Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ኮሪደር ስራ ምንድነው ? አሁን ያለበት ደረጃስ ምን ይመስላል ?

አጭር መረጃ ስለ ኮሪደር ልማቱ ፦

☑ 48.7 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል።

☑ የተመረጡ 5 ኮሪደሮች ላይ ነው የልማት ስራ ያለው።

☑ ከ4 ኪሎ - ፒያሳና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ፣ ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ መገናኛ ፣ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ ፣ ከ4 ኪሎ መስቀል አደባባይ ቦሌ ድልድይ ፣ ከቦሌ ድልድይ በመገናኛ እስከ አፍሪካ ኮንፌሽን ኮሪደር ልማቱ ያካልላል።

☑ ስራዎቹ 24/7 የሚሰሩ ሲሆን ብዙ ቦታ መሰረታዊ ስራዎች አልቀዋል። 

☑ 16000 ሰዎች ስራ እድል አግኝተዋል።

የኮሪደር ልማቱ ፦ መንገዶችን ማስፋት፣ የመንገድ ዳሮችን ማሳመር ፣ የእግረኛና የሳይክል ብስክሌት መሄጃዎችን መስራት፣ ፕላዛዎችን መስራት ያጠቃልላል።


ከሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስራውን ከከተማው አመራሮች እና ከስራው መሪዎች ጋር ግምገማ አድርገው ነበር።

በዚህ ወቅት ምን ተባለ ? ስራው ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?

#ኮሪደር1

(4 ኪሎ - ቀበና - ኬንያ ኤምባሲ - መገናኛ)

አቶ ጃንጥራር አባይ፦

- ከ4 ኪሎ ቀበና ኬንያ ኤምባሲ ያለው 2.5 ኪ/ሜ ነው ፤ ከኬንያ ኤምባሲ መገናኛ ታችኛው ያለው 2.3 ኪ/ሜ ነው ፤ በላይ እስከ ሳውዝ ጌት ያለው 8.03 ኪ/ሜ ነው። ድምሩ 10.26 ኪ/ሜ ነው።

- ቴሌ፣ መብራት ፣ውሃ መሰረተ ልማት የሚነሱ 100% ተነስተው እንዲዘዋወሩና ወደ ግራውንድ እንዲገቡ የማድረግ ስራ ከሞላ ጎደል ተሰርቷል። 100% የፍሳሽ ማስወገጃዎች ግራውንድ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው።

- በኮሪደሩ 557 ተነሺ መኖሪያ ቤቶች አሉ። በመንገድ የሚያልፉት 100% ተነስተዋል። ሌሎች ተነስተው የሚለሙ ካለው አቅም አንጻር ሙሉ በሙሉ አልተነሱም፤ ለሌላ ጊዜ እንዲቆዩ ተደርጓል።

- 45 የፌዴራል ቤቶች መንገድ የሚነካቸው አሉ 12ቱ ተነስተዋል። የንግድ ቤቶች 5 አሉ 3ቱ ተነስተዋል። 

- የቀበሌ ቤቶች 700 ተለይተዋል። ዕጣ ያወጡ 246 አሉ። 130 ቤት ተረክበዋል። መንገድ ላይ ያሉት ሁሉም ተረክበዋል። የቀበሌ ንግድ ቤቶችም 100% ተነስተዋል።

- የግል ቤት ያላቸውና ተስማምተው ለመነሳት የወሰኑ መሬት ለማግኛት ዕጣ አውጥተው መተማመኛ ተሰጥቷቸው የወጡ አሉ። አንዳንዶች መሬት እስኪዘጋጅ እየጠበቁ ነው። 

- የመንገድ ጠረጋ ፣ ማጽዳት 98% ተሰርቷል። 

- 4,500 ካ/ሜ ላይ ያረፈው 4 ኪሎ ፕላዛ 32.6% ተሰርቷል። 

- የከርቭስቶን ግንባታ 49,393 በሜትር መሰራት አለበት 5,319 ነው የተሰራው 10.7% ነው።

- የጎርፍ ማስዋገጃ ስራዎች ከ4 ኪሎ እስከ ኬንያ ኤምባሲ ድረስ አብዛኛው አልቋል።

- የባይክ መንገድ 10.26 ኪ/ሜ ነው። ከዚህ ስራ 9.13% ላይ ነው። 

- ባለቁ ቦታዎች የአረንጓዴ ስራዎች ተጀምረዋል። 

- የእግረኛ ድልድይ ፣ አንድ ቦታ የመኪና ፓርኪንግ አለ ገና ዲዛይን ላይ ነው። 

- 13 የአውቶብስ ቤይ አለ ፤ 14 የታክሲ ቤይ (9ኙ በጋራ ማስተናገጃ ነው) ፣ 4 ብቻውን የአንበሳ ቤይ አለ 5 የታክሲ ብቻ ቤይ አለ ከመንገዱ ጋር እየተሰሩ ነው።

