Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


የቤት ኪራይ . . .


የነዋሪዎች ድምፅ !

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ ፤ ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር / ተከራይን ማስወጣት እንደማይችል ይወቀው " ካለ በኃላ ነው።

የከተማ አስተዳደሩ መመሪያ " እየተራዘመ " ዛሬ ድረስ የመጣ ሲሆን የእስካሁን ተግባራዊነት ምን ይመስል ነበር ? አሁንስ የቤት ኪራይ ጉዳይ ምን ላይ ነው ? በሚል ለአ/አ ቤተሰቦች ባቀረብነው ጥያቄ ከተከራዮች እንዲሁም ከአከራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶች መጥተዋል።

ከብዙ በጥቂቱ በዚህ አሰባስበን አስቀምጠናል።

.

.

.

" ቤት ኪራይ ተጨምሮብኛል ፤ አከራዮች ቤት ኪራይ ካልጨመርሁ ለእድሳት ብለው እንደሚያስወጡኝ ነው የነገሩኝ " - ነገሰ

" መመሪያዉ ወረቀት ላይ ብቻ ነዉ እኔ 1000 ብር ተጨምሮብኛል " - ሰርካለም

" የምን መመሪያ ነው የሚሉት ? እንደፈለጉ ነው ሚጨምሩት እኮ " - ሃዩ

" ተግባራዊነቱ 0 ከመሆኑም በላይ ጭማሪው ወደ እኛ እንዲወርድ ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ የሚመስለው " - ኩም

" እኔና ጎረቤቶቼ ከ 4ወራት በፊት የቤት ኪራይ ጭማሪ ተደርጎብን ጨምረን የነበረ ቢሆንም አሁን የቤት ባለቤቶች ላይ በተጣለባቸው ግብር ምክንያት ሁላችንም ቤታቸውን ለቀን እንድንወጣ ተነግሮን ሌላ ቤት እያፈላለግን ቢሆንም ሌላ ቦታ ላይ ያለው ጭማሪም የቤቱንም ሆነ የሰፈሩት ሁኔታ እንኳ ያገናዘበ አይደለም፡፡ እናም ተጨንቀናል " - ዲግ

" አከራይ ላይ ብቻ መፍረድ ትክክል አይደለም መንግስት የሚሰራውን አያቅም " - አብዱ

" አዎ እውነት ነው ከምነግራችሁ በላይ ጭማሪ ነው የተደረገው ፤ ሰው ተሰቃይቷል፤ ከማውራት ባሻገር መሬት ላይ ስራ ይሠራ " - ሃይሌ


" ሰላም እንዴት ናችሁ በከተማችን አዲስ አበባ አብዛኛው በሚባል ከመሬት ግብር ጭማሪ ጋር በተያያዘ የቤት ኪራይ በትንሹ ከ1000 ብር ጀምሮ እንዲሁም የንግድ ተቋማት ላይ ከ3000 ጀምሮ እየተጨመረ ነው ያለው አልጨምርም አልወጣም ለሚል ተከራይ በውሃና በመብራት እየጎዱት ነው ያለው ይህም እንዲታይ ጥቆማ ብሰጡ አመሰግናለሁ " - ናታኔም

" እኔ የምኖረው ቤቴል አካባቢ ነው ባለሁበት ህንፃ ውስጥ የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ኪራይ እንዳይጨመር መመሪያ ካወጣ በኃላ ለሶስተኛ ጊዜ የጨመሩ ሲሆን አሁን ደግሞ ከ100 ፐርሰንት በላይ ጨምረዋል። " - ስሜ አንዳይጠቀስ

" አልቻልንም ቤት ክራይ ባንዴ 1000 ብር ተጨምሮብኛል መኖር የቻልን አይደለም " - ፎርቲን

" እኔ ተከራይቼ የምኖርበት ቤት የወጣው ደንብ ሳይቀየር ከሶስት ወር በፊት አንድ ሺህ ብር እንድንጨምር ተደረገ። ምንም ሳናንገራግር ጨመርን። አሁን ደግሞ የሰኔ ወር ስንከፍል ህጉ እስከ ሰኔ እንዳይጨምሩ ቢደነግግም ከሚቀጥለው ሁለት ሺህ ብር እንድንጨምር ተነግሮናል። ባጠቃላይ ሶስት ሺህ ብር ማለት ነው። " - ሰሉ

