Used car The donkey sanctuary

Used car The donkey sanctuary


የጨረታ ማስታወቂያ

ዶንኪ ሳንክችዋሪ ኢትዮጵያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ስሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች

የተሽከርካሪዎች ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ግንቦት 28/2012 ዓ/ም ድረስ ቦሌ መንገድ ሳይ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ተሽከርካሪዎቹን በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ድርጅቱ በሚያዘጋጀው አስጎብኚ ማየት የሚችሉ መሆነን ስንገልፅ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የወሰዱ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ግንቦት 21/2012፣ ግንቦት 24/2012 እና ግንቦት 27/2012 ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ማየት ይችላሉ።

ተጫራቾች እያንዳንዱን ተሽከርካሪ የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው በመቅረብ እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።

የሚጫረቱበትን ተሽከርካሪ መነሻ ዋጋ 5% በባንክ ክፍያ መያዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ዝውውር እና ቀረጥ ላልተከፈለባቸው ተሽከርካሪዎች ቀረጡን እንዲሁም ተያያዥ የመንግሥት ክፍያዎችን የሚከፍሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልያስያዘ ተጫራች ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም።

ጨረታው ግንቦት 28/2012 ዓ. ም ተዘግቶ ግንቦት 29/2012 ዓ. ም የሚከፈት ሲሆን የአሸናፊዎቹም ስም ዝርዝር በድርጅቱ የማስታወቂያ ቦርድ ላይ የሚለጠፍ ይሆናል። በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ሰኞ ሰኔ 1/2012 ዓ.ም ከድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን መሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘ ዶንኪ ሳንክችዋሪ ኢትዮጵያ

ቦሌ መንገድ ላይ ህንፃ 4 ኛ ፎቅ

ስልክ 0116 185708

ፖ. ሳ. ቁ. 1055/1250



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 20 ቀን 2012

Deadline: June 10, 2020


© walia tender

Report Page