TikvahEthiopia

TikvahEthiopia


ረቡዕ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ/ም


ጋዜጠኛ መስገን ደሳለኝ ተከሰውበት የነበረው ክስና ሂቱ ምን ይመስል ነበር?


ጋዜጠኛው፣ በሐምሌ 2014 ዓ/ም፣ “ጥብቅ የመከላከያ ሠራዊትን ምስጢር ማባከን፤ መከላከያ ሠራዊቱን መከፋፈል፤ የመከላከያ ሠራዊቱን ስም ማጥፋት” የሚሉ ሦስት ክሶች ተመስርተውባቸው ነበር።


በዚህም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለስደስት ወራት በእስር ቆይተዋል።


ከዚያም በፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት የሕገ መንግሥት እና የሽብር ወንጀል ችሎት፣ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክሶች ‘ነጻ’ ብሎ ሦስተኛው ክስ ደግሞ አንቀጽ ተቀይሮ እንዲከላከል ውሳኔ በማሳለፉ በዋስ ተፈትተው ነበር።


ነገር ግን የፌደራል መንግሥት ዓቃቢ ህግ ጋዜጠኛ ተመስገን በሁለቱ ክሶች “ነጻ” መባላቸውን ተቃውሞ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብሏል።


ይህን ተከቶሎ ጋዜጠኛው በወቅቱ የነበሩትን ዳኞች "ትክክለኛ ፍርድ ይሰጡኛል ብዬ ስለማላምን ዳኛ ይቀየርልኝ” የሚል ጥያቄ ቢያቀርብም ጥያቄው ውድቅ ተደርጎበት ነበር።


በኋላ ላይም ሚያዚያ 2016 ዓ/ም በወቅቱ የነበሩት ሦስቱም ዳኞች ተቀይረዋል።


በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክሶችም ክርክር እየተደረገ፣ የክሶቹ ጉዳዮች ለአንድ አመት ከ5 ወራት በላይ እየታዩ ቆይተዋል።


በመጨረሻም፣ ሐምሌ 23 ቀን የዋለው ችሎት፣ “የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ትክክልና የሚነቀፍ ሆኖ ስላላገኘነው ጋዜጠኛው በነፃ እንዲሰናበት የተሰጠው ውሳኔ ጽንቷል” በሚል ጋዜጠኛው ነጻ ተብለዋል።


#TikvahEthiopiaFamilyAA


@tikvahethiopia

Report Page