Used KK1

Used KK1

Walia Tender

ማስታወቂያ

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለተረፈ ምርትና የተጋቡ

የማሸጊያ ዕቃዎች፣ አዲስና ያገለገሉ የግንባታ ዕቃዎች፣

ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች ፣ ያገለገሉ የከባድ ኮንስትራክሽን

ማሺነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና ያገለገሉ ኮምፒዩተርና

ተያያዥ ዕቃዎች ለመሽጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በምርት እና በሌሎች ተያያዥ እንቅስቃሴዎች የሚጠራቀሙ

ልዩ ልዩ ተረፈ ምርቶችና የተጋቡ የማሽጊያ ዕቃዎች፣
አዲስና ያገለገሉ የግንባታ ዕቃዎች፣
ያገለገሉ የቢሮ ዕቃዎች፣
ያገለገሉ የከባድ ማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣
ያገለገሉ ኮምፒዩተርና ተያያዥ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለዚህ የሚከተለው አሰራር ሥራ ላይ ስለሚውል ተጫራቾች ይህንን ተገንዝበው የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

1ኛ. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ዕቃዎች ናሙና ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የፋብሪካው ቅጥር ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡

2ኛ. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው የቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ያለበትን ሰነድ በማይመለስ ብር 50 መግዛት ይችላሉ፡፡

3ኛ. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT)ን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ከጨረታ ሰነዱ ጋር የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4ኛ. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ፣ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ኮፒ አንድ ላይ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ( ቅዳሜን ይጨምራል) ውስጥ ዋናው መስሪያ ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

5ኛ. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አጠገብ ባለው የኩባንያው ዋና መ/ ቤት 4 ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ የጨረታ ኮሚቴው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6ኛ. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው የተረፈ ምርቶችና የተጋቡ የማሽጊያ ዕቃዎች ከኩባንያው ጋር ለስድስት ወር የሚቆይ ውል የሚዋዋሉ ሲሆን የመልካም ሥራ አፈፃፀምን /performance Bond/ በተመለከተ በሚጠራቀመው የዕቃ መጠን ላይ በመመስረት የእቃውን ዋጋ 10% በሲ. ፒኦ ያስይዛሉ፡፡ ለ ሌሎች ዕቃዎች የአንድ ጊዜ ሽያጭ ውል መረከብ ይችላሉ፡፡

7ኛ . ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በጠቅላላ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ 0115 15 90 15 / 0911 82 06 02 ይደውሉ።

ኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 28 ቀን 2012
Deadline: June 19, 2020


©walia tender

Report Page