Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


“ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራሉ” - ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኀበር

ኦቲዝምና ዳውንሲንድረም ያለባቸውን ልጆት የትምህትና ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን የሚሰጡ አምስት ማኀበራት፣ ማህበረሰቡ እንዲህ አይነት የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ልጆች ያለው አመለካከት በፍረጃ የተሸበበ መሆኑን፣ መንግሥትም ለዘርፉ የሚገባውን ትኩረት እንዳልሰጠ ገልጸዋል።


ከማኀበራቱ መካከል የብሩክ ኢትዮጵያ የእድገት ውስንነት ያለባቸው ማዕከል መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ናርዶስ አሰፋ ባደረጉት ገለጻ፣ “እኔ መጀመሪያ ትልቅ ግቢ ተከራይቼ ሁሉ ነገር ተሟልቶ የበር። አቅም እያጣሁ ስመጣ ግን የቀበሌ ኮንዶሚኒየም ተከራይቼ ነው አሁን እያስማርኩ ያለሁት” ብለዋል።


ለምን ማኀበሩን ከአዲስ አበባ ውጪም አታስፋፉትም ተብሎ ለቀረበ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ “አይደለም ከከተማ ውጪ ለመክፈት እዚህ ያለውንም እያቃተኝ ነው ያለው። መንግሥት፤ እኛ ጋ የመሬት ችግር የለብንም አይደል እንዴ! ግን ለእኛ ሥራ ሲሆን መሬቱ በጣም ጠበበ¡፣ እንጂ በሌላ ስናይ በሽ ነው። እንደ ጉድ ነው የሚያገኙት። ግን እንዲህ አይነት ሥራ የምንሰራ ሰዎች ብርቅ ነው የሆነብን” ሲሉ ወቅሰዋል።


በዘርፉ ዙሪያ ይበልጥ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ተግዳሮቶችን በተመለከተ ገለጻ እንዲያደርጉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኀበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ በበኩላቸው፣ “እንደ አገር የአዕምሮ እድገት ወስንነት ችግር ያለባቸው ዜጎች ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ የሚያጋጥማቸው ዋናው የግንዛቤ ችግር ነው” ብለዋል።


“በዚህ ግንዛቤ እጥረት ‘ከአምላክ ቁጣ፣ ከኀጢያት፣ ከእርግማን የመጣ’ ብለው የሚያስቡ ሰዎች ልጆቹን እንደሰው እንዳይቆጥሯቸው ምክንያት ሆኗል። ይሄ ደግሞ በእቅድና በትግበራዎች ላይ እኩል ተጠቃሚ እንዳይየሆኑ ማነቆ ይሆናል። ምክንያቱም እዛ እቅድና ቀረጻ ላይ በኃላፊነት የሚቀመጥ አንድ ሰው የግንዛቤ ማነሱን የያዘ የማኀበረሱቡ አንድ አካል ነው” ሲሉ አክለዋል።


ይህ የግንዛቤ እጥረት ልጆቹ የትምህርት ተደራሽነት፣ እኩል የሥራ ተጠቃሚነት እንዳያገኙ እንደሚዳርግ አስረድተው፣ “ለምሳሌ የእኛ አገር የሥራ ቅጥርን ብናየው አሳንና ጦጣን ዛፍ ላይ ውጡ የማለት አይነት ነው” ሲሉ የሁኔታውን አስቸጋሪነት አስረድተዋል።


ከሌሎች ዜጎች ጋር እኩል የሥራ እድል ለመግኘት ደግሞ መማር እንዳለባቸው፣ ለመማር ደግሞ በትምህርት ተደጋፊ እንዳልተደረጉ፣ ትምህርት ቤት የገቡት እንኳ Quality service እንደማያገኙ፣ በዘርፉ የትምህርትና የአካል መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ ከፍተኛ እጥረት በመኖሩ ድጋፉን ማግኘት እንዳልቻሉ አብራርተዋል።


የአዕምሮ እድገት ውስንነት እድገት ውስንነት ያለባቸው መርጃ መሳሪያዎችና Artistic Device የሚባሉት ምን ምን ናቸው? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ወ/ሮ ምህረት በሰጡት ቃል፦


