Ultrasound in IBD

Ultrasound in IBD

Crohn’s & Colitis Ethiopia

🟣 አልትራሳውንድ ምንድን ነው?

አልትራሳውንድ፣ ወይም ሶኖግራፊ በመባል የሚታወቀው፣ የሰውነትን የውስጠኛ ክፍል በተንቀሳቃሽ ምስል በመስራት የሚያሳይ ነው። ምርመራው በእጅ በሚያዝ መሳሪያ የድምፅ ሞገዶችን በመጠቀም የሚካሄድ የምርመራ ዘዴ ሲሆን ወደተፈለገው የሰውነት አካል አካባቢ ሲጎተት በሚፈጠረው የድምጽ ሞገድ መሳሪያው አንብቦ ምስል ይፈጥራል።


ይህ ምርመራ ጨረር የማይለቅ፣ ሰውነታችንን በማይጎዳ መልኩ በምስል የመመርመሪያ ዘዴ ነው።


አልትራሳውንድ ከሚያሳያቸው የአንጀት ሁኔታዎች አንዳንዱ፡


• የአንጀት ግድግዳ ውፍረት

• የአንጀት መጥበብ ደረጃዎችን ለመለየት

• ፊስቱላ (በአካል ክፍሎች/ቆዳ መካከል ያሉ ያልተለመዱ ክፍተቶች)

• ማበጥ (መግል መቋጠር)


🟣 አልትራሳውንድ ሂደት እንዴት ነው?


የአሰራር ሂደቱ ታካሚው በጀርባው ላይ በመተኛት ይጀመራል። ይህም የሆድ አካባቢን በመሳሪያው በቀላሉ ለመድረስ ያስችላል። በመቀጠል ውሃ አዘል ጄል ሆድ ላይ ይቀባል። ይህም አየር በመሃል ገብቶ በመሳሪያው የሚተላለፈውን የድምፅ ሞገዶች እንዳያስተጓጉል ይከላከላል። ይህ አጭር ሂደት ሲሆን እንደ CT ስካን ወይም ኤክስሬይ ሳይሆን ታካሚውን ለጨረር አያጋልጥም።



🟣 አልትራሳውንድ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?


የ አልትራሳውንድጥቅሞች የአንጀት ግድግዳ ውፍረትን በፍጥነት ለመገምገም ይጠቅማል።

የቀለም ዶፕለር ሶኖግራፊን በመጠቀም የአንጀትን የደም ቧንቧን ማየት የ አልትራሳውንድ ሁለተኛ ጥቅም ነው።

ሦስተኛው ዋነኛ ጠቀሜታ ከሌሎች የምስል ምርመራ ዘዴዎች ጋር ሲነጻጸር, የአንጀት ውስጥ የምግብን መንቀሳቀስ ሁኔታ በቀጥታ እይታን ያካትታል።


የ አልትራሳውንድ ምርመራው ብቻውን ሳይሆን ከላቦራቶሪ ምርመራ፣ የአንጀት ናሙና፣ ኢንዶስኮፒ እና የመሳሰሉትን ጨምሮ በሌሎች የምርመራ ዘዴዎች በመታገዝ የአንጀት ቁስለትን ለማግኘት እንዲሁም ለመከታተል ይጠቅማል። እንዲሁም እንደ እብጠቶች እና ፌስቱላ ያሉ ውስብስቦች በ አልትራሳውንድ ጊዜ በቀላሉ ሊገኙ ይችላሉ።


🟣 ማጠቃለያ 🟣


አንጀት ቁስለት ምርመራ አንድ ብቻ እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል ፣ እና ማንኛውም ዓይነት የምርመራ ዘዴዎች ፣ ኢንዶስኮፒ ፣ ኤምአርአይ ፣ የላብራቶሪ መለኪያዎች ወይም አልትራሳውንድ፣ በአንጀት ቁስለት ህክምና ላይ በተለያየ ጊዜ ለተለያየ ምክኒያት ሊታዘዝ ይችላል። ሆኖም አልትራሳውንድ ለየት የሚያደርገው ጨረር አለመልቀቁ፣ ዋጋው ከሌሎቹ አንጻር መቀነሱ፣ እንዲሁም ወደሰውነት ክፍል ሳይገባ ቆዳን ብቻ በመዳደስ የአንጀት ጤና ሁኔታን በምስል መልክ ማሳየቱ ነው።


ማጣቀሻ፡ The use of ultrasound in inflammatory bowel disease - PMC (nih.gov)

Report Page