Tx 7

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2012
የኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (ፖጥኢ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ሎት የተሽከርካሪ ጎማ ግዥ፣
2. ሎት የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ፣
3 ሎት Tablet with cover
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡
ተጫራቾች በዚሁ የስራ መስክ ለመስራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት በሲ.ፒ.ኦ 2000.00 ብር / ሁለት ሺህ ብር / ይ ሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 ብር መቶ ብ ር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ አበባ እስታዲየም መንገድ ትራንስፖርት ያለበት ተመሳሳይ ህንፃ ላይ በሚገኘው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ቢሮ ቁጥር 109 ምድር ላይ በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች እንደ አስፈላጊነታቸው ኢንስፔክሽን ለሚያስፈልጋቸው ናሙና ማቅረብ እና በተጠቀሰው ብዛት መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ተጫራቶች ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ፣ፋይናንሺያል ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ሲፒኦ በአንድ ፖስታ ከታሸገ በኋላ ማጠቃለያ በትልቅ ፖስታ ማሸግ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ዋጋውን በመሙላት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው የሚጠናቀቀው ሚያዝያ 28 ቀን 2012 8 ፡00 ተዘግቶ 8 ፡30 ይከፈታል::
ኢንስቲትዩታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው::
አዲስ አበባ እስታዲየም ትራንስፖርት ባለስልጣን ያለበት ግቢ መንትያ ህንፃ ምድር ቢሮ ላይ
ለበለጠ ማብራሪያ - በስልክ ቁጥር -011869 9897 ደውለው ይጠይቁ፡
የኢ. ፌ. ዲ. ሪ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት
አዲስ አበባ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13፥2012
Deadline: May 6, 2020