Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል ሙለ ገለጻ፦

“ኮሚዩኒኬሽኑ ላይ ያልነው ቃል በቃል እደዛ ባይሆንም እንደዛ እንደሚሉ እኛም እናውቃለን፡፡ በሰዓቱም በነበረን ስምሪት የሰጠነው መረጃ ማንም ሰው ሰልጥኖ ብቁ ሆኖ በፍቅር አገሩን አገልግሎ እስከተገኘ ጊዜ ድረስ ተመራጭ ነው የሚሆነው የሚል ነው፡፡ 

በትክክልም ነው ደግሞ፡፡ ከነበረው አንድ ነገር ጨምሯል፡፡ እነዚህ ልጆች በጣም ነው የማደንቀው በግሌ ለልቤም በጣም በጣም ቅርብ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ 

የማያውቁት አካባቢ፣ በማያውቁት ቋንቋ ባለበት ደፍረው ሂደው ሀገር፣ ህዝብ ፍለጋ ተሰማርተው ኃላፊነታውን የተወጡ ዜጎች ናቸው፡፡ 

ስለዚህ ሲመለሱ ስርዓቱን የሚያተጋ የሚያበረታታ ሁኔታ መፍጠር ተገቢ ነው፡፡ ይህንኑ ከግምት ውስጥ አስገብተን እየሰራን ነው የቆየነው፡፡ ያው የምንጠብቀው ነገር ሲኖር ቶሎ እንዲያልቅ ስለሚፈለግ ነው እንጂ።

የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ባለፉት 2 ዓመታት ስንሰራ የቆየነው አብዛኛው መካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ነው። እነዚህ ልጆች የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ምሩቃን ናቸው፡፡ 

በአብዛኛው የሥራ ባህሪ የቤት ውስጥ ሥራ ባህሪ ነው የነበረው፡፡ ጎን ለጎን ሲሰራ የነበረው በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል መላክን ይጨምራል። ስለዚህ 98 በመቶ ሴቶችን ነው የላክነው፡፡ 2 በመቶ ገደማ ወንዶች ናቸው የሄዱት። ወደ መካካለኛው ምሥራቅ፡፡ 

ከመካከለኛ ምሥራቅ አገራትም ያለን አዲሱ ስምምነት የሰለጠነና በከፊል የሰለጠ የሰው ኃይል መላክን የሚያስችል ነው፡፡ ድሮ እንደነበረው አይደለም ማለት ነው።

ስለዚህ የገበያ መዳረሻ እያሰፋን ነው ያለነው፡፡ ሰው ስለተመዘገበ ብቻ ይሄዳል ማለት አይደለም፡፡ ለጉዳዩ ተፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት ያስፈልጋል፡፡ 

ለምስሌ የሰለጠነ የሰው ኃይል እንልካለን ስንስል ሀገራቱ በሚፈልጓቸው የሙያ መስኮች የሚላኩ ወጣቶች ሰርቲፋይ የሚያደርጓቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መኖር አለባቸው፡፡ 

ዘንድሮ ይህንን ከሚመለከታቸው ጋር ሆነን ማሳካት ችለናል፡፡ ስለዚህ አንዳንዶቹ የሙያ መስኮች ላይ በዬጊዜው ይፋ እያደረግን ነው ያለው። ሰሞኑን ይፋ ያደረግነውን የሱዊድንና የኖርዌይ ገበያ ጭምሮ ይፋ አድረገናልል፡፡ በርካታ የሙያ መስኮች ላይ የሰለጠኑ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ 

የተመዘገቡ ሰዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው በደብን (ኦንላይን የምናዘጋጃቸውን ይዞቶች አሉ፡፡ ተመዝግበው ደግሞ ዓቀፍ ስታንዳርዶች አሉ መውሰድ ያለባቸው የሥልጠና የፈተና አይነት) ይሄን ያሟላ ሰው መሄድ ይችላል፡፡  

ስርዓት አልምተናል፡፡ ስርዓቱ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ማስተናገድ የሚችል ነው፡፡ በቴክኖሎጅ የታገዘ ነው፡፡ የሰው ጣልቃ ገብነት የለውም፡፡ የአክስቴ የአጎቴ የሚባል ነገር የለም ማለት ነው፡፡ ሪኳየርመንት ያሟላ በሙሉ ይህንን እድል ማግኘት ይችላል፡፡ 

ከዚህ ውስጥ አንዱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ናቸው ማለት ነው፡፡ 2014 ዓ/ም ላይ 40 ሺሕ ገደማ ሰው ነው የተላከው ቅድም ባልኩት ቀመር፡፡ 

የሥራው ባህሪ የሚጋብዝ አልነበረም፣ ምሩቃን ለሆኑ ሴትና ወንድ ወጣቶች፡፡ ቢያንስ እስከ 8ኛ ክፍል የተማሩ ሴት ወጣቶችን በአመዛኙ የሚጋብ ነው የነበረው፡፡ 

2015 ዓ/ም ወደ 127 ሺሕ ገደማ ዜጎችን ነው የላክነው፡፡ ይሄ በቴክኖሎጅ የታገዘ ነበር፡፡ 2016 ዓ/ም 345 ሺሕ ዜጎችን ልከናል፡፡ ይሄን ትርጉሙን በደንብ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Report Page