Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


የኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ ምን አሉ ?

" የማይጠበቅ ነው ብዬ መናገር አልችልም።

ብዙ ማሻሻያዎች እየተደረጉ መጥተው ነበር ፤ ተጨማሪ ብድር ለማግኘትም ከIMF እና WB የነበረው ድርድር መጨረሻ የተጠየቀው ድርድሩ እንዲሳካ floating ማድረግ ወይም ደግሞ devaluate ማድረግ ነበር። የ10 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍም እንደሚጠበቅ ተነግሮ ነበር ይሄ ሊሆን የሚችለው የIMF ፍላጎት ሲሟላ ብቻ ነው። ብዙ ነገሮችን ስናይ የአሁኑ ውሳኔ ሊሆን አይችልም ብሎ ማሰብ አይቻልም።

በእርግጥ አሁን የተደረገው devaluate /ገንዘብ ማዳከም/ አይደለም። devaluation ማድረግ እና floating ይለያያል።


devaluate ማድረግ ምን ማለት ነው ? floating ማለትስ ?

devaluate የገንዘቡን የመግዛት አቅም በተወሰነ መልኩ በመንግስት ውሳኔ ማዳከም ማለት ነው። አሁን ግን እንደዛ አይደለም የተደረገው።

አሁን የተደረገው በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት / floating / ነው።

የውጭ ምንዛሪ ተመን በ3 መልኩ ይመራል።

1. fixed exchange rate / 👉 በመንግስት ውሳኔ / መንግስት አንድ ዶላር በዚህ ያህል ብር ነው የሚወሰነው ብሎ ድርቅ ሲያደርግ በዛ ብር ብቻ ነው የሚወሰነው ሲል።

2. floating managing 👉 ኢትዮጵያ እስከ ዛሬ ስትመራበት የነበረው ነው። በመንግስት ውሳኔ አለው ግን በየቀኑ መንሸራተት ያለው ነው። በየቀኑ የሚምሸራተት ነው። በምዛሬው ላይ በየዕለቱ ለውጥ የሚታይበት ነው። መንግስት መነሻውን እያስቀመጠ ገበያው እየወሰነ ሲቆይ ነው።

3. floating 👉 በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር ሲመራ ነው።

ለምሳሌ ፦ ጥቁር ገበያውን እንመልከት አንድ ዶላር በስንት ብር ነው የሚመነዘረው የሚለውን ጥዋት ነው የምንሰማው፤ ጥዋት ገበያው ወስኖ ይጠብቃል። ብዙ ዶላር ከመጣ / ብዙ ሰዎች ዶላር ይዘው ከመጡ የሚመነዘርበት ብር ረከስ ይላል ዶላር እጥረት ካለ ከፍ ይላል። ይህ ማለት ነው በፍላጎት እና አቅርቦት መመራት ማለት።

አሁን መንግስት የወሰነው በገበያው ላይ ባለው ፍላጎት እና አቅርቦት ገንዘብ ከዶላር አንጻር እንዲመራ ነው (floating exchange rate)።

ብዙ floating እያደረጉ የሚመሩ ሀገራት አሉ ያደጉ ሀገራትን ጭምር።


floating የሚመራው እንዴት ነው ?

ብሔራዊ ባንክ 1 ዶላር በዚህ ብር ይመንዘር ማለት አይችልም። ለኢትዮጵያ ብር ያላቸው ፍላጎት ኢትዮጵያ ለውጭ ምንዛሬ ያላት ፍላጎት ዓለም አቀፍ ገበያው ላይ ያለው እንቅስቃሴ ከግምት ይገባል።

ገበያው የዕለቱን ፍላጎት ይወስናል። በዕለቱ ዶላር በጣም ከተፈለገ ከፍ ይላል። ካልተፈለገ ዝቅ ይላል።

ሌሎች ሀገራት ያለው የወለድ ተመንም ተፅእኖ ይፈጥራል። አንዳንደች ሀገራቸው ላይ ጥሩ ወለድ ካለ ገንዘባቸውን ያስቀምጣሉ ደከም ሲል ወደ ሌላ ሀገር ወስደው ያስቀምጣሉ።

