TikvahEthiopia

TikvahEthiopia



"መስሪያ ቤቱ መድኃኒት ለመግዛት ገንዘብ እያጠረው ነው" -የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት


የአይደር ኮምፕረንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ካጋጠመው የመድኃኒት እና የህክምና ግብዓቶች እጥረት ጋር በተያያዘ በሆስፒታሉ እና በታካሚዎች ዘንድ በርካታ ችግሮችን እያስከተለ የሚገኝ ሲሆን ተቋሙ ባሉበት ተደራራቢ እዳዎች ምክንያት ችግሩን መቅረፍ ተስኖታል።


ሆስፒታሉ ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር ባለበት ከፍተኛ ያልተከፈለ እዳ ምክንያት ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።


በተቋሙ አጋጥሟል ለተባለ የመድኃኒቶች እጥረት ምክንያትም ያለው ውስን በጀት እና ያለበት ውዝፍ ተጠቃሽ ናቸው።


ካሉበት ችግሮች በተጨማሪ አንዳንድ መድኃኒቶች በመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩልም እያጡ መሆኑን ሆስፒታሉ ለቲክቫህ አሳውቋል። 


ሆስፒታሉ ላቀረበው ቅሬታ እና ስላልተከፈለው ከፍተኛ እዳ የአገልግሎቱን የመቀሌ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ገብረማርያምን አነጋግረናል።


ምን ምላሽ ሰጡ?


ማንኛውም የጤና ተቋም በሚዋዋለው ውል መሰረት በዱቤ መድኃኒት እንደሚቀርብለት የተናገሩት አስተባባሪው በውሉ መሰረትም በ 30 ቀን መከፈል እንዳለበት አስረድተዋል።


ይሁን እንጂ አይደር ይህንን ውል ሳይፈጽም በ 2016 በጤና ሚኒስቴር ከተሸፈነለት የተወሰነ ክፍያ እና እራሱም ከከፈለው አምስት ሚሊየን ብር ውጪ ያልከፈለው 40 ሚሊየን ብር ያልተከፈለ የመድኃኒት እዳ ወደ 2017 በጀት ዓመት እንደተላለፈበት ተናግረዋል።


"ይህ እዳ እያለባቸውም ቢሆን ህዝብ እንዳይጎዳ በሚል መድኃኒቶችን በብድር እንዲወስዱ አልከለከልንም ለ 2017 የዱቤ ሽያጭ ውል ተዋውለናል " ብለዋል።


ነገር ግን የሰጠናቸው ማሳሰቢያ አሁን ከወሰዳችሁ ሳትከፍሉ ደግማችሁ መጠየቅ አትችሉም የሚል መሆኑን ነግረውናል።


መስሪያ ቤቱ መድኃኒት ለመግዛት ገንዘብ እያጠረው ነው ያሉ ሲሆን መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በብድር የሚያቀርባቸውን መድኃኒቶች ክፍያ ባለመፈጸም ትግራይ ክልል ቀዳሚ መሆኑን ተናግረዋል።


"በያዝነው በጀት ዓመት ከሃምሌ ወር ጀምሮ ብቻ 13 ሚሊየን ብር የሚገመት መድኃኒት በብድር ለአይደር ሰጥተናቸዋል ከዚህ ውስጥ 5 ሚሊየን ብር ከፍለውናል የተቀረው አልተከፈለም " ነው ያሉት።


በዚህ ምክንያት ይህን ሳይከፍሉ መድኃኒት እንደማይሰጣቸው ለሆስፒታሉ አሳውቀናል ብለዋል።


ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ነገር ግን የለም አሁንም የተወሰኑ ወሳኝ ወሳኝ የሆኑ መድኃኒቶችን በብድር እንሰጣለን ነገር ግን በበፊቱ አሰራር መቀጠል አንችልም ሲሉ አክለዋል።


የእኛ ጥያቄ በበጀታቸው መሰረት ይውሰዱ እንጂ ከበጀታቸው በላይ መውሰድ አትችሉም የሚል ነው ከዛ በላይ ከወሰዱ ከየት አምጥተው ይከፍሉታል? ሲሉ ጠይቀዋል


የፕሮግራም ወይም የነጻ የሚባሉ የተለያዩ መድኃኒቶች አሉ እነዚህ የሚመጡ ከሆነ ለአይደር አንከለክልም ትልቅ ሆስፒታል ስለሆነ በቅድሚያ ነው የምንሰጠው ብለዋል።


በተወሰኑ መድሃኒቶች እና የህክምና ግብዓቶች ላይም አጋጥሟል ስለተባለው እጥረትም "ማደንዘዣ እና ለመስፋት የሚያገለግሉ ሱቸሮች(Sutures) በተወሰነ ደረጃ እጥረቶች አሉ ነገር ግን እየገቡ ያሉ አሉ ከተራገፈ እናያለን ከመጣ መስጠት እንችላለን አንከለክልም" ብለዋል።


የስነ ልቦና መድኃኒቶችን በሚመለከትም "በሁሉም አይነት የስነ ልቦና መድኃኒቶች እጥረት አለ ለማለት ይከብዳል በተወሰኑ መድኃኒቶች ክፍተቶች ይኖራሉ ተጠቃሚ ጨምሯል የሚለው ያስማማናል የእኛም አቅርቦት በዛው ልክ ጨምሯል" ብለዋል።


ለጦርነቱ በኋላ የስነ ልቦና መድኃኒቶች ተጠቃሚ መጨሩን ያነሱ ሲሆን አቅርቦቱም በተወሰነ መጠን የመጨመር ሁኔታ አለ ነው ያሉት።


የካንሰር መድኃኒቶችን በሚመለከትም በተቋማችን እጥረት የለም ነገር ግን ሆስፒታሉ አንወስድም ብለው ነው የተውት የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።


ይህንን ስንል ሁሉም ፍላጎት ተሟልቷል ማለታችን አይደለም ነገር ግን በአንጻራዊነት የተሻለ አቅርቦት አለ ክፍተቶች ሲኖሩም በጋራ ተነጋግረን ከሌላ ቦታ እንድናስመጣላቸው መጠየቅ ይችላሉ ብለዋል።


ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሆስፒታሉ በጀታቸው እንዲጨምር ማድረግ ወይም ደሞ ከጤና ጥበቃ እርዳታ እንዲደረግላቸው መጠየቅ አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል ።

@tikvahethiopia

Report Page