Used 2 ad bank.rav4

Used 2 ad bank.rav4


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ለሰጠዉ ብድር በዋስትና የያዛቸዉን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።በዚሁ መሰረት ማንኛዉም ተጫራች ሐራጁ በሚካሄድበት ቀን ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት በጨረታዉ ተወዳድሮ ንብረቱን እንዲገዛ ተጋብዟል፡፡

ተጫራቾች የ ጨረታዉን መነሻ ዋጋ 25% በ ባንኩ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ(cpo) አሰርቶ በጨረታው እለት ይዞ በመቅረብ ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ።
ጨረታዉ በማስታወቂያዉ ላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ፣ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ፣ ታዛቢዎች በተገኙበት፣ የመያዣ ንብረቱ በሚገኝበት የሚካሄድ ይሆናል።
የጨረታዉ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ ጨረታዉ ከተከናወነበት ማግስት ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀን ዉስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ዉስጥ ካልከፈለ ግን ለጨረታ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታዉ ተሰርዞ ለሐራጅ የሚቀርብ ይሆናል፡፡በጨረታዉ ተሳትፈዉ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወዲያኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
ኃ/የተ/የግል ማህበርን ወይም አክሲዮን ማህበርን ወክሎ መጫረት የሚፈልግ ሥራ አስኪያጅ ወይም ም/ሥራ አስኪያጅ የድርጅት የመመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ይዞ መቅረብ ያለበት ሲሆን የሥራ አስኪያጅ ወይም የም/ሥራ አስኪያጅ ለዉጥ ተደርጎ ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የቃለ ጉባኤ ከመመስረቻ ጽሑፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ጋር ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
የጨረታዉ አሸናፊ ለመንግስት የሚከፈለዉን ማንኛውንም አስፈላጊ ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ቀረጥ ክፍያ ይከፍላል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉ ንብረት ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ከጨረታዉ ቀን በፊት ባሉ የስራ ቀናት እና ሰዓት በባንኩ አበዳሪ ቅርንጫፎች በመቅረብ በሚያዘጋጀዉ ፕሮግራም መሰረት ንብረቱ ያለበትን ሁኔታ መመልከት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ አዲስ እንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ሕግ አገልግሎት በስልክ ቁጥር 0115571934፣ ቦሌ መ/አለም 0116670386 እና አብይ ቅርንጫፍ0115570501 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::
አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ አ. ማ.



Posted: ሪፖርተር ግንቦት 02 ቀን 2012
Deadline: June 6, 2020


© walia tender

Report Page