" እኔ ሶስት በአራት አንድ ክላስ ቤት ላይ 4ሽ ነበር የምከፍለው 1ሽ ብር ጪማሪ ተደርጎብኛል 5000ሽ ብር ነው የምከፍለው ባለትዳር ነኝ ደሞዜ 8800ብር ነው ሚስቴ ስራ የላትም መኖር ሁሉ አስጠላኝ ጊዜው አአ ላይ መኖር አያስችልም በእውነት መግለፅ በማልችለው ሁኔታ ህዝብ ተማሯል እግዚአብሄር አምላክ ብቻ አገራችንን ሠላም አድርጎ አከራዮችንም ልቦና ሰጥቶ የተረጋጋ ህይወት እንድንኖር ያድርገን አመሠግናለሁ። " - ዘላለም

" ጤና ይስጥልኝ፣ እኔ የምኖረው ሃያት 49 አካባቢ ሲሆን 40/60 ላይ ተከራይቼ ነው፡፡ እናም የኔ አከራይ ብር ጨምር ላለማለት ቤቱን እፈልገዋለሁ ልገባበት ነው የሚል ምክንያት ነው የሰጠኝ፡፡ " - ዘሩባበል

" መንግስት ራሱ እጅግ የተጋነነ የካሬ ዋጋ እየተመነ ሌላውን አትጨምር ማለት ጭፍን የሆነ አሰተዳደር ነው " - እንግዳ


" እውነት ለመናገር ከመግለጫው ያለፈ አይሆንም " - አቢም

" እኔ የመንግስት መ/ቤት የምሰራ ሲሆን የግለሰብ ቤት ተከራይቼ ነው የምኖረው፤ የተጣለብኝን ከፍተኛ ግብር አሁን ባለው ኪራይ መሸፈን ስለማልችል ብሎ እጥፍ ጭማሬ ተደርጎብኛል፤ ለምን ብለን ስንጠይቅ ካልጨመራችሁ ቤቱን ልናድሰው ነው ውጡ ነው የሚሉን፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ተግባራዊነቱ ዜሮ ነው፡፡ በተለይ በፌደራል መ/ቤት የምንሰራ የመንግስት ሰራተኞች እንደከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች የቤት አላዋንስ ስለማይከፈለን ኑሮን ለመቋቋም ተቸግረናል! በዚህ ከቀጠለ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ጎዳና ነው የሚወጣው ! እባካችሁ በተለይ በፌደራል መ/ቤት ለምንሰራ የቤት አላዋንስ ለምን እንደማይከፈለን የሚመለከተውን አካል አነጋግራችሁ ምላሽ ስጡን " - TGD

" ወሬ ብቻ ተግባር የለም አከራይ ዉጣ ቢል ወይም ጨምር ቢል የተኛው የህግ አካል ነው ሚያስከብረው ? እምቢ ብለክ የቁም እስረኛ ከምቶን ተስማምቶ መጨመሩ ግድ ሆኖዋል ፤ ደግሞ በውስጥ አዋቂነት አስገድደው ነው ሚያስጨምሩት፤ እንደ ሰው አገልግሎት ማግኘት አትችልም ዉሃ፣ ሽንት ቤት፣ የግቢ በር በመዝጋት፣ ልብስ ማስጣት አትችልም ስትባል ሲመርክ ትለቃለክ። አከራዩም ጋር ስትሄድ ያላቅሙ ግብር ተጠይቆ ኬት ያምጣ ወይስ ቤቱን አፍርሶ ይቀመጥ ? አንድ ላይ። ብቻ ሆድ ይፍጀው " - ኤኣር

" አከራዮችም እኮ አገሪቱ ላይ የተከሰቱ ነዋጋ ንረቶች ሰለባ መሆናቸው መረሳት ነለበትም። መንግሰት ጭማሪ ሲያደርግ ይህ እንደሚመጣ ቀድሞ ማሰብ ነበረበት ። " - አቡ

