Tikvah Ethiopia

Tikvah Ethiopia


#የጀግኖቹ_ወላጆች

የኢትዮጵያን ስም በዓለም ከፍ እያደረጉ ካሉት አትሌቶቻችን መካከል ቤተሰቦቻቸው የግንኙነት መስመር ከዓመት በላይ በተቋረጠበት ትግራይ ክልል ውስጥ ይኖራሉ።

እነሱን ጨምሮ ሁሉም የክልሉ ህዝብ የኢንተርኔት ግንኙነት ባለመኖሩ ስሜቱን እንደኛ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለማጋራት አልታደለም።

ከከተማ ወጣ ባሉ የትግራይ ክፍል የሚኖሩ የአትሌቶች ቤተሰቦችም የልጆቻቸውን ድል የሰሙት ሌላው የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው።


#ለተሰንበት_ግደይ


የለተሰንበት ግደይ እናት እና አባት የልጃቸውን ድል የሰሙት እሁድ ዕለት ነበር። የለተሰንበት አባት ወደ መቐለ በሄዱበት ወቅት ነው የልጃቸውን ድል የሰሙት።

ይህንን ለእናት የነገሯቸው እሁድ ማታ ነበር። በዚህም እናት ደስ ቢሰኙም ደስታቸው ሙሉ አልነበረም ፤ ምክንያቱም የልጃቸውን ድምፅ ሊሰሙ ውድድሩን ሊከታተሉ አልቻሉምና።

እናት እና አባት ልጃቸውን ካገኙ ቀጣይ መስከረም ሁለት ዓመት ይሆናቸዋል።

ከዚህ ቀደም እየተመላለሰች የምታግዛቸው የምትረዳቸው ለተሰንበት እንደነበረች የሚገልፁት ወላጆች ስልክ ደውላ በባንክ ገንዘብ ትልክላቸው እንደነበር ነገር ግን አሁን ባንክ ፣ ስልክ አጠቃላይ ግንኙነት ባለመኖሩ ልታገኛቸው እንዳልቻለች ገልፀዋል።

በስልክ ሆነ በሌላ አማራጭ ለማያገኟት ልጃቸው " ነገ መንጋቱ አይቀርምና ጠንክረሽ ስሪ፣ ይሄ ግዜ አልፎ ከትግራይ ህዝብ ጋር የምትገናኝበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፤ በሰላም ያገናኘን " ብለዋታል።


#ጎተይቶም_ገብረስላሴ

የማራቶን የወርቅ ባለድሏ የጎተይቶም ገብረስላሴ እናት ወ/ሮ በረኽይቱ ካሳ በልጃቸው ድል ደስ ቢሰኙም ደስታቸው ሙሉ አይደለም።

ነዋሪነታቸው በእንደርታ ወረዳ ማይቀያህ የምትባል መንደር የሆነው የጎተይቶም እናት ፤ ድሉን የሰሙት ውድድሩ ከተጠናቀቀ ከሰዓታት በኃላ ምሽት አራት ሰዓት ላፕ ነበር።

ከድሉ በኃላ " ድሉን ቢሰሙ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ወላጆቼ ይደሰቱ ነበር ስትል " እኔም ከእሷ ጋር አለቀስኩኝ የሚሉት እናት " በጣም ተደስቻለሁ ግን ደስታዬ ግማሽ ነው። ከዚህ በፊት በነበረው ውድድር ስታሸንፍ ቀጥታ ስትደውል ነበር። በስልክ ነበር የምንገናኘው። አሁን ከሁለት ዓመት ወዲህ ስትወዳደር በቴሌቪዥን ነው የምንሰውማው እንጂ በስልክ አንሰማም " ብለዋል።

ከልጃቸው ጋር ከ7 ወር በፊት አላማጣ ሄደው በስልክ የተገናኙ ሲሆን ከዛ በኃላ ግን በሰዎች በኩል በድምፅ አድርጋ ነው የምትልከውና ድምጿን የሚሰሙት።

እናት " ሁሉን ተሸክማ ናፍቆትም ፣ ሁሉን ነገር ተሸክማ እዚህ መድረሷ በጣም ነው የተደሰትኩባት እዚህ መድረሷ በጣም ደስ ያለኝ። የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው እንጂ ቤተሰቧን ሳታገኝ እዚህ መድረሷ በጣም ነው ደስ ያሰኘኝ። " ብለዋል።

ጎተይቶም ፤ ከሚደሰተው የምትደሰት ፣ ከሚያዝነው ጋር የምታዝን፣ ተጫዋች ጠንካራ ነበረችው የሚሉት እናት " ወደ አትሌትነት የገባችው ከትምህርት ቤት ነው በልጅነቷ ተፅእኖ ያሳድር የነበረው ቁንጣ ስታደርግ ቁንጣ ምን ያደርግላታል ይሄ የወንዶች ነው። ለምንድነው እንዲህ ምታደርገው ስትባል ነበር። እኔ ግን ልጄ ጠንካራ ናት ከህፃንነቷ ጠንካራ መሆኗን አውቄ የፈለገችውን ታድርግ ብዬ እያልኩ ነው እዚህ የደረሰችው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ጠንካራ ስለሆነች በእግዚአብሔር ፍቃድ እኔ ጋዜጠኛ ትሆናለች ብዬ ነው የተመኘሁት " ሲሉም አክለዋል።

እናት ለልጃቸው " ጎተይቶም ልጄ ከህፃንነትሽ ጀምሮ ነው የኔን ክብር የምታሳይኝ ልጄ ያንቺን ልጅ ለመሳም ነው የምመኘው አይዞሽ ደስ ይበልሽ ለመገናኘት ያብቃን ነገ ይነጋል ሰው ለሰው ይገናኛል ይነጋልና አይዞሽ በርቺ " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ከዚህ ባለፈ ሰላም ሰፍኖ የተራራቀ እንዲገኝ የልጆቻቸውን ድምፅ እንዲሰሙ፣ ሌላውም ከወገኑ ጋር እንዲገናኝ ተመኝተዋል።

" እኔ ምኞት ሰላም ሆኖ ከህዝቤ ጋር ፣እንደ ህዝቤ ትውልድም ወላጅም ሁሉ እንዲገናኝ ነው የምመኘው ጎተይቶምም ይሁን ከሌሎች ልጆቼ ከወንዱም ከሴቷም ከሁሉም ቤተሰብ ለመገናኘት ሰላም ቢሆን ነው ምኞቴ "ብለዋል።

(ይህ ፁህፍ የተዘጋጀው የአትሌቶቹ ቤተሰቦች ለቪኦኤ ትግርኛው ክፍል እና በትግራይ ቲቪ እንግሊዘኛ ክፍል ከተሰጡት ነው)

@tikvahethiopia

Report Page