Used car oromia pro1

Used car oromia pro1

ADMIN 3 SELAMAWIT
በመላው ሀገሪቱ በሁሉም ጋዜጣዎች የሚወጡ መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በድህረገጻቸው በተጨማሪም ለዋልያ ቴንደር የሚላኩ ሁሉንን ጨረታዎች በቴሌግራም ይከታተሉ!

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2012

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ ጽ/ቤቶች የሆኑ በክልል፣ በዞንና በወረዳ የሚገኙ

የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፤
ሞተር ሳይክሎች፤
ጄኔሬተሮችና
ቁርጭራጭ ብረታብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ።

የኤጀንሲው አድራሻ፣ አዲስ አበባ ሳርቤት ከፑሽኪን አደባባይ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት ሳይደርስ ቤተልሔም ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አንደኛ ፎቅ በመቅረ ብ የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 ሰዓት- 11፡00 ሰዓት ብቻ ነው።

የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከ3፡00 ሰዓት-11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ. ም ከጧቱ 4 ፡30 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ ቤት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋ ጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ በባ ንክ የተረጋገጠ CPO በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓም ከጥዋቱ በ4 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4 ፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0917813660 የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ / ፊንፊኔ/ አዲስ አበባ CPO ለማስራት፡-

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ/

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 27 ቀን 2012

Deadline: July 9, 2020


© walia tender

Report Page