" እና ከየት አምጥቶ ይክፈልህ ግብር ? ስትጨምር ገቢም እንደሚጨምር ማገናዘብ አለብህ "- ABI

" አረ ወንድሞቼ ሁሉም ቀልድ ሆነ! ከተማ አስተዳደሩም ህግ ማውጣት እንጂ ተፈጻሚነቱ ላይ ዜሮ ነው ማለት ይቻላል። ካቢኔው የወሰነውን ሽሮ ጭማሪ ሲያደርጉ እና ካልጨመራችሁ ልቀቁልን ሲሉ ማን አየ? ማን ጠየቀ! ይህን በመመርኮዝ ቀበሌ ለማመልከት ሲኬድ ዘና ብሎ በፌዝ መልክ ተስማሙ ነው የሚሉት! አረ ተውን! ሁሉም እንደፈለገ ደሀው ላይ የሚፈነጭበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የማይሰራበት አዋጅ፡ ህግ እና መመሪያ ለምን ይወጣል? " - ቀልቤሳ

" Ene lenigid tekerayich yemiserabet hinitsa beamet 800,000 birr new temisebesibut kezihim lay ametaw tirif Ena 10% TOT yikefilalhu menigist gin berenida Hulu sayiker lekito beamet 3.6 million new yemitisebesibut Bilo 155,000 birr bezi amete enidikefilhu kemiketilew amet jemiro wede 600,000 birr yemitega birr teminobachewal Ene lebiro yemikefilew 15,000 neber Menigist beziw keketele gin wede 40,000 birr akababi yihonal tezegaju bilewal " - Abissinya


" ይሄው እኔ ራሱ 9000 ነበር ምከፍለው ባንዴ 5000 ብር ተጨምሮብኝ ቤት ፍለጋ ላይ ነኝ 😭😭😭 " - አትዌይት

" እኔ በምን ቃላት መግለፅ እንዳለብኝ አላውቅም እብረተሰቡ ኑሮ ከብዶናል መንግስት መላ ይበለን እኮ ነው እያልን ያለነው አይሰማም እንዴ? እሱም ሳያንስ በግብሩ ምክኒያት የቤት ኪራይ መጨመር ምን የሚሉት ነው ።ወደድክም ጠላህም አከራይ በሁላችንም ላይ ጨምሮአል እንደየቤቱ ሁኔታ ከ500 ብር ጀምሮ ለማን አቤት ይባላል ? " - ብዙአለም

" የከተማ አስተዳደሩ ዉሳኔ #ፌዝ ይመስላል። ደሞዝ ጨመረ በሚል፡ሰበብ የእቃ ዋጋዎች በእጥፍ በሚንሩባት ሃገር፣ አከራይ ላይ ግብር ስትጨምር ከዚህ ዉጪ ምን እንዲሆን ጠብቀዉ ነበር ? " ዝጎራ

" አከራይ ምን ያድርግ ? የሌላውን ገንዘብ ለመንግስት ከየት አምጥቶ ይክፈል ? አሁን ባለው ሁኔተ እያስወጠ ያለው አከራይ ሠይሆን መንግስት እራሱ ነው ። መንግስት ህጉን ከመውጠቱ በፊት ቆም ብሎ ብየስብባት ይሸላል። " - ያረቢ አማና

" የንግድ ሱቅ ተከራይቼ እሰራለሁ ነው፤ ባለቤቱ 60% ጨምሩ ያለ ቢሆንም ከብዙ ጭቅጭቅ በሗላ 35% ጭማሪ አድርጓል " - የሰብ

" ተግባራዊ አይደለም ይህ ፖለቲካ ነው። እኔ አከራዬ ያልተገባ ጭማሪ ቢጨምሩብኝ ለማን ነው የምከሰው ? ብከስስ አከራይ ጋ ተደባብሮ መኖር አይሆንም ወይ ? ጥቆማ ብሰጥስ አከራዮች ተከራይን በወጣ በገባ ቁጥር ያልተገባ ነገር አይደርስ ወይ?

አከራይ የውሃ እና የመብራት ሲጨምርበት በረንዳ ለበረንዳ ኡኡኡ የሚለው እኮ 90% ነው። እሱም ባይሆን በትንሽ በትልቁ ንትርክ ይፈጥሩ እና ተከራይ ተማሮ ሲወጣ የሚገባው አዲስ ሰው ላይ የፈለጉትን ይጨምራሉ !

ደግሞም አከራይም ትክክል ነው ድሃ ሰርቶ ጥሮ ግሮ በሰራው ቤት መንግስት ያልተገባ ግብር ሲጠይቃቸው ንሮ ቀን በቀን እዬጨመረ እነሱስ በምን እንዲኖሩ ታስቦ ነው ?

