Tikvah Ethiopia

Tikvah Ethiopia


🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ መንግስት እንደ መንግስት ሥራውን እየሰራ አይደለም ” ሲል ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ተቸ።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ የነበራቸው የፓርቲው ሊቀመበር ዶክተር አብዱልቃድር አደም ስለወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች የፓርቲያቸውን ምልከታ ተናግረዋል።


Q. ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ውሳኔ መዘግዬት ዜጎችን ቅር አሰኝቷል። በተቃራኒው የኑሮ ውድነቱ ደግሞ ንሯል። ምን በጀ ?

ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ፦

“ እኛም ከኢሰማኮ ኃላፊዎች ቢሮ ሂደን ተነጋግረናል። አሁን ባለው ሁኔታ ይበልጥ ተጎጂ እየሆነ ያለው ዝቅተኛ ደመወዝ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ነው።

የሠራተኞች ክፍያ እጅግ በጣም ዝቅተኛ እና ዜጎችን በህይወት የማያቆይ ነው።

ሙስናውንም የሚያባብሰው ያ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን በጥናት ተመስርቶ Introduce ማድረግ ያስፈልጋል። ”


Q. በተለይ ሰሞኑን የሚወጡ ዐዋጆች ተበራክተዋል። አንዳንዶችም፣ “ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ያመዘነ ነው” ሲሉ ይተቻሉ። የፓርቲዎ ግምገማ ምንድን ነው?

ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ፦

“ዐዋጂ አገር የሚመራበት ቁልፍ ነገር ነው። ዐዋጂም ሆነ ደንብና መመሪያ ሲዘጋጂ ግን ጥንቃቄ፣ ውይይት፣ አገራዊ አንድምታ ያስፈልገዋል።

በእርግጥ ባለፉት 5 ዓመታት የተቻኮሉ ውሳኔዎችን፣ ህጎችን ማውጣት፣ ተቋማትን አቋቁሞ ምንም ሥራ ሳይሰሩ መልሶ ማፍረስ እየተለማመድነው መጥቷል።

እናም ህግ ሲወጣ በግልጸኝነት ማንን ይጠቅማል? ማንንስ ይጎዳል? ብሎ አጢኖ ጉዳቱን Mitigate ለማድረግም ቅድመ ዝግጅት ያስፈልጋል።”


Q. በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ችግር ባለመቆሙ ንጹሐን እየተገደሉ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። የፓርቲዎ ግምገማና የመፍትሄ ሀሳብ ምንድን ነው?

ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ፦

“አሁን ላለው አገራዊ ሁኔታ ትልቁና መሠረታዊ ችግር ጦርነትና ግጭት ነው። በኢትዮጵያ በተለይ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ከፍተኛ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ነው።

ሌሎች አካባቢዎችም ሰላምና የተረጋጉ ናቸው ማለት አይደለም። እዚህም እዚያም ውጥረቶች አሉ። ለምሳሌ አፋርና ሶማሌ መካከል በወሰን ምክንያት ግጭት አለ። 

በዚህ ምክንያት ዜጎች ይገደላሉ። አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል፤ በሌሎች አካባቢዎችም ከቄያቸው ይፈናቀላሉ።

ዜጎች ‘መንግስት አለ፤ መንግስት ይጠብቀኛል፤ የምከፍለው ግብር ሰላሜን ያስጠብቅልኛል’ ብለው የሚያስቡበት ሁኔታ የለም።

የዜጎች ከቤት በሰላም ወጥቶ መመለስ እጂግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። የክልልነት ጥያቄዎች መልስ አላገኙም፤ ቅሬታዎች አሉ።” 

ስለፓለቲካ ምህዳር ዶ/ር አብዱልቃድር ምን አሉ ?

“በሌላ በኩል ግልጽ ከሆነው ጦርነት መለስ ስንል የፓለቲካ አለመረጋጋት አለ። የፓለቲካ ምህዳሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጠቧል። 

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፕሮግራም ማዘጋጀት፣ አባላትን መቀስቀስ በምርጫ ወቅት ዋና ዋና ተግባሮቻችን ነበሩ፣ ግን ማድረግ አልተቻለም።

የመንግስት ሚዲያዎች በታክስ ከፋዩ የሚተዳደሩ ናቸው፤ ነገር ግን Almost የአንድ ፓርቲ ልሳን ናቸው። ገዢው ፓርቲም ይህንኑ የሚክድ አይመስለኝም።

በገዢውና በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ የሆነ አለመተማመን አለ። ይሄ በምርጫውም በሀገራዊ ምክክሩም ላይ ይስተዋላል። አብሮ የመስራት እድል በጣም ጠቧል።”


የመልካም አስተዳደር እጦትን በተመከተ ዶ/ር አብዱልቃድር ምን አሉ?

