Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


በደቡብ ክልላዊ መንግሥት ፤ በጉራጌ ዞን በመስቃን እና ማረቆ መካከል በተደጋጋሚ ጊዜ የፀጥታ ችግሮች እየተከሰቱ የሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ ንብረት ሲወድም ፣ ተማሪዎች ከትምህርት ሲስተጓጎሉ ፣ የመንግሥት ስራም ሲበደል በአጠቃላይ በቀጠናው ከፍተኛ ተፅእኖ ሲደርስ ቆይቷል።

በአካባቢው ያለውን ችግር ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም የዕርቅ ጥረቶች ተደርገውም ያውቃሉ።

ከሰሞኑን ደግሞ በዚሁ አካባቢ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የበርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ጉዳትም ደርሷል።

አንድ ስለ ጉዳዩ አውቃለሁ ያሉ የቤተሰባችን አባል ፤ " መስቃን እና ማረቆ ባንተ ወረዳ ይሄን ያክል ቀበሌ አለኝ አንተ የለህም የኔነዉ ያለኝ ባንተ ወረዳ እየተባባሉ ግጭት ከተጀመረ ከ2010 አንስቶ እስከ ዛሬዉ ቀን ሰዉ ከመሞትና ቤት ንብረት ከመቃጠልና ከመዘረፍ አልቆመም " ብለዋል።

እኚሁ የቤተሰባችን አባል ፤ በዞኑ እንዲሁም በክልሉ ያሉ አመራሮች ለችግሩ ምንም አይነት ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጡ እንዳልቻሉ ፤ ካቅማችን በላይ ነዉ ብለዉም ለከፍተኛ አካል ለፌደራል መንግስት የሰጡት / ያስረከቡት ነገር እንደሌለ አስረድተዋል።

ከሰሞኑንም በዚሁ ቀጠና የሰዎች ህይወት መቀጠፉን ንብረት መውደሙን አመልክተዋል።

ከሰሞኑንቃላቸውን ለሪፖርተር የሰጡት የምስራቅ መስቃን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ፤ " በሀገራዊ ለውጡ 2010 አካባቢ ለውጡን ባለመቀበል የተወሰነ ፅንፈኛ ኃይል ግጭት እንዲከሰት አድርጎ እህትማማች እና ወንድማማች በሆነው ማህበረሰብ ግጭት ተከስቶ መጨረሻ ላይ በክልሉ አነሳሽነት በዞኑ መንግሥት በወረዳው ፣በማረቆ ህዝብ ፍቃደኝነት አምና ጥር 7 እርቀ ሰላም ተደርጎ ነበር " ብለዋል።

ይህ እርቅ ከተፈፀመ በኃላ ከመስቃንም በማረቆም ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ተሰርቶ ነበር ፤ በተደረገው ጥረት ሰላማዊ ሁኔታ ተፈጥሮ እየሄደ ባለበት እርቁ " ህገወጥ ነው ፤ ጥያቄያችን አልተመለሰም " ባሉ አካላት እርቁ 15 ቀን ሳይሞላው አንድ ተፈናቃይ ቤቱ ውስጥ እንደተቀመጠ በክላሽ መመታቱን ፣ 6 ተፈናቃዮችም መገደላቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ በኃላም እርቅ ለመፈፀም ጥረት ቢደረግም ፤ የድንበር የወሰን የቀበሌ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣቸዋል ቢባልም ከሰኔ 14 ጀምሮ ትንኮሳ ሲፈፀም ነበር ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ትንኮሳው ቀጥሎ ከሰሞኑን በቀበሌዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል።

በአካባቢዉ በተለይም የመሰቃንና ማረቆ ማህበረሰብ በስፋት ግጭት ዉስጥ እንደሚገቡበት በሚታወቀዉ አንሲኖ ወረዳ ጋሮሬና ጃይሮ ቀበሌ ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ሰባት የሚደርሱ ንጹሀን ሞትና በርካታ ጉዳቶች መከሰታቸውን ቲክቫህ ከሚመለከታቸው አካላት ያገኘው መረጃ ያስረዳል።

ይህን ችግር ለመቅረፍም ከአካባቢዉ የፖሊስ አባላት በተጨማሪ የክልሉ አድማ ብተና ቡድን አካላት ወደቦታዉ በማቅናት ጥረት ላይ ቢሆኑም ሰላሙ በሚፈለገዉ ልክ መምጣት አልተቻለም።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ ትላንት ትላንትና ስልክ የደወልንላቸው የምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ በመስቃንና ማረቆ ብሄረሰብ ዘንድ የተፈጠረዉን ችግር ለመቅረፍ የአካባቢዉን ወግና ባህል መሰረት ያደረገ ሽምግልና መጀመሩን ገልጸውልን ነበር።

ሰርነቀል መፍትሄ ማምጣት በማስፈለጉ ነው የአካባቢዉን ወግና ባህል የጠበቀ የሽምግልና አንቅስቃሴ መጀመሩን ያስረዱን።

ለእንቅስቃሴዉ መሳካት ከሁለቱም ወገን የሀገር ሽማግሌዎች ታዋቂ ሰዎችና የጸጥታ አካላት ተሳታፊ ሆነው ነበር።

ስለሽምግልና ስርአቱ ሂደት እንዲሁም የአካባቢዉን ሰላም ለማስጠበቅ ስለተሰማራዉ የፖሊስና ተጨማሪ ሀይል በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ የሽምግልና ሂደቱ ሳይጠናቀቅ መረጃ መስጠት አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ ጥያቄዉን በይደር አቆይተዉታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ ዛሬ ጥዋት በዲዳ ቀበሌ ለገበያ ወደ ኢንሴኖ ከተማ በማቅናት ላይ የነበሩ ገበያተኞች ላይ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ 8 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ 14 ቆስለዋል።

አብዛኞቹ አዛውንቶች እና ሴቶች መሆናቸው ተመላክቷል።

ታጣቂዋቹ ጥቃቱን ከፈፀሙ በኋላ ከአካባቢው ተሰውረዋል ተብሏል።

ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የቤተሰባችን አባል ፤ ረጅም ጊዜ የቆየ የቀበሌ ይገባኛል ጉዳይ በቀጠናው መኖሩን አስታውሰዋል።

ከሳምንት በፊት እንዲሁም ከቀናት በፊት የሰዎች ህይወት የቀጠፈ ጥቃት መሰንዘሩም አስረድተዋል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

Report Page