*ለትምህርት የሚረዱ ስዕላዊና የድምጽ መግለጫ

*የፊደሎች መገጣጠሚያ ፐዝል

*ለማስተማሪያነት የሚረዱ ኦዲዮ ቪዡዋላይዝ 

*የማስታወስ ብቃታቸውን ማስታወሻ 

*የሚረብሹ ድምጾች ሲኖሩ መከላከልያ 

*መድኃኒታቸውን ሊያስቀምጡባቸው የሚችሉ 

*ውስንነቱ ያለባቸው ልጆች ለሚያጋጥሟቸው የአካል ጉዳቶች የሚረዱ ለየት ያሉ ዊልቸሮች 

እንዲሁም የአካል ድጋፍን በተመለከተ በተግባቦት ወቅት ለመናገር ተቸግረው ዋጥ የሚያደርጓቸውን ፊደሎች በመተካት ድምጽ የሚመላለሱባቸው በኪቦርድ መልክ የተቀመጡ Artistic Devices ዋና ዋናዎቹ መሳሪያዎች መሆናቸውን በዝርዝር ገልጸዋል።


እነዚህ መሳሪዎች የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ዜግች እንደሚያስፈልጉ ለጤና ሚኒስቴር ከዚህ በፊት አሳውቀው እንደነበር ያስታወሱት ወ/ሮ ምህረት፣ “ከውጪ ነው የሚመጡት ከእኛ አገር እየተመረቱ ስላልሆነ። የትምህርት መሳሪያዎችም Even ተገዝቶ እንኳ ማግኘት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነው ያለነው ኢትዮጵያ ውስጥ” ሲሉ አስረድተዋል።


“አብዛኛዎቹን የምናገኛቸው ሊጎበኙን ከውጪ የሚመጡ ሰዎችን በመለማመጥ በሻንጣ እንዲገቡ በማድረግ ሥራ ነው። ግን በዛ ደረጃ መሆን የለበትም። ይህ በሕይወት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ከቀረጥ ነጻ ገብቶ መከፋፈል የሚችልበትን አማራጮች ማግኘት የምንችልበትን መንገድ መንግሥት ሊያግዘንና ስትሪቴጂዎይ፣ ፓሊሲዎችም ተቀርጸው የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችን ልንደግፍበት የምንችል መሳሪያ ማግኘት ግድ ነው” ብለዋል።


በኢትዮጵያ ምን ያክል የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች አሉ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ወ/ሮ ምህረት፣ በቅርብ ጊዜ ገና አንድ መረጃ ሊወጣ መሆኑን ጠቁመው፣ ከዚህ በፊት ባለው መረጃ “ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራሉ። ካለንበት ግጭት አንጻር የአካል ጉዳት ሊጨምር ስለሚችል ዘቅርብ ጊዜ የሚወጣው ቁጥር ደግሞ ከዚህ እንደሚጨምር ያስገነዝባል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘገባውን ያጠናቀረው፣ 12 የሚሆኑ ዳውንሲንድረምና ኦቲዝም ያለባቸው ልጆችን ትምህርትና ሌሎች ስልጠናዎች እያንዲዪገኙ የሚያደርጉ ማኀበራት “ድምጻችንን በጋራ እናሰማ” በሚል ኀብረት ፈጥረው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለዘነጠኛ ጊዜ እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም የሚከበረውን የዳውንሲንድረም ዓመታዊ በዓል አስመልክተው ከኀብረቱ መካከል የተገኙት አምስት ማኀበራት ዓርብ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም በስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ታድሞ በነበረበት ወቅት ጥያቄዎችን በግሉ ጭምር በለማንሳት ነው።


ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ/ም


ኦቲዝምና ዳውንሲንድረም ልዩነት አላቸው?


