Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


#Ethiopia


በ “ብሩህ ንግድ ፈጠራ ሀሳብ ” ውድድር ከተመዘገቡ 1,375 ተሳታፊዎች መካከል 150 አሸናፊዎች 2 ሺህ ዶላር ለሚያሸልመው ለመጨረሻው ዙር ውድድር መለየታቸው ተነግሯል።


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሥሩ ካሉ ተቋማት ጋር በመተባበር “ ማሰልጠን፣ መሸለምና ማብቃት” በሚል መሪ ቃል “ብሩህ ሀገር አቀፍ ዓመታዊ የንግድ ፈጠራ ሀሳብ ውድድር” አማካኝነት አዳዲስ ቴክኖሎጅ የሚያመነጩና የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች ያወዳድራል፡፡


አሸናፊዎቹን በማሰልጠንና በመሸለም፣ በመጨረሻም የፈጠራ ሃሳባቸው በተጨባጭ ወደ ምርት እንዲሸጋገር እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡


በዚሁ መሠረት ውድድሩ እንደ ከዚህ ቀደሙ በ2016 በጀት ዓመትም በየወረዳው 1,375 ተወዳዳሪዎች እንደተመዘገቡ፣ ከእነዚህ መካከል 150 የሚሆኑት ብቁ ሆነው እንደተለዩ የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴዔታ አቶ ሰለሞን ተካ ገልጸዋል፡፡


ለውድድር ከቀረቡት ከእነዚህም ውስጥ 242 ከተለያዩ ክልለሎች፣ 119 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መለየታቸውን ነው ያስረዱት፡፡


ከእነዚህ ተወዳዳሪዎች ውስጥም የሥራ ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው የኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት በተሰጠው የሳይኮሜትሪክ ቅድመ ልየታ ቃለመጠይቅ 150 ተወዳዳሪዎች ለመጨረሻው ዙር ውድድር መለየቱ ተነግሯል፡፡


እነዚህ 150 ተወዳዳሪዎች መካከል በአንድ ማዕከል ሆነው በቀጣዮቹ ቀናት ስልጠና እንደሚወስዱ፣ ከ150ዎቹ ተወዳዳሪዎች መከካል በፈጠራ ሃሳባቸው ለሚያሸንፉ 50 ተወዳዳሪዎች እያንዳንዳቸው 2 ሺሕ ዶላር እንደሚሸለሙ ተመላክቷል፡፡


ከሽልማቱ ባሻገር የኢንኩቤሽንና አክስለሬሽን ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ፣ ከልማት ባንክና ከሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር በሚፈጠርላቸው ትስስር የፈጠራ ሥራቸው ወደ ምርት እንዲገባ ክትትል የሚደረግ መሆኑም ተገልጿል፡፡


ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ ቁጥሩ ምነው ትንሽ ሆነ? በርካታ ሥራ አጥ ወጣቶችን የእድሉ ተጠቃሚ ለማድረግ የተወዳዳሪዎችን ቁጥር ለምን ከዚህ መጨመር አልተቻለም? ሲል የኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩን ጠይቋል።


የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሰን ሁሴን (ዶ/ር)፣ በትክክል አንሷል፡፡ የአቅም ጉዳይ ነው ውስን ያደረገን፡፡ የበጀት ጉዳይ ነው፡፡ ከዓመት ዓመት እየጨመርን ነው ግን በቂ ነው ብዬ አላስብም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡


“በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ናቸው መሳተፍ ያለባቸው፡፡ ይህን ሥራ እያስፋፋን ነው፡፡ ድሮ በሳምንት ሦስት የሰልጠና መርሃ ግብር የነበረን አሁን በአንድ ሳምንት እስከ 67 የደረስንብት ሁኔታ ነው ያለው” ብለዋል፡፡


መርሃ ግብሩ አሁን ለ4ኛ ጊዜ እየተካሄደ እንደመሆኑ መጠን ባለፉት ሦስት ዓመታት ውድድሩን ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ዛሬ ምን ደረጃ ላይ ናቸው? ቁጥራቸውስ ምን ያህል ነው? ለሚለው የጢክቫህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽም፤ “ሦስት ጊዜ ወደ 150 የሚሆኑ አልፈዋል፡፡ ሰመርካምፕ ውስጥ የገቡት ወደ 380 የሚደርሱ ወጣቶች ናቸው” ነው ያሉት፡፡


“ማምረት፤ መሸጥ፤ ድርክት ማቋቋም ጀምረዋል፡፡ ሌሎች አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ማሸነፍ የቻሉ አሉ፡፡ ምርቶቻውን ገበያ ውስጥ የምናገኛቸው አሉ” ሲሉ አክዋል፡፡


#TikvahEthiopiaFamilyAA


@tikvahethiopia

Report Page