Trust the process

Trust the process

N.D💫

እውነቱን ለመናገር adulthood really sucks።ምን ለማለት ነው በፊት ከግቢ ወደ ቤት ለእረፍት ሂዱ ሲባል በጣም ደስተኛ 😆😆እሆን ነበር። የሰፈር ሰው ዶክተር እንዴት ነሽ? በርቺ አንቺ ነሽ ወደፊት የምታክሚኝ ምንምን እያለ ሲኮሩብኝ ጓደኞቼ ደግሞ ታድለሽ የኛ ት/ት እኮ እንዲሁ ይሁን እንጂ ከተማሩስ አይቀር medicine ነው ሲሉኝ የሚሰማኝን superiority complex አሁንም ድረስ ሳስታውሰው ይገርመኛል።ሁኔታዎች ከመቼው እንደተለወጡ ባላቅም አሁን ላይ ግን ግራ እስኪገባኝ ድረስ እነሱ winners🏆🏆እኔ ደግሞ loser ከሚባሉት ደረጃ ተመድበናል።የሰፈር ሰው እስካሁን አልተመረቅሽም እንዴ? በሚል ሽሙጥ እየገላመጡኝ ገና ዞር ሳይሉ እንኳ "አይ ይሄኔ ከብዷት ወድቃ እንጂ ይሄ ሁሉ አመትማ አይሆንም፤ጉድ ነው ዘንድሮ ይላሉ።አይ ኮሮና ያላደረገን ነገር የለም ብዬ አልፈዋለሁ።

ሌላው ነገር ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር መግባባት እስኪከብደኝ ድረስ ነገሮች ተለውጠዋል።እነሱ ደሞዝተኛ እኔ ደግሞ ተማሪ ሆኜ ስለ ኑሮ ያለን አመለካከት ዶሮ ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ነው።እኔ ገና internship ሳልገባ በምትኖረኝ 6000 ስንት እቅድ እያወጣሁ ነው፤ጀለሶች ደግሞ በ 20,000 ብር እንዴት መኖር እንደከበዳቸው ያወራሉ(🤯🤯seriously 🤯🤯...እኔ እኮ የእናንተን ሁለት እጥፍ ነው ሁሉን ነገር የማደርገው። ሶስት አመት ሳይሆን ሰባት አመት ነው የምማረው።እንደእናንተ ሙሉ ቀን makeup እየተቀባሁ ሳይሆን ከ18 ሰአት በላይ እያጠናሁ ነው። still ወደ ፊት የሚከፈለኝ ደሞዝ ከእናንተ ግማሽ እንደሆነ እያወኩ እንኳን am trying my best)። እና ጓደኞቼ ስለ human hair ሲያወሩ እኔ ስለ human anatomy🧠🫀🫁 ሳወራ እነሱ ነጂብ ብለው ስለ ከተማው ሀብታም ሲያወሩ እኔ ደግሞ ስለ doctor najeeb ሳወራ ብቻ ሳንግባባ እንለያያለን።


ከሁሉም የሚከፋው ግን ሰሞኑን ያጋጠመኝ ነገር ነው። እና የሆነ ቀን ከቤት በቢጃማ ፀጉሬን አራት ቦታ ተሰርቼ ላጥ ላጥ እያልኩ አስፓልት ልሻገር ስል የሆነ የቤት መኪና🚗🚘 ክላክስ ያደርጋል። መቼም ለኔ አይሆንም በሚል ባጃጆቹ እስኪያልቁ ድረስ ቆሜ እያለ አሁንም ካላክስ ይደረጋል። ማን ነው ደሞ ብዬ ዞር ስል እጁን እያውለበለበ ነው። ዞር ብዬ ባይ ማንም የለም። "ይሄኔ ዲያስፖራ ይሆናል።የገጠር ኮረዳ መስዬው ሊያገባኝ ቢሆንስ ብዬ እየተሽኮረመምኩ😍☺😚 ወደ መኪናው ጠጋ አልኩ።የሆነ ቦታ የማውቀው መሰለኝ።አስታውስሺኝ ሲለኝ አይ አልኩት። ቤን እኮ ነኝ ሲለኝ አመዴ ነው ቡንን ያለው። ለብዙ ሰአታት ባለማመን አፍጥቼ እያየሁት ነበር።


