Tx 3

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡ - አ / ክ / ከ / መ / ል / ማ / የመ / ግዥ / አስ / ቡድን /02/2012
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለራሱና በስሩ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣
ሎት 2 ደንብ ልብስ እና የጽዳት ዕቃዎች፣
ሎት 3 ቋሚ ዕቃ ላፕ ቶፕ እና ኮምፒዩተር፣
ሎት 4 እፈር ማዳበሪያ ፍግ፣
ሎት 5 የመኪና ጥገና፣
ስስሆነም በጨረታው ተሳትፋችሁ ስመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች
ተጫራቶች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ፡ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ የመለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ሰነድ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የክፍያ ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነድ ከገዙ በኋላ እዛው ኛ ፎቅ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቶች ለጨረታ የሚወዳደሩበትን ለእያንዳንዱ ሎት ወይም የበጀት ርዕስ በሲፒዮ የብር መጠን ለሎት1. የጽህፈት መሣሪያዎች 2,000.00 / ሁለት ሺህ/ ሎት 2.ደንብ ልብስ እና የፅዳት ዕቃዎች 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ሎት 3.ቋሚ ዕቃላፕ ቶፕ እና ዲስክ ቶፕ ኮምፒዩተር 5,000.00/ አምስት ሺህ/ ሎት 4. አፈር ማዳበሪያ ፍግ 5,000.00/ አምስት ሺህ/ ሎት 5 የመኪና ጥገና 10,000,00/አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒዮ ማስያዝ አለባቸው።
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥርና የዕቃውን ዓይነት በግልጽ ኤንቨሎፕ ላይ በመጻፍና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠ/ አገ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ማስገባት አለባቸው
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ10 ኛው ቀን 11 ፡00 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ተዘግቶ በ11 ኛው ቀን 3 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ( ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ይከፈታል።
ተጫራቶች ጨረታው ከመከፈቱ1 ቀን በፊትናሙና ማቅረብ ላለባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙናው ለማይቀርብባቸው የዕቃ ዓይነቶች በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘሩትን ጥሬ ዕቃዎች የእያንዳንዱን ነጠላ ዋጋ ድምር ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምሮ ማካተት ይኖርባቸዋል።
ጽ/ቤቱ ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቀምባቸው መስፈርቶች ዕቃዎቹ መ/ቤቱ ባስቀመጠው እስፔስፍኬሽን መሰረት መሆናቸውን ወይም በሚቀርበው ናሙና፣ ጥራት፣ ዋስትና፣ አነስተኛ ዋጋና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።
ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሌሎች ተጫራቶች በሚያቀርቡት ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
በየሎቱ የሚሳተፉ ተወዳዳሪ ድርጅቶች በዘርፉ የሚሰሩ ድርጅቶች ብቻ መሆን አለባቸው::
አድራሻ :በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ o9 ቀዳማዊ ምኒልክ ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት ወይም ሲፒዩ ኮሌጅ አካባቢ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት
በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት
ጽ/ ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 14፥2012
Deadline: May 1, 2020