ሌሎች ሀገራይ ያለው የዋጋ ንረትም ተጽኖ ይፈጥራል። ዋጋ ንረት ኖሮ ገንዘብ ከተዳከመ እዚህ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍ እና ዝቅ ማለቱ የማይቀር ነው።

አሁን በfloating መምራት ውስጥ ኢትዮጵያ ገብታበታለች።

floating ከማድረጉ በፊት የሚጠየቁ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ ዋናው በቂ reserve ማድረግ ያስፈልጋል።

floating ለገበያ በጣም መጥፎ ላይሆን ይችላል ግን በቂ የዶላር reserve ኢኮኖሚው መያዝ አለበት።

floating በተጀመረ በጀንበር ውስጥ ገበያው ብዙ ሊለዋወጥ ይችላል። ፍላጎት ካለ ዶላር አሁን ካለው በእጥፍ ሆኖ ሊያድር ይችላል።

ይህ ደግሞ ገበያውን ያናጋዋል። ስለዚህ ይሄን የሚያመጣጥን ብቂ የዶላር reserve በባንክ ቤቶች በብሄራዊ ባንክ ይዞ መገኘት ይገባል።

ለምን ? ጥቁር ገበያው አይጠፋም። ጥቁር ገበያው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ስላለ ብቻ አይደለም ሌሎችም ምክንያቶች አሉ። sabotage ሊኖር ይችላል፣ ክልከላዎችም እንደ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በዚህም በጥቁር ገበያው ዶላር ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።

floating ኢኮኖሚ ለማሳደግ ብቻ ነው ብሎ መናገር አይቻልም። የውጭ ጫና፣ ብድር ፣እርዳታ ፍለጋም ስላለበት ኢኮኖሚው ስለሚጠቀም ብቻ ሳይሆን የIMF ዓለም አቅፍ ተቋማትም ጫና ስላለ እሱን ለመቋቋምና በቀጣይ ትብብራቸውን ለማግኘት ሲባል ሊወሰን ይችላል።

በጣም በጣም ድፍረት የተሞላበት በአንዴ የሚጠበቅ ውሳኔ አይደለም። በእርግጥ የዛሬ 3 ዓመት ገንዘብ ሚኒስቴር መደላደል ሰርተን floating ጋር እንመጣለን ሲል ነበር።

ገበያው እንዳይናጋም ሊሆን ይችላል " ገንዘብ ይዳከማል ? " ተብሎ መንግስት ሲጠየቅ " በፍጹም እሱን አላሰብንም " የሚል ምላሽ ሲሰጥ የነበረው።

መልሱ ግን እንዲህ ነው የሚጠበቀው devaluate አደርጋለሁ floating አደርጋለሁ ተብሎ በዜና ላይለቀቅ ይችላል።

ውሳኔው በጣም ድፍረት ያለው ውሳኔ ነው።

ገበያው በጣም shock / መናጋት የሚጠብቀው እንደሆነ ምንም ክርክር የሚያስፈልገው አይደለም።

መጀመሪያ የሚሆነው import በጣም ውድ ያደርገዋል። floating ሲደረግ ገንዘብ devaluate መሆኑ / መዳከሙ አይቀርም። ይህ ማለት ወደ ጥቁር ገበያው ወዳለው ተመንና ከዛም ከፍ እያለ ነው የሚሄደው።

ስለዚህ ከባንክ ላይ 58 ብር ገዝተው / በጥቁር ገበያው ተመን ገዝተው ወደ ገበያው import ያደርጉ የነበሩ አሁን floating ከሆነ በጣም በከፍተኛ ገንዘብ 1 ዶላርን መግዛታቸው አይቀርም። በዚህም ከውጭ የገዙት ቁሳቁስ ሀገር ውስጥ ሲገባ ውድ መሆኑ አይቀርም። ከባድ መሆኑም አይቀርም ይሄን መንግስትም ያመነው ነው።

