ ለተሽከርካሪ 150/ አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት (ለዕቃ) እና ለተሽከርካሪ አስራ አምስት/5/ ተከታታይ የስራ ቀናቶች ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለዕቃ አስረኛው ቀን (10) እና ለተሽከርካሪ በአስራ አምስተኛው ቀን ሰነዱ የሚሸጠው እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10 ) እና አስራ አምስት/15/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ለዕቃ አስረኛው የስራ ቀን (10) እና ለተ ሽከርካሪ በ15 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4 ፡30 ሰዓት የተጫራቾቹ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ በሚገኘው የኤጀንሲው ዋና መ/ ቤት 7 ኛ ፎቅ ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011-5582402 /011-5582437 /011-5582408

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ




Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012
Deadline: June 12, 2020


© walia tender

Report Page