☑ አጠቃላይ የመንገድ ስራው ከ42% በላይ ነው።


#ኮሪደር2

(ቦሌ VIP - እስጢፋኖስ - 4 ኪሎ)

አቶ ሞገስ ጥበቡ ፦

- ከቦሌ VIP እስከ እስጢፋኖስ 4 ኪሎ ያለው ኮሪደር 8 ኪ/ሜ ይፈጃል። 

- 12 ዲዛይኖች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል። ወደ ስራም ተግብቷል።

- ከታለመላቸው ዓላማ ውጭ ለፓርኪንግ ተብለው የተሰሩ ግን ለሱፐር ማርኬትና ለሌላ ዓላማ አውለው የነበሩትን ወደ ፓርኪንግ እንዲመለሱ እየተሰራ ነው።

- ከCCTV ካሜራና ብልህ ትራንስፖርት ጋር የሚረዱ 3.2 ኪ/ሜ ኬብል ዝርጋታ በኢትዮ ቴሌኮም እርዳታ እየተሰራ ነው።

- 4.6 ኪ/ሜ ርዝመት ነው ከቦሌ እስጢፋኖስ ያለው 40 ሜትሩን ወደ 50 ሜትር እየሰፋ ነው። 90% የወሰን ማስከበር ስራዎች አልቀዋል። 

- በግራና በቀኝ ሳርና ዛፍ የሚተከልበት ቦታ አለ። እሱም እየተሰራ ነው።

- በርካታ ፓርኪንጎች ብዙ ቦታ ታቅደዋል። አንዱ ተጀምሯል። 

- እዚሁ ሀገር ውስጥ 5 ኢንዱስትሪዎች ተመርጠው ፖል እያመረቱ ነው። ግራናይት የማንጠፍ ስራም በስኬት እየተከናወነ ነው (በሀገር ውስጥ አምራቾች) ። 

- እስከ ግንቦት አጋማሽ ድረስ አጠቃላክ ስራው ያልቃል።


#ኮሪደር3

(ቦሌ ኤርፖርት - መገናኛ - ሲኤምሲ)

አቶ ጥራቱ በየነ ፦

- ከቦሌ ኤርፖርት እስከ መገናኛ ከመገናኛ እስከ ሲኤምሲ የሚያጠቃልል ኮሪደር ነው።

- ኮሪደሩ የሚናካቸው የቀበሌ ቤቶች ተተኪ ቤት እንዲያገኙ በማድረግ እንዲነሱ ሆነዋል። 

- የንግድ ቤቶች ምትክ መስጠት፣ ካሳ ክፍያ የመሥጠት ስራ እየተሰራ ነው። በኮሪደሩ ካሉ 47 ቦታዎች 27 ቦታ ምትክ ተሰጥቷል።

- ከቦሌ - መገናኛ መንገድ አዲስ ድሬኔጅ ዝርጋታ እየተሰራ ነው። 4700 ሜትር ዝርጋታ የነበረ ሲሆን 3600 ዝርጋታ አልቋል።

- የኤሌክትሪክ እና ቴሌ መስመር ዝርጋታዎች ዝርጋታ እየተካሄደ ነው።

- የመኪና ማቆሚያ፣ የአውቶብስ ታክሲ ፌርማታ ስራዎች አብረው እየተሰሩ ነው። 23 የታክሲና የባስ ፌርማታዎች አሉ።

- የአፈር ቆረጣ ብዙ ስራ አለ። እያለቀ ነው። 

- ፒቪሲ ቀበራም እያለቀ ነው።


#ኮሪደር4

(ሜክሲኮ - ሳር ቤት - ጎተራ - ወሎ ሰፈር አደባባይ)

አቶ ሞገስ ባልቻ ፦

- ከሜክሲኮ ሳር ቤት ከሳር ቤት በጎታራ ወሎ ሰፈር አደባባይ የሚያካልል ኮረደር ነው። 

- ከሜክሲኮ - ሳር ቤት ዋና ዋና የመንገድ ስራው አልቋል። በሁለቱም በኩል ግሪነሪ ስራ እያለቀ ነው። የባይክ መንገድ ፣ የታይልስ ንጣፍ አልቋል። 

