Tx1

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ የ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት 2ኛ ዙር መገልገያ የሚሆን
የጽዳት እቃ ፤
መድኃኒቶች ፤
የደንብ ልብስ ስፌት፤
የጽህፈት መሳሪያዎች፣
ቋሚ እቃ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ።
ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ።
ግብር መከፈል ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን ኣይነት የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 408 መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት እቃዎች ቢድ ቦንድ/በሲፒኦ CPO/3000/ ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ሰነዱን ስያስገቡ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ወረዳ 07 ወጣቶች ማዕከል 1ኛ ፎቅ በመቅረብ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ 10 ቀናት ከዋለ በኋላ በ10 ኛው ቀን 11 ፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 11 ኛው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ተ ጫራቾች ወይም ህጋዊ ውኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በአላትና የእረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በሚቀጥሉት የስራ ቀናት በተመሳሳይ ወጣቶች ማዕከል 1ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል።
መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች በምትጫረቱባቸው እቃዎች ላይ ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ግዴታ ነው በአካል መምጣት ለማይችሉ እቃዎችም ቢሆን በፎቶ ሳምፕል ( ናሙና)ማቅረብ ይኖርባቸዋል ። ስልክ ቁጥር ፡-0118681289
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ ቤት የወረዳ 07 ጤና ጣቢያ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 15፥2012
Deadline: May 2, 2020