Turmeric Continued
Crohn's & Colitis Ethiopiaተጨማሪ የእርድ ጠቀሜታዎች
♦️እርድ በውስጡ የፀረ-ብግነት ባህሪ'ን ስላተላበሰ እንደ ሪህ ያሉ በሽታዎች እንዲሁም የጡንቻ እና መገጣጠሚያ ህመሞችን ለማስታገስ ይረዳል።
♦️በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮች በጉበታችን ውስጥ በማለፍ ይመክናሉ፤ እርድ ይህንን መርዛማነትን ከሰውነታችን የማስወገድ ሥራን እጅጉን ያግዛል ፤ በሰውነታችንም ያነሰ የመርዛማነት መጠን እንዲሁም የተነቃቃ ስርዓት-ፍርንት/Lymphatic System/ እንዲኖረን ያደርጋል።
♦️የእርድ ፀረ-ብግነታዊ ባህሪ ሴቶች የወር አበባ በሚያዩበት ወቅት የሚከሰትን ህመም ለማስታገስ ይረዳል።
♦️እርድን በቀን ሁለት ጊዜ መጠቀም በደማችን ውስጥ የሚገኘውን የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል።
♦️የእርድ ፀረ-ብግነታዊ ባህሪ ለመገጣጠሚያ ህመም ተመራጭ ያደርገዋል ፤ ምናልባትም ከIbuprofen የተሻለ ውጤታማ ሊሆን ይችላል።
♦️በእርድ ውስጥ የሚገኘው Curcumin የተሰኘው ንጥረ ነገር የደም ስሮቻችንን የውስጠኛውን ግድግዳ የሚሸፍነውን የመጀመሪያውን ንብር በማገዝ፤ የሰውነት ግፊትን እንዲሁም የደም መርጋትን ይከላከላል። የደም ባንቧችን የውስጠኛው ንብር ሥራ መዛባት ለልብ ህመም መከሰት ዋነኛውን ድርሻ ይይዛል። ስለዚህ እርድን መጠቀም የልባችንን ጤና እንዲሁም ደስታ ይጠብቃል።
ለምን እርድ ውስጥ ቁንዶ በርበሬ እንጨምራለን?
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ የእርድን የመድሐኒትነት ባህሪ ጥናቶች አረጋግጠዋል። አብዛኛው ሰው ቁንዶ በርበሬን ለቅማ ቅመም መጠቀም እንጂ ከቁብም አይቆጠረም ፤ ነገር ግን ለጤና እጅግ ጠቀሜታ አለው።
በእርድ እንዲሁም በቁንዶ በርበሬ ውስጥ የሚገኙ ዋነኛ ገቢር ይዘቶች ለፀረ ብግነት እንዲሁም ለፀረ-ኦክሲዳንት ባህሪያት በተጨማሪም በሽታን የመከላከል አቅም መኖር የበኩላቸውም አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
በእርድ ውስጥ የሚገኘው ዋነኛ ውህድ፣ Curcuminoid ይባላል። Curcumin እራሱ በእርድ ውስጥ የሚገኝ ዋነኛ ገባሪ እንዲሁም እጅግ ጠቃሚ ይዘት ነው።እንደ Polyphenol'ነቱ፣ Curcumin ለጤና ዘርፈ ብዙ ጥቀሜታዎች አሉት። ከእነዚህም መካከል፦ ሀይለኛ ፀረ ኦክሲዳንት ነው፤ በተጨማሪም ፀረ-ብግነት፣ ፀረ ባክቴርያ እንዲሁም ፀረ-ፈንገስ ባህሪያትን ተላብሷል።
ሆኖም ግን፣ የCurcumin ትልቁ ድክመት ወደ ሰውነታችን አመርቂ በሚባል ደረጃ አይሰርፅም፤ በሚያሳዝንም ሁኔታ በእርድ ውስጥ የሚገኘው Curcumin ወደ ደማችን ፍሰት ውስጥ እምብዛም አይቀላቀልም። በዚህም ምክኒያት የጤና እምርቶቹን ከመቋደስ ልንጎድል እንችላለን።
ይህ በእንዲህ እንዳላ፣ ቁንዶ በርበሬን እርድ ውስጥ መጨመር ግን ሊረዳን ይችላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፣ በቁንዶ በርበሬ ውስጥ የሚገኘውን Piperine የተሰኘ ንጥረ ነገር እርድ ውስጥ ከሚገኘው Curcumin ጋር እብሮ መጠቀም የCurcumin'ን ወደ ሰውነታችን የመሰረፅ እድሉን በ2000% ያህል ያሳድገዋል።
ቁንዶ በርበሬ በውስጡ Piperine የተሰኘ ህይወት-ገቢር ንጥረ ነገርን ይዟል። ጥናቶችም እንዳሳዩት Piperine ፦ የማቅለሽለሽ ስሜት ማሻል፣ የእራስ ምታት ህመምን ማስታገስ ፤ ደካማ የምግብ መፈጨት በሚኖርበት ጊዜ ማገዝ ፤ በተጨማሪም በውስጡ የፀረ-ብግነት ባህሪን ተጎናፅፏል። ይህ በእንዲህ እንዳላ ዋናኛው የPiperine ገፀ በረከት ግን የCurcmin'ን ወደ ሰውነታችን የመሰረፅ መጠንን መጨመር ነው።
እርድ ለማን አይመከርም?
