Tx adp

የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር AAPC/ NCB/006/ 2012/ ዓ . ም
የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በ2012 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፤
በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ያመልክቱ የሚል ጽሑፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፤
ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፤
የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድና የታደሰ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
የመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት።
አማራጭ ዋጋ እና አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና በአኢ/ከ/ፖሊስ ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰረተለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቶች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።
ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገባው ሠነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረቱበትን የዕቃዓይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ህትመት በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
ተጫራቾቹ የሰነድ ማስረከቢያ የሚያሲዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሠነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይንም አገልግሎቱም ስራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና ግምጃ ቤት ወይም በክፍል ስድስት በፍላጎት መግለጫ በተሰጠው ማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
በጨረታው ሰነድ በከፍል ስድስት(06) ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሠረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና የሚቀርብባቸው ናሙና መቅረብ አለበት።
ተጫራቾቹ ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀረቧቸውም ዕቃዎች ኮሚሽኑ ባወጣው ፍላጎት መገለጫ/እስፔስፍኬሽን መሰረት መሆኑን በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል።
ናሙናው ገቢ መሆን ያለበት ጨረታው በሚከፈትበት ቀን እስከቀኑ አራት ሰዓት ድረስ መሆን አለበት።
ተጫራቾቹ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርቦ እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመስስ አንድ መቶ ብር 100 ፡00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 - 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ16ኛ ቀን እስከ ከረፋዱ 04:00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ከፍት ሆኑ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግርና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
በጨረታ ሰነዱ ከፍል ሁለት ላይ በተጠቀሰው ቀን ከረፋዱ 4 ፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4 ፡30 ሰዓት ሲሆን በመስሪያቤቱ አምስተኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል።
የጨረታ መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል።
ዘግይቶ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በመከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0118625800/0111110448
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13፥2012
Deadline: May 6, 2020