Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


#ሲዳማ_ክልል 


" 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል " - የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ


በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በቦታ ጥበትና ሌሎች መሰል ችግሮች ሥራ ለማቆም እየተገደዱ መሆናቸውን ተደራጆቹ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣሉ። 


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሚነሱ ቅሬታዎች የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ምክችል ኃልፊ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደን ጠይቋል።


ምን አሉ ?


" በክልሉ 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል። ከዛ ውጭ ያሉት 48 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ሌሎች ወደ 52 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት የተሻለ ደረጃ ላይ ናቸው።" 


ኢንተርፕራይዞቹ የከሰሙበት ችግር ምን እንደሆነ፣ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ እንዲገልጹ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምክትል ኃላፊው ፦


- አንደኛ በሰብል የተደራጁት የተወሰኑ አካባቢዎች ከዝናብ እጥረት ጋር ተያይዞ ትንሽ ድርቅ ገጥሟቸው ነበር።


- ድርቅ የነበረባቸው አካቢዎች ፤ ከሀዋሳ ወጣ ብሎ ወደ 40 እና 30 ኪሎ ሜትር የሚገኙ እንደነ ሎካባያ፣ ብላቴ የሚባሉ አካባቢዎች አሉ። ወደ ዲላ አካባቢ ዳራ ከባዶና ኦቲሊቾ፣ ተፈሪ ኬላ የሚባሉ አካባቢዎች አሉ። ሌላው ደግሞ ወደ በሳ መሄጃ ቦና የሚባል አካባቢ አለ፤ እነኝህ አካባቢዎች ላይ ትንሽ የድርቅ ችግር ስለነበረ ለሰብል የተባሉ ኢተርፕራይዞች ያመረቱት ምርት ስለተበላሸ እዛው የከሰሙ እንዳሉ አረጋግጠናል።


- ከድርቁ በተጨማሪ የጸጥታ ችግር ለመክሰማቸው ምክንያት ነው። በተለይ አጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች ያሉበት አካባቢ በተወሰኑ ደረጃዎችም ቢሆን የፀጥታ ችግሮች በመኖራቸው የከሰሙ እዳሉ አይተናል።


- የከሰሙ እዲያሰራሩ ለማድረግ እንዲሁም " መስመር " የሚባል ፕሮጀክት ወደመክሰም እየሄዱ ያሉትን እተርፕራይዞች እንዳይከስሙ ለማድረግ 483 አካባቢ የሚሆኑ ኢተርፕራይዞችን ድጋፍ ሊያደርግ ቃል ገብቶ የተበታተኑትን ጭምር እደገና እዲያንሰራሩ የማድረጉን ሰራ እየሰራን ነው።


- ወደ ከተማ ያሉት ደግሞ በገበያ ማጣት፣ በማኅበር እስከ 30 ድረስ የሚደራጁት ኢንተርፕራይዞች እርስ በእርሳቸው ካለለመስማማት ጋር ተያይዞ የተበታተኑ እዳሉ አይተናል። 


- ወደ ስምንት በመቶ አካባቢ የሚሆኑት በራሳቸው ምክንያት ብቻ የተበታተኑ አሉ። በምን ምክንያት እደተበታተኑ ጥናት ስናደርግ መጀመሪያ ሲገቡ በቂ ስልጠና አግኝተው ካለመግባታቸው ስለሆነ ነው።


- የእኛ ባለሙያዎች በተለይ በማእከል ላይ ያሉ ባለሙያዎች በቂ ድጋፍ ባለማድረጋቸው የከሰሙ እዳሉም አይተናል። ወደ ገጠር ያሉት ደግሞ ገጠር ላይ የክላስተር ባለሙያዎች ናቸው ያሉትና እነዚህ የክላስተር ባለሙያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉላቸው ካለመሆኑ የተበታተኑ እዳሉ አይተናል።


አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በመሬት ጥበት ሥራ ለማቋረጥ እንደሚገደዱ ይገልፃሉ። 


ሲዳማ ክልልም አዲስ ክልል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙ ቅሬታዎች ሲነሱ ይደመጣልና በመሬት ጥበት ምክንያት ያለው ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቢሮው ጥያቄ አቅቧል።


አቶ ከፍያለው ፦


* አንደኛ ክልሉ ካሽ ክሮፕ የሆነ ክልል ነው። ሁለተኛ ደግሞ የመሬት ጥበት ያለበትንና ደንስሊ ፖፕሌትድ የሆነ ክልል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ችግሩ እንዳለ ይታወቃል።


* ይህን ችግር ለመቅረፍ በተለይ በይርጋአልምና በሀዋሳ በኢተርፕራይዞችና በግለሰቦች፣ በባለሀብቶች እዲሁም በሌሎች ከተሞች ህገወጥ የተያዙ ኮቲነሮችን ለይተው ህጋዊ የማድረግ፣ ቀድመው የነበሩችን ኢተርፕራይዞች ወደ ሌላ ዘርፍ በማሸጋገር ለአዳድሶቹ የመስጠቱን ሥራ እየተሰራ ነው።


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ስለ ቦታ ችግር ምን ይላል ?


ከሳምንታት በፊህ በነበረ አንድ መድረክ በክልሎች የሚስተዋውን የመሥሪያ ቦታ ችግርን በተመለከተ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።


ወ/ሮ ሙፈሪያት ፤ " የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ጋ በተያያዘ ከልማት ባንክ ጋ የጀመርነው ሥራ አለ " ብለዋል።


"የዝግጅት ምዕራፉ ትንሽ ጊዜ ወስዶብናል፣ እሱን የማጠናቀቅ ሥራ ተሰርቷል፣ ቀጥሎ በየክልሎቹ ወደ ትግበራ ነው የምንገባው" ያሉ ሲሆን " 80 በመቶ ባንኩ፣ 20 በመቶ ክልሎቹ ሸፍነው ደረጃውን የጠበቀ የማምረቻ ስፍራ እንዲኖር የማድረግ ሥራ እየሰራን ነው" ሲሉ አስረድተዋል።


መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

Report Page