አይ ቤን፤ ትክክለኛ ስሙ በላይነህ ነው።ሁኔታዎች አስቂኝ የሚሆኑት አለምክንያት አይደለም። ከበላይነህ ጋር አብረን የተማርነው 8-10 ነው። ከክፍላችን ካለው ተማሪ እንደ ቤን በጣም አስቀያሚ፥በጣም ደደብ፥በጣም ሞኝ በቃ "he was z worst in everthing🤮"። ለዛም ብለው ነው መሰለኝ ጓደኞቹ ሌላው ነገር ቢቀር እንኳ ስሙ ይመር በሚል ቤን ያሉት።እና ከቤን ጋር ለ 3 አመታት አብረን ስንቀመጥ ሁሉንም ነገር የሚሰራው ከኔ ነበር።እና በጣም ብዙ ጊዜ ልመክረው፥motivate ላደርገው ብሞክርም ግን ምንም ለውጥ ስላልነበረው 10 ላይ matric ወደቀ።በሰአቱ ለቤን ባዝንም እኔ ግን በማለፌ የአለምን ቁልፍ የጨበጥኩ መስሎኝ about my bright future ደቂቃ የማባክንበት ደቂቃ የለኝም ነበር።ከዛ ስለ ቤን አንድም ቀን ጠይቄም ፥ሰምቼም አስቤውም አላቅም ነበር፤ያው በዚች ደቂቃ ከሩቅ አይቼው እንጂ ነክቼው በማላቀው የቤን መኪና ውስጥ ተቀምጬ ቢሆንም

እኔ፦ዋው በጣም ተለውጠሀል😎።ሳይህ እኮ አንተ መሆንህም ለማወቅ ተቸግሬ ነበር።

ቤን፦ ya u're right. I changed

እኔ፦ አዎ እና ኑሮ እንዴት ነው?(እንግሊዝኛው ልክ ነው ወይስ ጆሮዬ ነው ብዬ ለማለፍ እየሞከርኩ)

ቤን ፦አአ u know ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ ነው። ofcourse thanking God ,okay። ስራ ብዙም አይደለም ግን ቢያንስ በ ወር 100,000 ይከፍሉኛል።እኔ ግን ልተወው እያሰብኩ ነው። imagine be 100,000 ብር ምን አይነት ኑሮ ልኖር እንደምችል።

አዎ ልክ ነህ ብዬ ሳልጨርስ ስልክ ተደወለለት። መቼም ይሄ የኔ ችግር ይሆናል እንጂ እንዴት በ 100,000 ብር ብቻ ሰው አንድ ወር ሙሉ ይኖራል? የሚለውን ሳላስብ ቀረሁ ብዬ ራሴን በጣም ወቀስኩት። ትዝ ሲለኝ የኔ የወደፊት ደሞዝ ከ 10,000 አይበልጥም።ታድያ እንዴት ልኖር ነው ብዬ ሳስብ ለካ "እርካታ" አለኝ። እርካታ እንደ bitcoin ,digital currency🌏🏛🚚 ሆኖ ስጠቀመው በሀሳቤ ታየኝ።

እኔ፦ሰላም ነው ባለሱቅ። እስኪ 1 ኪሎ ሽንኩርት ስጠኝ?

ባለሱቅ፦100 ብር ነው ዶክተር

እኔ፦እርካታን እንደመገበያያ መጠቀም ጀምረሃላ?

ባለሱቅ፦አዎ በሚገባ እንጂ። በጣም አዋጪ investment ነው።ወደፊት ለማበደር ራሱ እያሰብኩ ነው።

እኔ፦ዋው በጣም ደስ ይላል።እኔም በጣም ብዙ እርካታ ስላለኝ መበደር የሚፈልግ ካለ ወደ እኔ ላክልኝ።

ባለሱቅ፦እሺ doc

ከዛ ብዙ እርካታ ያጣ ሰው መጥቶ ሲገዛኝ፤ከዛ ሀብታም⛵✈⌚🌞 ስሆን ሲታየኝ፡ ቤን ከሀሳቤ መለሰኝ

ቤን፦ በቃ ብታይ በጣም ኑሮ እየከበደኝ ነው።modelling እንደምታስቢው ቀላል ነገር አይደለም።ጠዋት 4:00 ላይ ለ photo shoot መነሳት ከባድ ነው።ከዛ everyday ምትበይው ምግብ plan ተደርጎ ነው፤ጂም መስራት ፤ሴቶቹ ደግሞ ከምልሽ በላይ ቆንጆ🤡🤡 ስለሆኑ የትዋን እንደምመርጥ በጣም ግራ ይገባል። ለቢዝነስ ተብሎ party መውጣት... ብቻ አስጠልቶኛል።