ለምሳሌ እኔ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ ያልተገባ ወርሃዊ ግብር እከፍላለሁ ኢሰማኮ እንደሚያውቀው ከሱ የተረፈኝ ቆጥቤ ቤት ብገዛ ዞሮ ላልተገባ ግብር የምመለስ ከሆነ ቤት ገዝቶ መስራትስ ከኪራይ መች አስወጣ ?

መንግስት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት ሲገባ በድሃው ላይ በዬግዜው የሚያርፈው በትር ሀገሪትስ ካለባት ችግር ሳትወጣ ሰላማዊ ዜጋን እስከመሃል ገብቶ ማሸበር ምን ይሉታል ? ሁሉ ነገር በጨመረ ቁጥር ድሃውን ህዝብ ነው እዬጎዳ ያለው እስከመቸ ነው ይህ የሚሆነው ?* መንግስት ግራ ገብቶት የሚያሸንፈውን ህዝብ ላይ በትሩን ከማሳረፍ ካላወረደ አከራይ መጨመሩም ተገቢ ነው።

ምክንያቱም እነሱም ሁሉም ነገር እዬጨመረ በመጣ ነገሮች ጥረው ግረው የሰሩት።

እኔ ቢጨመርብኝ የማዝነው ባከራዬ ሳይሆን በመንግስት ነው ። አሁን ባለው ሁኔታ መንግስት ተቸግሮ እያስቸገረ ያለው እያንዳንዱን ህዝብ ከገበሬ እስከ ከተማ ነው እያመሰ ያለው ስለዚህ መንግስት ራሱ ካልተረጋጋ ህዝብን በዚህ ተራ የፖለቲካ ወሬ ማንም አይደሰትም ። ካለፉት የኮሮና እና ከተማ አስተዳደሩ እንዳትጨምሩ ካለ ጀምሮ ነው ከፍተኛ ጭማሪ በተከራይ የሚጠዬቀው።

በተወደደ ስሚንቶ እና ብረት :አሸዋ ጠጠር እዬተበደሩ የሰሩትን ቤት ከፍተኛ ግብር ጠይቆ ንብረት ላይ አትጨመሩ ማለት ስላቅ ነው።

ራሱ መንግስት ቆም ብሎ ያስብ !

ወይም የካሬ ግብር ተግባራዊ ቢደረግ ትንሽ መፍትሄ ያመጣል ግን ይህም የግል ንብረትን ነፃነት መጋፋት ነው። አመሰግናለሁ። " - እብኖ


" እኔ በመሪ ሎቄ ሳይት ባለሁለት መኝታ ደርሶኛ ከባለፈው አመት ሰኔ ጀምሮ እየኖርኩበት ነበር። እስካሁን ድረስ ውሃ የለም ። በስንት ክርክር መሬት ድረስ አድርሰውልን በሳምንት አንድ ቀን እሁድ እሁድ እንወስዳለን ። አንድ ጀሪካን ውሃ በ18 (ለተሸካሚ 15 ብር እና ለውሃው 3 ብር) ብር እየገዛን ነው የምንኖረው ። ይህም እስከ 6ኛ ፍሎር ነው ከዛ በላይ ከሆነ ደግሞ እስከ 30 ብር ይጠጋል። መንግስት ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ እየኖርን የይዞታ ግብር ብሎ 3318(2886 ፍሬ ግብር + 433 ቅጣት (15%) ብር አስከፈለን። ይህም የ2015 50% ግብር ነው። ለ2016 ደግሞ ሙሉው ሲሆን ወደ 6ሺህ ይጠጋል፣ እሱንም መንግስት ካልጨመረበት ነው። የሚያሳዝነው የቢቱ ወርሃዊ ኪራይ ግምት ከ11ብር በላይ ተገምቶ የዚህን አመታዊ ኪራይ 4.5% ክፈሉ ማለት የጤና ነው? እና መንግስት ኪራውን በዚህ ገምቶ ካስከፈለ አከራዩ በዚህ ስሌት መሰረት ተከራዩን ቢያስከፍል ጥፋቱ ምን ላይ ነው? ቤቱ ያንተ ነውና ግብር ክፈል ካለኝ በገንዘቤ የፈለገኝን ብጨምር መንግስት ምን አገባው? መንግስት ከሚገባው በላይ እየጠየቀ እኔን የሚገባኝን እንዳልጠይቅ የሚከለክል ህግ ከየት ነው ያለ? " - TD

" በሚያሳዝን ሁኔታ ህዝቡን ለማማረር አስበው ካልሆነ በስተቀር እሄ አግባብ የሌለው ጭማሪ ሲደረግ ለዛውም ህዝቡ በዚህ በኑሮ ውድነት፣ በመፈናቀል፣እንዲሁም በአጠቃላይ በኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ላይ ባለንበት ወቅት እንዲህ አይነት ያልተገባ ግብር ጭማሪ ሲደረግ የቤት ኪራይ እንደሚጨምር የታወቀ ነው።

ካሁን በኃላ በአከራዮቻችን ላይ መፍረድ ተገቢ አይደለም ዋነው የችግሩ ፈስጣሪ መንግስት ነው።

እኔ ትንሽ የንግድ ሱቅ አለችኝ የምኖረውም ተከራይቸ ነው። አሁን የምኖርበት ቤትም ሆነ ሱቅ ጭማሪ ተጠይቄያለሁ፤ አጠቃላይ ስራ በጣም ቀንሷል፤ በዛ ላይ አሁንም በመንግስት በኩል የንግድ ግብር መጨመር አለብት ተብሎ ተወስኗል። አሁን በአከራዮቻችን እንዴት እንፍረድ? እሽ የገዛ ሀገራችን በተቸገርንበት በዚህ ወቅት መንግሥት (ካለ) ካልተረዳን ማን አዝኖ ይቀበለናል።  ብቻ ይጨንቃል። " - ቫም

" እነሱ ምነው የቤት ኪራይ ላይ ብቻ ትኩረት አርገው ከመስራት በየቀኑ ተለዋዋጭ የሆነውን የገበያ ሁኔታ ለማሻሻል ቢሰሩ የቤት ኪራይ ተቀብሎ ስንት ቤተሰብ የሚያስተዳድር ሰው በሞላበት ሀገር ምን ተርፎት ነው ይሄን ያህል ግብር የሚከፍለው ተዘዋውሮ ሰርቶ ቤተሰብ የሚያስተዳድር ግለሰብ ወጥቶ መመለሱን እርግጠኛ ባልሆነበት ሀገር የት ሰርቶ ግብር ይከፍላል ? መጀመሪያ ሰላም ላይ ይሰራ ከዛ ሰው ጠግቦ የሚያድርበት ሁኔታ ፍጠሩ ሰው ከሰራ ሰላም ካለው ለሀገር ነው ይከፍላል " - TB

" In my opinion thr government is losing the game . Maseb yalebn eko tekeray endemechegerew hulu akerayem ybelal ytetal yastmral yalebsal bzaw lik dmo ychegeral . Mengest gn akeray lay eytalew yalew chana ejg betam keftgn ena ke lik yalefe nw. Eski ehen tyake yememlsgn

አከራይ የገቢ ምንጩ ከኑሮ ጋር አብሮ ካልጨመረ ግብር ከየት አምጥቶ ነው ለመንግሥት የሚገብረው??

Yehen tyake tekerayochm betgarut desyelgnal Amesegnalw " -Ki

" ሰላም ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች። እኔ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ነው የምኖረው፣ አሁን በተነሳው የኪራይ ጭማሬ ህዝቡ ግራ ገብቶት መሮን ነው ያለው። ተፈናቃዩ በመብዛቱ እና ሸራ ቤቱ በመፍረሡ ቤት ብትፈልግ ራሱ አይገኝም ። እኔ እንዳያስወጡኝ ብዬ ቀድሜ ራሴ ብር እዬጨመርኩ ነው፣እንደዚሁም ብለው አንዴ የማብራት አንዴ የውሃ የክፍያ ደረሰኝ ያመጡብኛል፣እንዳይጨምሩ ጨንቋቼዋል፣ከሠሞኑ ግን እንድጨምር ተነግሮኛል።እወጣለሁ እንጅ አልከፍልም ብያለሁ።ሠው ጋ የሚኖሩ አይመስሉም እኮ በፈጣሪ። " - አሚ

" አረ ተዉን መቼ ተግባራዊ ተደረገ ይሄው ዉጣ ተብዬ ቤት ጠፋ ቢገኝ እንኩዋን ከ አቅም በላይ ነው ምንስ ተሰርቶ ይከፈላል " - ኤልያስ

