Tx 43

Tx 43


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2012

የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር አየ/አ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት 02/2012 መሰረት የ2012 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ግዥ መለያ ቁጥር አየ/አ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት 02/2012

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/ በመከፈል መግዛት አለባቸው፡፡

3 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ ከላይ በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4 ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለማስገባት በሚመጣበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አብሮ ማስገባት አለበት፡፡ ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማናወዳድር መሆኑን በቅድሚያ ት/ቤቱ ይገልጻል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እንዲሁም CPO ከኮፒው ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ እና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በማግስቱ ማለትም በ11 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4 ፡00 ሰዓት በአየር አምባ 2 ኛ ደረጃ ት/ ቤት በቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫትን ያካተተ መሆኑ መገለጽ አለበት፡፡

7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (0%) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

8. ት/ቤቱ አሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ ሳይቀየር 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡

9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ 10 ቀናት ውስጥ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ ይኖርበታል፡፡

10. ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሀ. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

አድራሻ፡- በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 0 አስተዳደር ቦሌ ሚካኤል ሩዋንዳ ኤምባሲ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት

በስልክ ቁጥር፡- 011-626 03 99/011-626 22 8 / 011-869 09 03 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡



በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርት/ ቢሮ የአየር አምባ 2 ኛ ደረጃ ት/ ቤት









_______________________________
Category : Cleaning and Janitorial., Cleaning and Janitorial Equipments, Construction and Construction Machinery, Construction Raw Materials, Electrical and Electronics, Electronics Equipment, Office Supplies and Stationery, Stationery Supplies, Purchase., Textile and Leather Products, Textiles/ Fabrics and Wearing

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 17 ቀን 2012
Deadline :2020-04-09

Report Page