- በሜክሲኮ - ሳር ቤት ኮሪደር 3 የህዝብ መጸዳጃ ቤት የተለያየ ቦታ ላይ አለ፤ በ1 ሳምንት ያልቃል። 

- እስከ ሳር ቤት የታክሲ እና ባስ ተርሚናሎች አሉ። የባስ ተርሚናሉ የወሰን ችግር ስላለ በቀጣይ ያልቃል። 

- ከጎተራ - ወሎ ሰፈር አብዛኛው የፈረሳ ፣ የአርኬድ ስራዎች አልቀዋል። ጊዜ እየወሰደ ያለው ወሎ ሰፈር መከላከያ ጋር ያለው 640 ሜትር የሬቴኒግ ዎል ስራ ነው (እስከ 8 ሜትር ወደላይ ከፍታ ያለው)።

- ሜክሲኮ ካፌ ጋር ፕላዛ ስራ አለ፤ በአንድ ሳምንት ያልቃል። AU ጋር ያለው ፕላዛ አብዛኛው አልቋል በ 15 ቀን ይጠናቀቃል።

- ሳርቤት ጋር በአንድ ባለሃብት አማካኝነት ፕላዛ እየተሰራ ይገኛል።

☑ በአጠቃላይ ኮሪደሩ እስከ ግንቦት 30 ሙሉ በሙሉ ያልቃል።


#ኮሪደር5

(አራዳ አድዋ ዙሪያ)

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፦

- አራዳና አድዋ ዙሪያ ኮሪደር አንዱ ፕሮጀክት ነው።

- ከ4 ኪሎ አደባባይ እስከ ቸርችል ጎዳና በሁለት ተከፍሎ እየተሰራ ነው። 

- እስከ ራስ መኮንን ድልድይ ያለው በራስ ኃይል እስከ ቸርችል ያለው በኮንትራት እየተሰራ ነው። 

- ከራስ መኮንን ድልድል ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በእሳት አደጋ ፅ/ቤት የሚወጣው ፣ ከሲኒማ አምፒር ወደ ሚኒልክ አደባባይ ቀጥታ የሚሄደው ፣ በሀገር ፍቅር አድርጎ ወደ ሚኒሊክ አደባባይ የሚወጣ መንገድ አለ ይሄ ሁሉ ከ4 ኪሎ ፒያሳ ባለው ያለ ነው።

- አዲስ መንገድ ከቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን የሚመጣው እንዲሻሻል ተደርጎ በአራዳ ክ/ከተማ በኩል ሆኖ ቀጥታ ሲኒማ ኢምፓየር ፒያሳ የሚገጥም አለ። በታች በቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም ወደ ጣይቱ ሆቴል የሚሄድ ነው።

- ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ያለው ኮብል ወደ ስታንዳርድ መንገድ እንዲመጣ እየተደረገ ነው።

- ፓርኪንግ እና ታክሲ ተርሚናል ደጎል አደባባይ ጋር ይሰራል። ሚኒሊክ አደባባይ ጋር ትልቅ የባስ ተርሚናል መሬት ውስጥ የሚገባ ይሰራል። ሁለቱም ፕላዛ አላቸው ከላይ።

- 4 ኪሎ ጋር የመኪና ማቆሚያና የታክሲ ተርሚናል ብቻ ይሆናል።

- ከ70 ደረጃ ቀጥታ መጥቶ በወንዙ ተሻግሮ በመስታወት (glass) ድልድይ ለእግረኛ ዎክ ማድረጊያ ይሰራል። እገረኛ ወንዙን በመስታወት ድልድይ እንዲሻገር ይደረጋል። 

- ከቅድስተ ማርያም የሚመጣው መንገድ ወደ ውስጥ 25 ሜትር የሆነ ርዝመቱ 120 ሜትር የሆነ ድልድይ አለው። ወንዙ ላይ ተደርሷል የድልድይ ስራው ቁፏሮ ላይ ነው።

- ፒያሳ ውስጥ ውስጡን የፍሳሽ መስመር እየተሰራ ነው።

- የህንጻ እድሳትም እየተካሄደ ነው።

- በዚህ ኮሪደር 70 የህዝብ ማጸዳጃ ቤቶች ተካተዋል።

- ከመኖሪያ ቤት ወጥቶ ያልተስተናገደ የለም። 1.3 ቢሊዮን ብር ካሳ ተከፍሏል። 20 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ ለተነሺ ተተክቷል።

