Tikvah Ethiopia
የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) በተጨማሪ ምን አሉ?
ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪ፣ "አንዳንድ አካባቢዎች ት/ቤቶች ራሱ የተፈናቃዮች መጠለያ ሆነዋል። ይህ በአገር ተረካቢዎች ላይ ጫና ይፈጥራል" ሲሉ ተናግረዋል።
"ከጦርነት፣ ከግጭት ጋር ተያይዞ አጠቃላይ ት/ቤቶች ከግጭት ነጻ መሆን አለባቸው የሚል አዋጅ እንዲፈረም እያደረግን ነው" ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ የተፈናቃይ መምህራንን ቁጥር በተመለከተም፣ "አሁን በትክክል መግለጽ ይከብደኛል" ብለዋል።
በአጠቃላይ መምህራን የሚያነሷቸው ቅሬታዎችን በተመለከተ በሰጡት ማረጋገጫ ምን አሉ?
-“በተለይ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ (2 ወረዳዎች) ከደመወዝ ክፍያ፣ ተቆራርጦ ከመከፈል፣ ዘግይቶ ከመምጣት ጋር የሚመጡ ቅሬታዎች አሉ።
-የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ በጀት መዶቦ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው። ደቡብ ኢትዮጵያም ‘ጥረት እያደረግን ነው’ ነው የሚሉት የክልል መንግስታቱ።
-ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ሰሞኑን የተፈጠሩ ቅሬታዎች እንዳሉ መረጃው ደርሶኛል። ከ2 ቀናት በፊት ከትምህርት ቢሮ ኃላፊው ጋ አውርቻለሁ። ‘መፍትሄ እያበጀን ነው’ ብሏል። ጥረቶች አሉ፣ ክፍተቶች አሉ፣ ቅሬታዎች አሉ።
-#በትግራይ ክልልም የእኛ ተወካዮች ከዚህ ተልከው ቅሬታዎችን ሰምተዋል። በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ችግሮች እንዳሉ ይታወቃል። ቅሬታቸው ይደመጥ ነው የምንለው። አንዳንድ የማያጋጥሙ ነገሮች አሉ ለመፍትሄው እየጣርን ነው።
Q መምህራኑ ለሚያነሷቸው ቅሬታዎች ለመፍታት ማኀበረዎ ምን እየሰራ ነው?
*ማኀበሩ ጥረት እያደረገ ነው። 700 ሺሕ አባላት አሉት። በየክልሎች ጭምር ዓመታዊ መድረክ አለው። የመማር ማስተማር፣ የትምህርት ጥራት ችግር፣ በመልካም አስተዳደር፣ የሰላም ጉዳዮችን አጀንዳ ቀርጾ ይወያያል።
*መፍትሄዎች እንዲመጡም የሚደረጉ ጥረቶች አሉ። ሳይቋረጡ ይቀጥላሉ። በተለይ አንገብጋቢ የሆኑ ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ትኩረት እንዲሰጡ እየሰራ ነው" ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia