Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


#Update

ኦክሎክ ሞተርስ “ስሜን አጥፍቷል” ላለው ቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ምን ምላሽ ሰጠ ?

“ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር (ኦክሎክ ሞተርስ) ተሽከርካሪ ለማስመጣት “ ከ40 በላይ ከሚሆኑ ተለያዩ ሕጋዊ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ” ጋር ውል ገብቶ እንደነበር፣ በውሉ መሠረት ለማኀበራቱ አባላት ተሽከርካሪዎችን እንዳላስረከበ የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 በሰጠው መግለጫ አስውቆ ነበር።

የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት፣ “1.2 ቢሊዮን የምስኪን ሕዝብን ገንዘብ 4 ዓመታት ሙሉ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ እየተጠቀመበት ነው። በውላችን መሠረት መኪና አላስረከበንም ” ሲሉም ወቀሳ ማቅረባቸው ይታወቃል።

የማኀበራቱ ኃላፊ አቶ ግዑሽ መብራህቶም በወቅቱ በሰጡት ቃል፣ “ ከ2012 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ በሚባል ድርጅት መኪና ያስገባል ወይም ገጣጥሞ ይሰጠናል በሚል ነው የነበረን ሂደት። ነገር ግን በዚህ መሠረት መኪናውን ማስረከብ አልቻለም” ማለታቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

ይሁን እንጂ ማኀበራቱ ይህን ቢሉም ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ በወቅቱ ለተነሳበት ቅሬታ ምለሽ እንዲሰጥ ስልክ ባለማንሳቱ፣ የፅሑፍ ጥያቄ ቢላክለትም በወቅቱ ምላሽ ባለመስጠቱ ምላሹን ማካተት አልተቻለም ነበር።

ይህ በእንዲህ እያለ ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር በበከሉ፣ በቱሪስት ታክሲ ማኀበራትን መግለጫ አስመልክቶ ሐሙስ መጋቢት 2016 ዓ/ም ቃሊቲ በሚገኘው መ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ " የስም ማጥፋት ዘመቻ ተፈጽሞብኛል " በማለት ኮንኗል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማኀበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁንን የድርጅቱ ስም ጠፋ ያሉበትን ምክንያት ጠይቋል።

አቶ ታመነ ካሳሁን ፦

“ ‘ሕዝቡ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ድሃዎችን እያስለቀሰ ነው። 1.2 ቢሊዮን ብር ወስዶ እየሰራበት ነው’ የሚለው በሕዝብም በመንግሥትም ዘንድ ተቀባይነት እንድናጣ ለማድረግ የተደረገ ሩጫ ነው። ” ብለዋል።


ቱሪስት ታክሲ ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላከውና ኦክሎክ ሞተርስ በውሉ መሠረት ተሽከርካሪዎችን እንዲያስረክባቸው የሚጠይቀው ደብዳቤ ፤ ኦክሎክ በተሽከርካሪዎች ላይ የሚያደርገው የዋጋ ጭማሪ ለተለያዩ ኪሳራዎች እየዳረገው መሆኑን በመጥቀስ ይከሳል።

ደብዳቤው አክሎም፣ “ ይህ የሚሆነው ደግሞ ከዚህ ቀደም እኛ ክፍያ ከከፈልነው ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘባችን፣ ትርፍ ሆነ ወለድ በማናገኝበት ሁኔታ በመሆኑ ጉዳዩን የከፋ የሚያደርገው ሲሆን፣ መንግሥት፣ ህግና ተጠያቂነት ባለበት አገር ላይ ድርጅታችሁ ኦክሎኮ ጀነራል ትሬዲንግ ግን በማን አለብኝነት በመንቀሳቀስ ክህደትና ማጭበርበር እየፈጸመብን እንደሆነ እንዲሰማን አድርጎናል ” ይላል።

ለዚሁ የደብዳቤ ቃል ምላሽ እንዲሰጡ ተጠይቀው አቶ ታመነ ካሳሁን በሰጡት ቃል ፦

“ እነዚህ ሰዎች (1.2 ቢሊዮን ከፈሉ የተባሉት) የከፈሉት 110 ሚሊዮን ብር ነው። ያመጣነው መኪና ግቢ ውስጥ እንኳ የቆመው ብቻ 200 መኪና ነው። 200 መኪና በትንሹ እንኳ በ1 ሚሊዮን 950 ሺሕ ብር ስናባዛው ከ400 ሚሊዮን በላይ ነው። ስለዚህ የዛን ያህል ዋጋ ከፍለን ስናመጣ እኛ ከእነርሱ (ከማኀበራቱ) የተቀበልነው ገንዘብ ግን ያን ያህል (110 ሚሊዮን ብር) ነው ” ብለዋል።