" እኔ አከራይ ነኝ። ለጊዜው ጭማሪም ሆነ ተከራይን ማስወጣት አላስሰብኩም ። ግን ውሳኔዬ ከሰብአዊነት የመነጨ እንጂ ህጋዊ መሠረት የሌለውን "የመንግሰት ማሳሰቢያ" በማክበር አይደለም ! " - አቡ


" የቤት ኪራይ አልተጨመረብኝም፡ ግን ቤቱን ለራሴ ጉዳይ ስለምፈልገው ውጡልኝ እየተባልን ነው፡፡ ምክንያቱን ሳጣራ ግን ይሀው ግብር ነው ብለውኛል። " - ጎበዜ

" ሠላም ቲክቫዎች በአከራይና ተከራይ ያለዉ ጭንቀት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የመጣ ነገር ነዉ መንግስት ባወጣዉ የግብር ጭማሪ ምክንያት በማድረግ አከራዮች በተከራይ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ በማድረግ ይገኛሉ ስለዚህ መንግስት ራሡን የቻለ ህጋዊ ተመን ማህበረሠቡን በማይጎዳ መልክ ተመን አዉጥቶ ተግባራዊ ቢያደርግ ትልቅ ስራ ነዉ። " - መልከፀዲቅ

" አከራየች እያስጨነቁን ይገኛሉ። እኔ የተከራየሁትን ቤት ጭማሪ ከተከለከለ ጀምሮ 2 ግዜ አስጨምረውኛል አሁንም የካሬው ክፍያ ሳይጀመር ሌላ 2000 ለማስጨመር እየተሯሩሯጡ ነው። " - ታሬ

" እስከ ሰኔ 30 ? ከዛስ በሆላ ነው አከራዮቹም የሚጨምሩት ከሰኔ 30 በሆላ ነው እንጂ አሁንማ ምን ይጨምራሉ ። " - አቤል

" በእኔ በኩል 55% ተጨምሮብኛል አከራየ ጥሩ አቅም ያለው ነው ግን ደላላ መቀመጫ አሳጡት እኔ ስወጣ ለሌላው ማከራየት መቼም በሰው ንብረት ሙጭጭ አይባል " - Mun

" ዋናው መፍትሄ የቤት ኪራይ ተመን ቶሎ ብሎ በዚህ ወር/ከሰኔ 30 በፊት/ በምክር ቤት አፀድቆ ተግባራዊ ማድረግ ነው። ይሄ ነው ዘላቂ መፍትሄው። ለጊዜው ግንቤት ኪራይ መጨመር ወንጀል ሆኖ በፍርድ ቤት መዳኘት አለበት። አንደኛ ሳቦታጅ ነው ሁለተኛ ህግ መጣስ ነው። So ክስ ተመስርቶ በህግ መዳኘት አለበት ኪራይ ሚጨምር እያንዳንዱ አከራይ። ወደፊትም የኪራይ ተመኑ ሲፀድቅ ከተመኑ በላይ መጨመር በተመሳሳይ ወንጀል ሆኖ በፍርድ ቤት ሊያስጠይቅ ይገባል። " - ዘ ዌይ

" የቤት ኪራይ ጭማሬው ጉዳይ አሳስቦናል። የኔ ባለ1 መኝታ ኮንዶሚኒየም 3,000 ብር ጨምር እያሉኝ ነው። ይህ ካሎነ 3 ወር እንሰጣለን ትወጣለህ ብለውኛል። ከዚህ በፊት የወጣው ሕግ አልቋል፣ በሕጉ ምክንያት ምንም ሳንጨምር ቆይተናል። እናም አሁን ግብሩም አለብን ብለው በአንዴ ከሐምሌ 1 ጀምረህ 3,000 ብር ጨምር ብለውኛል። በጣም ተጨካክነናል። " - ስሜ አይጠቀስ


" በጣም የሚገርመው አከራይ ሆሌ መበደል አለበት እሱ ላይ አገሪቱላይ ያለው የኑሮ ዉድነት እሱን አይመለከተውም በቤት ኪራይ ልጅ የሚያሰተምር ሌላም ወጪዎች አሉበት ውነት ነው ከየት አምጥቶ ግብር ሊከፋል ነው አከራይም የዚህች አገር ዜጋ ነው። " - አክሊሉ