በትላንትናው መግለጫ መጨረሻ ላይ ፥ ' ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችል ተግባራት ይከናወናሉ ። የማህበራዊ ሴፍቲኔት መርሀግብሮች ድጎማ ይደረግላቸዋል ፣ ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሊያስከትሉ ከሚችሉ የአጭር ጊዜ አሉታዊ ተፅእኖ ለመጠበቅ አስፈላጊ የደመው ድጎማና ማሻሻያ ለተወሰኑ ጊዜያት ይደረጋል ' ይላል። ይሄ ማለት ገበያው shock ሆኖ እንደሚቆይ ያውቃል።

ከድጎማ ወጣበታለው ያለውን ነዳጅ እንኳን ' የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን በከፊል መንግስት የሚደጉም ይሆናል ' ይላል። Shock እንደሚፈጠር በጣም ያውቃል። import ቁሳቁሶች በጣም ውድ እንደሚሆኑ ያውቃል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ሸቀጣሸቀጥ ብቻ ሳይሆን ለProduction የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች import ይደረጋሉ፤ ስለዚህ ውድ መሆናቸው አይቀርም።

በፍጹም ደመወዝ አልጨምርም የሚለው ዜና አሁን ደመወዝ እጨምራለሁ እደጉማለሁ እያለ ነው። ከነዳጅ ድጎማ እራሴን አወጣለሁ ይል የነበረው ዜና አሁን መደጎሜን እቀጥላለሁ እያለ ነው። ስለዚህ import ቁሳቁስ ውድ እንደሚሆን ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ ወደ ብድር ስንመጣ የወለድ ተመን ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል መረዳት ይቻላል።

floating ጉዳይ ሲመጣ የተወሰኑትን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችላል። ሌሎችን ተጎጂ ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ በ58 ብር ተመን ጊዜ ዶላር ይዘው የነበሩ ሰዎች ምንዛሬ ሲጨምር የሆኑ አካላት ተጠቃሚ መሆናቸው አይቀርም በግልባጩም እንደዛው ነው።

የመንግስት የዕዳ ክፍያም ለምሳሌ አንድ ዶላር 58 ብር እያለ ዕዳ ውስጥ የገባ ኢኮኖሚና አሁን ሲጨምር እዳ መክፈል የተለያዩ ናቸው። የመንግስት የዕዳ ጫና ሊያድግ ይችላል።

ብዙ ነገሮች import ስለሚድሩግ ገበያው ላይ ተፅእኖ ማሳደሩም አይቀርም።

መንግስት እንደ ጥቅም የሚያስበው ከሌሎች አጋሮች ድጋፍ አገኛለሁ፣ ከIMF ከWB ድጋፍ አላጣም የሚል እሳቤ አለው። ሊሆን ይችላል። ግን የድጋፍ አጠቃቀሙ በጣም መሰረታዊ ካልሆነ ጠቅላላ ኢኮኖሚውን ለመደገፍ ትንሽ ሊያስቸግር ይችላል።

መንግስት ተመልሶ importን ከፍተኛ ደጓሚና አጋዥ መሆኑ አይቀርም። ምክንያቱም የዜጎች የመግዛት አቅም በጣም ደካማ በሆነበት ሁኔታ import inflation አብሮ ስለሚመጣ import በሚደረጉ መሰረታዊ ቁሶች ላይ ከዚህ ቀደም ይወስድ የነበረውም እርምጃ ለመውሰድ ሊገደድ ነው።

መሰረታዊ የማህበረሰብ ፍላጎቶችን መደጎም ውስጥ ሊገባ ነው። ስለዚህ የመንግስትን የሀገር ውስጥ ዕዳ ከፍተኛ እንዳያደርገው ያሰጋል።

የውጭ ቀጥተኛ investment ላይ ማሻሻያው ጥሩ ጎን ሊኖረው ይችላል። አንድ ዶላር ይዞ የመጣ የውጭ ባለሃብት በ58 ብር ይገዛ ነበር አሁን floating ከሆነ devaluate ከተደረገ ይዞት የሚመጣው ከፍ ያለ ይሆናል ምንዛሬው።

በቀጣይ የውጭ ባላሃብቶች ወደ ገበያው ሊያደርጋቸው ይችላል።

ግን በዚህ ወቅት floating መደረጉ በግሌ በጣም አስደንጋጭ ነው። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብዬ አልገምትኩም። "

(ከግል ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የተወሰደ)

@tikvahethiopia

Report Page