#TikvahFamily
Tikvah-Ethiopiaየመቐለ ዓይደር ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ድጋፍ :
በትግራይ ጦርነት ከምዕራባዊ ዞን ተፈናቅለው መቐለ ለሚገኙ ዜጎች የመቐለ ዓይደር ክፍለ ከተማ ቀጠና 7 ነዋሪዎች 40 ሺህ ብር የሚደርስ ድጋፍ አደረጉ።
ተፈናቃዮቹ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ህፃናት፣ ሽማግሌዎች፣ በከባድ መሳሪያ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆኑ በክፍለ ከተማው ፖሊስ ኮሚኒቲ ተጠልለው ነው የሚገኙት።
በዓይደር ክ/ከተማ ነዋሪዎች የተደረገው ድጋፍ ነዋሪው በራሱ በመነሳሳት ጤፍ፣ ሽሮ፣ ዘይት፣ በርበሬ፣ ፣ሳሙና፣ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ፣ ሽንኩርት ፣ ቲማቲም ድንች የምግብ፣ የዓልባሳት ሌሎችም ጠቃሚ ቁሳቁሶች፣ ለአንዳንድ ነገር እንዲሆናቸው ደግሞ ነዋሪው ገንዘብ አውጥቶ በማሰባሰብ ነው ድጋፍ ያደረገው።
የዓይደር ክ/ከተማ ነዋሪዎች ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አርዓያነታቸውን በመከተል ሁሉም የመቐለ ነዋሪ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
በቀጠና 6 ፖሊስ ኮሚኒቲ ከ120 በላይ ዜጎች በሁለት ክፍል ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ሁኔታው በጣም ከባድ እንደሆነ በማንሳት ዘላቂነት ያለው ት/ቤት ወይም ሌላ ቦታ እንዲያርፉ ሊደረግ እንደሚገባ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ነፍሰጡሮች ችግር ላይ ይገኛሉ፤ ለተለያዩ በሽታዎችም እየተጋለጡ በመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ተብሏል።
ተፈናቃዮቹ የመቐለ ህዝብ እያደረገላቸው ላለው ያልተቋረጠ ሁለንተናው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ድጋፍ ማስረከቡ :
ሰሞኑን ቅዱድ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ከ50.000 በላይ ደብተሮችና ሌሎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ወደ መቐለ መላኩ ይታወሳል።
ትላንት የስፖርት ማህበሩ ተወካዮች ቡድን በከተማው በመገኘት ስጦታዎቹን ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ አስረክበዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ማህበር በቀጣይ ቀናት ወደ ማይካድራ እና መተከል ተመሳሳይ ድጋፎችን እንደሚልክ አሳውቋል።
የትግራይ ከተሞች የነበረው ተቃውሞ እና አድማ ማብቃቱ ፦
በትግራይ ክልል ግፍ እየተፈፀመ ፣ የሃይማኖት መሪዎች እየተገደሉ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉዳት እየደረሰባቸው ባለበት ወቅት የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ድርጊቱን ሳያወግዙ ወደ ትግራይ ክልል መምጣታቸው ትክክል አይደለም በሚል ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ/አድማ አብቅቷል።
በትግራይ ክልል ከማክሰኞ ጀምሮ ተቃውሞ ሲካሄድ ነበር።
ተቃውሞው በመቐለ ጀምሮ ውቅሮ ፣ ፍረወይኒ፣ እዳጋሃሙስ ፣ ዓዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም ፣ ሽረ እንደስላሰ ከተማ ተስፋፍቶ ነበር።
በመቐለ መደበኛ እንቅስቃሴ የጀመረው ከአርብ ጀምሮ ነው።
ተቃውሞ ሲደረግባቸው የነበሩት በሌሎች ከተሞች ከትላንት ጀምሮ ወደ መደበኛው እንቅስቃሴ መግባታቸው ተሰምቷል።
የንግድ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት ጀምረዋል ፤ የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ወደመደበኛው ሁኔታ ተመልሷል።
EU ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች “ጥሩ ሥራ” እየሰሩ መሆኑን መግለፁ :
የአውሮፓ ሕብረት መልዕክተኛና የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፔካ ሃቪስቶ ዓለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ክልል “ጥሩ ሥራ” እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
የሕብረቱ መልዕክተኛ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፣ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከሌሎች ሚኒስትሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ፔካ ሃቪስቶ የውይይቱ ዋና ትኩረት በትግራይ ክልል እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ከነገ የካቲት 8 ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ መባሉ :
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉ ተገልጿል።
እነደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ለመማር ማስተማር አመቺ በሆኑ የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ከነገ የካቲት 8 ጀምሮ ትምህርት እንዲጀመር መወሰኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ኢንጂነር ኣስቴር ይትባረክ ዛሬ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ አሳውቀዋል።
ኢ/ር ኣስቴር ፥ ወላጆች ልጆቻቸው ሳይማሩ በመቆየታቸው ፣ ትምህርት ቤት ተዘግቶ በመቆየቱ ለተፈጠረው የስነልቦና ጫና በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ከነገ የካቲት 8 ጀምሮ አመቺ በሆኑ ቦታዎች ትምህርት ለማስጀመር የሚያስችሉ ዝርዝር ሁኔታዎች መታየታቸው፣ የአስተማሪዎች እንዲሁም የወላጆች አስተያየት መሰማቱ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ንግግር መደረጉን ኢ/ር አስቴር በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።
ነገ በክልሉ በሚጀምረው ትምህርት አንዳንዶቹ ሙሉ በሙሉ ሲጀምሩ ለመክፈት አመቺ ባልሆነባቸው ቦታዎች ደግሞ ቀስ ተብሎ እንደሚከፈት ተገልጿል።
አሁንም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ቀሪ መሟላት የሚገባቸውን ጉዳዮች ለማሟላት እየተሰራ መሆኑን ትምህርት ቢሮው አሳውቋል።
[የመቐለ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የዓይደር ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ፣ የትግራይ ቴቪ ፣ ጋዜጠኛ ሙልጌታ አፅብሃ (መቐለ-ቪኦኤ) ፣ አል ዓይን ኒውስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ]
Compiled By : Tikvah-Ethiopia
@tikvahethiopia