“የመልካም አስተዳደር ሁኔታ Almost ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ ይመስላል። 

-የብልሹ አሰራር/ሙስና መንሰራፋት፣

-የግልጸኝነትና ተጠያቂነት መርሆች መጣስ፣ 

-የዜጎች ያለ በቂ ምክንያት መታሰርና መንገላታት፣

-የፓለቲካ ፓርቲዎች አካላትና መሪዎት መታሰር፣

-የታሰሩ የህዝብ እንደራሴዎች ለፍርድ አለመቅረብ፣

-የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እየተለመደ መጥቷል።

መንግስት እንደ መንግስት ሥራውን እየሰራ አይደለም። 

ክልሎች አካባቢ የሚስተዋሉ የሠራተኞች በወቅቱ ደመወዝ አለማግኘት አጠቃላይ የቢሮ ክራሲውንና የሲቪል ሰርቪሱን የተበላሸ እንዲሆን አድርጎታል። ”


ምጣኔ ሀብትን በተመለከተ ዶ/ር አብዱልቃድር ምን አሉ?

“የMacro Economy መናጋት አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ የከፋ ሁኔታ ላይ ደርሷል። የኢትዮጵያ የልማት ስትራቴጂ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ ነው።

ይልቁንም ትኩረት የሚሹት ኢንፍራስትራክቸር፣ መብራት፣ ጤና፣ ውሃ መሠረታዊ ችግሮች ናቸው፤ ዜጎች በእነዚህ ነገሮች ተቸግረዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚል የሚሰራቸው ፕሮጀክቶች መቃኘት አለባቸው። ከፍተኛ የንግድ ጉድለት አለ። የምንሸጠውና የምንገዛው ልዩነቱ የሰፋ ነው። 

የበጀት Deficit አለ። መንግስት የሚሰበስበውና የሚያወጣውን ገንዘብ ለዚያውም አስፈላጊነታቸው አጠራጣሪ ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘቡ ወጪ ይሆናል።

ይሄ ኢኮኖሚው እንዲናጋ አድርጓል ብለን እናምናለን።”


የውጪ ግንኙነትን በተመለከተ ዶ/ር አብዱልቃድር ምን አሉ?

“ከቅርቡ ስንጀምር ጎረቤት አገሮች ጋር ያለን ግንኙነት ተቀዛቅዟል። አንዳንዴ እንዲያውም ወደ ውጥረት እንዳንሄድ ስጋት አለን።

ከሀያላን ሀገራት (East and West) ጋር ያሉን ግንኙነቶች ኢትዮጵያ በታሪክ የነበራት ተሰሚነት የለም። በቀጠናው ላይ ያለውን የበላይነት ኬኒያ እየወሰደች እንደሆነ እያየን ነው።

ሌላው የባህር በር ፍላጎት ጋር በተያያዘ የገባንበት በደንብ ያልተቃኘና የተቻኮለ ውሳኔ የውጪ ግንኙነታችንን እና ገጽታችንን አበላሽቶታል።”


Q. ታዲያ ለችግሮቹ ሁሉ መፍትሄያቸው ምን ይሆን?

- መንግስት ጦርነትን ማስቆም፣

- የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን መደገፍ፣ 

- ሙሰኞችን አስተማሪ ቅጣት መቅጣት

- የታመመውን ኢኮኖሚ በሥር ነቀር ማከም፣

- የፓለቲካ ምህዳር ማስፋት(የሚደያ Access)፣

- ለሥራ እድል እና ለኑሮ ውድነት ትኩረት መስጠት፣

- በሀገራዊ ምክክሩ መተማመን እንዲኖር ማድረግ፣ ወ.ዘ.ተ የመፍትሄ ሀሳቦች ናቸው።


#የፓለቲካፓርቲዎችምንይላሉ #ነእፓ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

Report Page