Tx 6

የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2012 ዓ.ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡
መድኃኒቶችን እና ሪኤጀንቶችን፤
የተለያዩ ህትመቶች፤
የደንብ ልብስ ስፌቶችን ፣
የጽዳት ዕቃዎችን እና
የጽሕፈት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ማንኛውም ሕጋዊ የንግድ ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በሥራ ሰዓት በመቅረብ እና የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እና የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እዮለጽን ጨረታው በ10 ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ11 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11 ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፡-
በግብር ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለጨረታ ማስከበሪያ መያዣ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ ሲፒኦ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን እንዲሁም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አስፈላጊውን የትብብር ደብዳቤ ለማወዳደር በሚከፈተው ፖስታ ማለትም በኮፒው ውስጥ በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፤
በተጫራቾች መመሪያ መሰረት በአቅራቢዎች ሊስት ላይ ድረገጽ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፤
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዝርዝር ጤና ጣቢያው ባቀረበው የዋጋ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት እና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤
ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ቁሳቁሶች ሁሉም ተጫራቶች ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር በጋራ ማቅረብ አለባቸው፤
ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችለው ከንግድ ፈቃዱ ጋር ተያያዥነት ባላቸው አቅርቦቶች/ አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።የሚቀርቡት ዋጋዎች ተጨማሪ እሴት ታክስን/ ተርን ኦቨር ታክስን ያካተቱ መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚወስደው መንገድ 200ሜትር ገባ ብሎ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0115536456/0115156192 በመደወል መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ ቤት ቂርቆስ ጤና ጣቢያ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 13፥2012
Deadline: May 4, 2020