እኔ፦ አዎ ይገባኛል።stressed ሆነሀል።(መቼም ጌታዬ ሆይ በዙፋንህ እንዳለህ አንዲትም ቀን ተጠራጥሬ አላውቅም። ግን እኔ ወደፊት እንዲኖረኝ የምመኘው ኑሮ እየኖረ መሮኛል ሲል ለምን ፍርድህን አትሰጥም።ከሱ ወስደህ ወደ እኔ ፤በጣም ቀላል እኮ ነው)

ቤን፦ ሳይሽ ግን አንቺ ትሆኛለሽ ብዬ በፍፁም አልጠብኩም ነበር።

እኔ፦እንዴት ማለት?አልገባኝም☹🧐😳።

ቤን፦ድሮ ጎበዝ ተማሪ ነበርሽ እስከማስታውሰው ድረስ። ዩኒቨርሲቲ 👩‍🎓🧑‍🎓የምትገቢ መስሎኝ ነበር።አሁን ግን እንደዚ በቢጃማ ተዝረክርከሽ፣ ወልደሽ እና ኑሮ አጎሳቁሎሽ ሳይሽ በጣም ነው ያዘንኩት። ቢያንስ ደህና ኑሮ ያለው ሰው አታገቢም እንዴ?...ይሄኔ አንድ 4 ልጅ አስፈልፍሎሻል።

🔥🔥Boom emotional damage🔥🔥🤯 

እኔ፦አይደለም እኮ ቤን። ዩኒቨርሲቲ ገብቻለሁ።ግን.....

ቤን፦ በቃ ተይው ማስረዳት አይጠብቅብሽም።ገብቶኛል ይሄኔ ከአንዱ ወጠጤ ፍቅር ይዞሽ ወይም ከአንዱ lecturer ለውጤት ብለሽ አርግዘሽ ነው።I am busy ለነገሩ። ስላንቺ ህይወት የሚያገባኝ ነገር የለም። ሰዎች እንዳንቺ ካለች ሴት ጋር ካዩኝ ያለኝ image ይበላሽብኛል።ይቺን የ 10,000 ብር check ያዣት።ለልጆችሽ አንዳንድ ነገር መግዣ ይሆንሻል ብሎ እየገፋኝ በሚባል መልኩ ከመኪናው አስወርዶኝ ጥሎኝ ሄደ።


😰😥😭ጌታ ሆይ ህልም ነው በለኝ። አሁን እንደዚህ ከላይ እስከታች ሰድቦኝ የሄደው ያ ነፈዝ በላይነህ ነው እንዳትለኝ ብቻ። ለነገሩ ይበለኝ እኔ ነኝ ጥፋተኛ። brand ልብስ ይመስል በፒጃማ ስንከላወስ እሱ ምን ያድርግ። እውነቱን ለመናገር በዚ ሰአት ላይ እንደበላይነህ ሀብታም ግን እውቀት አልባ ከምትሆኚና ድሀ ግን ባለብዙ እውቀት ብባል እንደ ቤን መሆንን እመርጣለሁ።ህሊና እና እርካታ ከገንዘብ በላይ ነው እንደሚሉት ሰዎች አይደለሁም።ነገር ግን ለወረቀት ብዬ ህሊናዬን ማጣት አልፈልግም(😃😀ችግሮቼ ሲስቁብኝ ይሰማኛል)። ከዚህ በሃላ የምመኘው ነገር ቢኖር የሆነ ቀን ሀኪም ሆኜ ቤን እንዲመጣ እና እንዲያየኝ ነው። እናቴን አለቀውም አኮላሸዋለሁ(just kidding)


ሁኔታዎች ተለዋውጠው እስከምናይ ድረስ ድህነታችንን እያስታመምን ለእውቀት እንተጋለን።TRUST THE PROCESS😇🤓🙈🙉🙊



N.D💫

C2 Gondar

Report Page