" የኔ አከራይ በአመት 24000 ብር ለሆነው ግብር እኔ ላይ ያደረገችው ጭማሪ በወር 6000 ሲሆን ይህ ማለት በአመት 72000 ብር ነው። መንግስት ያወጣው ክልከላን ልጠቀም ብሞክር ከቤት እንደምታስወጣኝም ገልጻልኛለች። መንግስት የአህያ ባል ነው የሆነብን። ምን ማድረግ ይቻላል። የሰማዩን መንግስት አቤት ማለት እንጂ። " - ታዲዮስ

" እያንዳንዱ ጫና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሰዎች ነው ። ነዳጅ ሲጨምር እኛ ቤት ኪራይ ሲጨምር እኛ ነን ሁሉንም። አከራዩንም አትፍረድ ልጅ ሚያስተምር ሚያሳድግ ። ለምግብ ሚሆን ጤፍ አለ እረ ስንቱ ። የአሁኑ ደሞ አበባሰብን ጣሪያና ግድግዳ ሲባል። " - HA

" ምንድነው ሚሉን አንዲጨምሩ ያረጉአቸው ግብር ጨምረው ራሳቸው መጨመር አችሉም ሚሉት ራሳቸው ወይ ምሩን ወይ ፍቱን አታወዛግቡን 😡😡😡😡😡😡😡😡😡😡😡 " - አብዲ

" ከቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ አከራያችን ከ13/10/15 በ 10 ቀን ልቀቁ አለን ። ካልሆነ ከምንከፍለው 6,000 ብር ወደ 20,000 ብር 233% ጭማሪ እንድትከፍሉ ሲል በጠበቃ ቢሮ ጻፉልን ። አሁን ይሄ ነገር እንዴት ይታያል። " - ትሪፕል

" ከቤት ማስወጣትን በተመለከተ አስተዳደሩ የሚያወጣቸው ደንቦች

- ግልፅ አይደሉም፣ኪራይ መጨመር እንደማይቻል ብቻ የሚደነግጉ ናቸው።

- በ አዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ታትመው አይወጡም

-በርካታ ፍርድ ቤቶች አይቀበሏቸውም ።

በዚህ ምክንያት ፍርድ ቤቶች በዚህ አይነት ኬዞች ተጨናንቀዋል።

ከተከሰሱት ውስጥ ፣ እኔም አንዱ ነኝ " - ሴንትኦፍ

" ኤረ የእኛስ ይብሳል መጀመሪያ የውሃና መብራት ራሳችሁ ክፈሉ አሉን ፤ የቤት ክራይ ላይ እንደማይጨምሩ ነግረውን ነበር ሁለት ወር እንኳን አልቆዪም እያንዳንዳችን ላይ ከ1500-2500 ብር ጨመሩብን ወደህግ እንሂድ ስንላቸው አንዳንዶቹ ነገ አዋጁ መነሳቱ አይቀርም ያኔ እላፊ ብጨምሩም መንግስት ምንም ላይል ይችላል አለን ፤ አማራጭ ያኔ ከመጮህ አሁን የተጣለብንን እንክፈል አሉ ። ከዛ ምንም አማራጭም መብትም የሌለን ሆነን እየከፈልን ነው። አሁንስ የመፍትሔ ያለህ ማለት እንፈልጋለን መሃል ካዛንቺስ ሂልተን ጀርባ " - ZE


" የንግዱን ማህበረሰብ ባላውቅም በተለይ አብዛኛው ድሀ ማህበረሰብ የሚጠቀምባቸውን 3በ3/4 የሚያከራዩ ኣከራዮች ኣብዛኞቹ ኣቅመ ደካሞችና ኣዛውንቶች ናቸው ነፃነታቸውን ትተው ኣከራይተው ቢያንስ የሆነ ቀለብ ለማግኘት እየሞከሩ ያሉት እንደዚህ ባለበት ሁኔታ የመጣውን በካሬ የሚሰላ ግብር ብቻቸውን ይከፍላሉ ብሎ ማሰብ ጤነኝነት ኣይደለም መንግስትም ይህ እንደሚመጣ ሳያስበው ቀርቶ ኣይመስለኝም ያለምንም ጥናት ያውም በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንደዚህ ድህነት ውሳኔ የወሰነው ስለሆነም ተከራዮቹ በያዙት ካሬ ልክ ተካፍሎ የሚደርሳቸውን ክፈሉ ማለት ልክ ነው ነገር ግን ከዛ በላይ መጨመር ልክ ኣይደለም 60% ግፍ ነው። " - የሱፍ