- ደህንነት ካሜራ፣ ፍሳሽ፣ መብራት፣ ቴሌኮም ፣ ብልህ ትራንስፖርት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

- መብራት፣ ቴኬሎም ፣ ፍሳሽ መሬት ውስጥ በመቀበራቸው አይታዩም።

- ከ4 ኪሎ እስከ ራስ መኮንን በሳምንት ያልቃል። ከደጎል ወደ አብርሆት የሚመጣው በ2 ሳምንት ያልቃል። ከአራዳ ህንጻ ፊትለፊት እስከ ቴድሮስ አደባባይ ከዛ ቤተመንግስት የሚመጣው 2 ሳምንት ይወስዳል። 

- ተርሜናል፣ ፕላዛ፣ የውሃ ፋውንቴኖች፣ ፓርኪንግ ፣ የባስ ተርሚናል ስራ ሙሉ በሙሉ እስከ ሰኔ መጨረሻ ያልቃል።

- ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ላይ የተነሳው የቤተክህነት ህንጻ ግንባታን ተጀምሯል። በፍጥነት ያልቃል።

- በስራው 5 ኮንክራትክተሮች ፣ 50 ማህበራት (ማፍረስ ፣ ታይልስ በመስራት፣ ታይልስ በማቅረብ፣ ቤት በማደስ) ፣ በሰው ቁጥር 1,403 ቋሚ ስራ አግኝተዋል። 12,875 ሰዎች ጊዜያዊ ስራ አግኝተዋል። በአጠቃላይ 14,275 ሰዎች ስራ ማግኘት ችሏል።

ℹ በአጠቃላይ በ5ቱ ኮሪደር ስራ 16,000 ሰዎች ስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ በስራዎች ላይ ፍጥነት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

" ክረምት እየመጣ ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራዎች ይፋጠኑ ሲሉ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

" የከተማው ህዝብ ዝም ያላችሁ ስላልተጎዳ አይደለም፤ ሱቁ ስላልተዘጋበት አይደለም ፤ ዝም ያላችሁ ሃሳባችሁን እና ስራችሁን አይቶ ነው። በየአደባባዩ ሲያያችሁ ይሄ የለበጣ ነገር አይደለም ስራ ነው ብንታገሳቸው የሚል ነገር በውስጡ ስላለው ነው እንጂ የተጎዳው ነገር ስለሌለ አይደለም " ብለዋል።

ነዋሪው ዝም ያለው ስላልተጎዳ ሳይሆን የሚሰራውን ስራ አይቶ እንታገሳቸው ብሎ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ሁሉ የሚሰራው ስራና ድካም ግን የከተማው ጽዳት እንዲጠበቅ ካልተደረገ ዋጋ አይኖረም ሲሉ ገልጻዋል።

የከተማው ጽዳት ለመጠበቅ በሀገር ደረጃ (አሁን በአዲስ አበባ) የመጸዳጃ ቤቶችን የመገንባት " #ጽዱ_ኢትዮጵያ " የተሰኘ ዘመቻ መጀመሩን ገልጸዋል።

በዚህም ቢበዛ 100 መጸዳጃ ቤቶች እንደሚሰራና የስራ እድል ፈጥሮ እንዲስፋፋ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

የከተማው ህንጻዎች እና ህንጻዎችን የሚሰሩ ባለንብረቶች የመጸዳጃ ቤቶችን ክፍት የማድረግ ግዴታ አለባቸው ብለዋል።

" አንድም ብር ሁለትም ብር የከፈል ችግር የለው። ሰው ግን ከፍሎ መጠቀም መቻል አለበት " ሲሉ አክለዋል።

አሁን ላይ ብር እየተዋጣ መሆኑን በቀጣይ ቦታ እንደሚለይና ኮንትራት ወጥቶ እንደሚሰራ አሳውቀዋል።

NB. የገንዝብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልግ (የጽዱ ኢትዮጵያን ቻሌጅ መቀላቀል የሚፈልግ) ዜጋ ሁሉ በንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር 1000623230248 (ጽዱ ኢትዮጵያ) ላይ ድጋፍ ማድረግ ይችላል ብለዋል።

#TikvahEthiopia

#TikvahEthiopiaAddisAbaba

@tikvahethiopia

Report Page