አክለውም ፦“ ደብዳቤ ነው የጻፉት እንጂ ያስገቡት ደረሰኝ ግን የለም ” ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ ቱሪስት ታክሲ 1.2 ቢሊዮን ብር እንደከፈሉ የሚያስረዳ ደብዳቤ ሲልክላችሁ እናንተ (ኦክሎክ) ምን ምላሽ ሰጣችሁ ? ሲል ጠይቋል።

አቶ ታመነ በምላሻቸው ፦

“ ‘1.2 ቢሊዮን ብር ነው የከፈልነው ተወክለንበታል’ ላሉትማ ይህንን አይነት ውክልና የላችሁም ብለን አሁን በምልክልህ አንድ ደብዳቤ መልስ የሰጠናቸው አለ ” ያሉ ሲሆን፣ የላኩት ደብዳቤ ከታክሲ ማኀበራት አቶ ግዑሽ መብራህቶም ለማኀበራቱ ውክልና እንደሌላቸው ያትታል።

ስለ 1.2 ቢሊዮን ብር ከሚያወሳው ደብዳቤ በተጨማሪ 1.2 ቢሊዮን ብር የተከፈለበትን ደረሰኝ እንዲያቀርቡ የተጠየቁት አቶ ግዑሽ መብራህቶም (ከቱሪስት ታክሲ ማኀበራት) በበኩላቸው፣ የተወሰኑትን ልከው የተወሰኑት ገና ከማኀበራቱ እየተሰባሰቡ እንደሆነ ከመግለጽ ውጪ ሙሉ ደረሰኝ አልላኩም።

በሌላ በኩል ቱሪስት ታክሲ ማኀበራት ከኦክሎክ ጋር ውል የገቡት በ2012 ዓ/ም መጨረሻ እንደሆነ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ተናግረው የነበረ ሲሆን፣ ኦክሎክ ለቲክቫህ በሰጠው ምላሽ ከእነርሱ ጋር ውል የገባው በ2015 ዓ/ም ታህሳስ ወር ላይ እንደሆነ ገልጾ ፣ “ 2012 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ውል ተዋዋልን የሚለው ጉዳይ ከሄሎ ታክሲ ጋር ተዋውለው ሊሆን ይችላል። ከእኛ ጋር ግን የተዋዋሉት ውል የለም ” ብሏል።

በተጨማሪም ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ኦክሎክ ከሄሎ ታክሲ ጋር የነበረው ውል ምንድን ነው ? ለምን ተቋረጠ ? የቱሪስት ታክሲ ማኀበራት አባላት “ኦክሎክ በስማችን የመጣውን መኪና እየሸጠ ነው” ማለታቸው በተመለከተ ያለዎት ምላሽ ምንድን ነው ? ሲል ለአቶ ታመነ ላቀረበው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፦

- “ 2012 ዓ/ም ላይ ከእኛ ጋ መኪና ለመግዛት ውል ተዋውሏል (ሄሎ ታክሲ)። በውላችን መሠረት ወደ 447 መኪና (SKD የሚባሉ) አገር ውስጥ አስገብተናል። ይህንን ስናስገባ ሄሎ ታክሲ መውሰድ አልቻለም። ምክንያቱም ቀረጥ ነፃ ስላልተፈቀደለት። መኪናዎቹ ደግሞ ከእነ ቀረጡ ነው የሚሸጡት። 

- ስለዚህ ከቱሪስት ታክሲና ከሄሎ ታክሲ ጋር አሁንም እየተምታታ ያለው ብዬ እያልኩ ያለሁት፣ ሄሎ ታክሲ ጋር የመጣው መኪና ከነቀረጡ የሚሸጥ ነው። SKD ነው። እነዚህ ሰዎች (ማኀበራቱ) ደግሞ ከገንዘብ ሚኒስቴር ቀረጥ ነጻ የተፈቀደላቸው ታህሳስ 2015 ዓ/ም ነው። ቀረጥ ነፃ ቢፈቀድም በCKD ነው፣ በSKD አልተፈቀደላቸውም። 

- እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋ ሲዋዋሉ CKD የሆነ መኪና ከእኛ ለመግዛት ነው የተዋዋሉት። ሄሎ ታክሲ ግን የተዋዋለው SKD መኪና ከእኛ ጋ ለመግዛት ነው። ስለዚህ አገር ውስጥ ገብተዋል። ግን መኪናዎቹን መውሰድ አልቻለም። መኪናዎቹ ከእነቀረጡ እየተሸጡ ነው።

- አሁን እየሸጥን ያለነው (መስቀል ፍላወር Show room አለን) መኪናዎቹ ምን አይነት ናቸው ተብሎ መጥቶ ማየት ይቻላል። መኪናዎቹ (መስቀል ፍላወር የሚሸጡት) CKD እንዳልሆኑ፣ SKD እንደሆኑ፣ ከ3 እና 2 ዓመታት በፊት የተገዙ እንደሆኑ እነርሱ (ማኀበራቱ) ጠንቅቀው ያውቃሉ” ብለዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia

Report Page