እርድን የማዕዳችን ክፍል በማድረግ መጠቀም ደህንነቱ ፍፁም የተጠበቀ ነው። ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ግን፤ በልዩ መልክ ከእርድ የሚዘጋጁ በኪኒን እና በሽሮፕ መልክ የሚቀርቡ ተጨማሪ ምግቦች ላይ ነው።
እነኚህን በልዩ መልክ ከእርድ የሚዘጋጁ ተጨማሪ ምግቦችን ከመጠቀም መቆጠብ ሊኖሩብን ከሚያስችሉ ሁኔታዎች መካከል፦
፨ የጨጓራ አሲድ የሚቀንሱ መድሐኒት በምንወስድበት ጊዜ።
/ከእርድ የሚዘጋጁ ተጨማሪ ምግቦች የጨጓራ አሲድ የሚቀንሱ መድሐኒቶቹን ሥራ ያረክሳሉ።/
፨ የስኳር ህመም መድሐኒት በሚወሰድበት ጊዜ።
/እርድ በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን የሚቀንሱ መድሐኒቶችን ከሚፈለገው በላይ ይጨምራል፤ ይህም አስጊና እጅጉን ያነስ የስኳር መጠን በደማችን እንዲኖር ያደርጋል፣ ይህም በሰውነታችን፦ የማላብ ስሜት፣ መንቀጥቀጥ፣ የእይታ ብዥታ፣ ራስ ማዞር፣ ጭንቀት፣ ግራ መጋባት፣እንዲሁም የልብ ምት መጨመር የመሳሰሉ ስሜቶች እንዲሰሙን ይሆናል።/
፨ የሀሞት ጠጠር ላለባቸው ሰዎች ላይ።
/የሀሞት ከረጢት መኮማተርን ስለሚጨምር፣ የሀሞት ጠጠር ህመምን ይባብሳል።/
፨ ደም ማቅጠኛ መድሐኒትን የሚጠቀሙ ሰዎች።
/እርድ በተፈጥሮ የሚገኝ የደም ማቅጠኛ ሲሆን፣ የደም ማቅጠኛ መድሐኒትን የሚጠቀሙ ሰዎች ላይ የመድማት ዕድላቸውን ይጨምራል።/
♦️በመጨረሻም ተጨማሪ ምግቦችን መጠቀም ከመወሰንዎ በፊት ሀኪምዎን ያማክሩ።
ማጠቃለያ
ጤናማ እንጀት በምግብ፤ በጭንቀት እንዲሁም በሌሎች ምክኒያቶች አማካኝነት ድንገት የሚከሰቱ የእንጀት መቆጣትን ለመቀነስ እጅግ ጠቃሚ ነው። እርድ በውስጡ ከሚገኘው Curcumin ከሚባለው ገቢር ይዘቱ የተነሳ ለምግብ ማጣፈጫ ቅመም ብቻ ሳይሆን፣ የአንጀት ጤናን ከመጠበቅ ጀምሮ በርካታ ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ገፀ-በረከቶችን ይዟል።
በእርድ ውስጥ የሚገኘው Curcumin እና በቁንዶ በርበሬ ውስጥ የሚገኘው Piperine ከያዙዋቸው ፀረ-ብግነት፣ ፀረ-ኦክሲዳንት ባህሪያት እንዲሁም በሽታን የመከላከል አቅም የተነሳ ጤናን በማሻሻል ረገድ በአዎንታ ታይተዋል።
Crohn's & Colitis Ethiopia