" መንግስት ጆሮ ካለው ድምጻችንን አሰሙልን ራሱ ቤት እያፈረሰ ምስኪኑን ህዝቡ አደባባይ ላይ እየበተነ የቤት ኪራዩን ጣሪያ ላይ ሰቅሎታል የሚቀመስ አልሆነም በዚህ ላይ የጣሪያና ግድግዳ ግብር ይዞ መጥቶ ራሳችንን አስጠግተን ወጥተን የምንገባበት ቤት አጥተናል በዚህ ቀጠለ ከባድ ነው እኔ ከ3,000 (ሶስት ሺህ) በላይ ካልጨመርክ ቤቱን ትለቃለህ እየተባልኩ ነውመንግስት የሚሰማ ከሆነ ቶሎ ማስተካከያ ያድርግ! " - ስሜ አይጠቀስ

" የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን በተመለከተ:-

በትናንትናው እለት ኮንዶምንየም ያከራየኝ ሰው በስልክ ደውሎ '' የመንግስት ግብር ስለጨመረብን የቤቱ ኪራይ ዋጋ ጨምረናል '' በማለት በወር 9,000.00 ብር ተከራይቸው የቆየሁትን 4 ኛ ወለል ላይ ያለ ባለ 2 መኝታ ቤት 3,000.00 ብር በመጨመር በወር 12,000.00 ብር መክፈል እንዳለብኝ ተነግሮኛል። እኔም ላስብበትና አሳውቅሀለሁ የሚል መልስ ከሰጠሁት በኋላ፣ ሌላ ቤት ለመከራየት ደላሎችን ስጠይቅ ከ15,000.00 በታች እንደማላገኝ መርዶ ነገሩኝ።

አዲስ አበባ ውስጥ መኖር እጅግ ከባድ ሆኗል።

አዲስ አበባን ለቅቄ ወደ ክፍለ ሀገር ለመቀየር አስቤ፣ ከአ/አ ውጭ የማይታከም ከፍተኛ የጤና ችግር ስላለብኝ ከከተማው ርቄ መኖር አልቻልኩም።

በጣም የሚገርመው ሌሎች ጠባብ የጭቃ ቤቶች ሳይቀር ከሚገመተው በላይ ክራይ ዋጋቸው እጅግ ውድ ነው።

ለማን አቤት ይባላል!?🤔 " - Yom

" መንግስት ዘላቂ መፍትሄ ይስጠን, በግብር ክፍያው ምክንያት የኮንዶሚኒየም የኪራይ ዋጋ የሚቻል አልሆነም አከራዪም ተከራዪም የማይጎዳበትን የዋጋ ተመን ቢያወጣ መልካም ነው " - አሚና

" Dear TIKVAH - ETHIOPIA,

This short note is in reference to your request to share with you my experience of any increase in house rental charges following the imposition of property tax on walls and roofs of buildings including residential houses in Addis Ababa.

Sharing my experience of the situation, the amount I'm paying for house (residential) rental increased by about 30% just 2 months ago. They have added more upon me starting this month, just after 2 months. I calculated the total increase in 3 months time to be around 45%.

it's obvious that house owners will charge renters more than it was before as they are being asked to pay a tax which they didn't use to.

However, the increased charge in rental services seems to be unproportional. " - Sadem

" ሰሚት ፍየል ቤት አከባቢ ያለው የቤት ጭማሪ ልነግራችሁ አልችልም +2 ባለ 4 መኝታ ለ 3 ዓመት በ 18,000 ብር ነበርኩኝ ከ 2 ሳምንት በፊት ግን 45,000 አድርጉት ወይም ቤት ፈልጉ ተብለናል ፤ በጣም ከባድ ነው በዚህ ክረምት ልጆች ይዘን በዚህ ላይ የደረስኩኝ ነፍሰጡር😔 " - መሲ

" በኔ በመኖሪያ ቤቴ 20% ለሚቀጥለው እንዲጨምር ተነግሮኛል " - t

@tikvahethiopia

Report Page