Unk 1
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር EiABC/NCB/004/2012
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥላ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ አርኪቴክቸር ሕንፃ ግንባታ እና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት ለ2012 ዓ.ም ከመንግሥት በተመደበለት በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን ለሁሉም ሎቶች 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር)
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልተው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፤በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር/በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ የተመዘገቡበትን የአቅራቢነት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ከተቋሙ በጀት እና ፋይናንስ መምሪያ ሙግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ የተገለጸውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋና 4፡30 ሰዓት ላይ በተቋሙ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያ ቀን የእረፍት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚዘጋና ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ አርኪቴክቸር ሕንፃ ግንባታ እና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት (የቀድሞ ሕንፃ ኮሌጅ) ልደታ ከከፍተኛው ፍርድ ቤት አጠገብ ፖ.ሳ.ቁ 518 ያግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር፡- 0112780934
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ አርኪቴክቸር ሕንፃ ግንባታ አና ከተማ ልማት ኢንስቲትዩት
Posted date: አዲስ ዘመን መጋቢት 12፣ 2012
Dead line:April 3, 2020 (መጋቢት 25)