በነህሚያ ኦቲዝም ማዕከል የሥነ ልቦና ባለሙያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ጌትዬ ኦቲዝም እና ዳውንሲንድረም ልዩነታቸውንና ምንነታቸውን በተመለከተ በሚከተለው መልኩ ማብራሪያዎችን እንካችሁ ብለዋል።


“ልዩነት አላቸው፣ ልዩነትም የላቸውም ብዬ መጀመር እችላለሁ” ያሉት የሥነ ልቦና ባለሙያው፣ “ኦቲዝም ከአዕምሮ እድገት ጋር የተያያዘ፣ ውስብስብ የሆነ ከነርቭ ስረዓት ጋር የተያያዘ ችግር ነው” ሲሉ አስረድተዋል። 


በየትኛው የዕድሜ ክልል እንደሚጀምር በሰጡት ማብራሪያም፣ ከሁለት ዓመታት በኋላ የሚታወቅ የአዕምሮ እድገት እክል ነ። ብዙ ጊዜ እኛ Define የምናደርገው፣ Neo development mental disorder የሚል ማብራሪያ ስላለው በነህሚያ” ብለው፣ አክለው በሰጡት ቃልም፦


*“ኦቲዝም ብዙ ጊዜ የሚለየው #በባህሪ፣ #በተግባቦት ክህሎቶቻቸውና በሚያሳዩከቸው ነገሮች ናቸው እንጂ ምንም አይነት አካላዊ ምልክት የላቸውም። ኦቲዝም በአብዛኛው #ወንዶችን የሚጎዳ (ከአምስቱ ልጆች 4ቱ ወንዶች፣ አንዷ ብቻ ሴት ሆና የምርመራ ውጤታቸው የሚያሳውቅ ነው።


*አዛዛኛውን ጊዜ ኦቲዝምን ለመለየት ከአንድ ዓመት ከስምንት ወር አስከ ሦስት ዓመታት ድረስ መጠበቅ ሊኖርብን ይችላል። ከዚያ በፊት የመታወቅ ዕድሉ በጣም ጠባብ ነው” የሚል ማብራሪያ ተሰጥተዋል።


ኦቲዝም ምንን ይጎዳል? ለሚለው ጥያቄ፣ የተግባቦት ክህሎቶቻቸውን እንደሚጓዳ የገለጹት የሥነ ልቦና ባለሙያው፣ የሚናገሩትን ነገር ይደጋግሙታል፣ አንድ ቃል ብቻ የመጠቀም እንጂ በሙሉ አረፍተ ነገር ለመግባባት ይቸገራሉ። ከሰዎች ጋር ያላቸው መስተጋብር በጣም የተገደበ፣ ከሰዎች ይልቅ #ማተሪያሎችን ወይም #የብቻቸው መሆንን የመምረጥ አይነት ምልኮቶች አሏቸው” ሲሉ አስረድተዋል።


*ስታዩአቸው፣ ስታወሯቸው ቀጥተኛ #የዓይን እይታ የመሸሽ (ያ ማለት ግን አያዩም ሳይሆን በደንብ የሚያዩ ናቸው)። አንዳንድ ጊዜ ለትዕዛዞች ወይም ለነገሮች ምላሽ የመስጠት ሂደት በጣም የተለያዩ ይሆናል (አይሰሙም ሳይሆን ይሰማሉ ግን መልስ አይሰጡም ማለት ነው)” ብለዋል።


*“ሌላው በጣም ድግግሞሽ የበዛባቸው ባህሪያትን ያሳያሉ። አንድ ነገር ከወደዱ ሁሌ ከዛው ነገር የተለዬ ቁርኝት መፍጠር (የሙጥኝ ማለት)፣ የለመዱትን አንድ ነገር ለመቀየር መቸገር ሊኖር ይችላል። እነዚህ ነገሮች ባህሪየመቸውን ወይም የተግባቦት ክፍላቸውን ሲያውኩት ይስተዋላል። ብዙ ጊዜ የኦቲዝምን ምልክት በዚህ መለየት እንችላለን” ነው ያሉት።


በሌላ በኩል አቶ ቴውድሮስ ዳውንሲንድረምን በተመለከተ በሰጡት ቃል፣ “ዳውንሲንድረም ስንል ግን ከዘረ መል ጋር የተያየዘ ችግር ነው” ሲሉ ገልጸው፣ “Chromosome Abnormality የሚባል ነገር አለ፣ አንድ ሰው ሲፈጠር 23 Chromosome ከወንዱ፣ 23 Chromosome ከሴቷ ይሆንና በሚፈጠርበት ሰዓት 24ኛ Chromosome Extra (ተጨማሪ) ይኖራል። በዛ ጊዜ የሚፈጠሩ ልጆት ዳውንሲንድረም የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ያለ የእድገት ችግር አለ ማለት ነው” ብለዋል።


“ብዙ ጊዜ ዳውንሲንድረም ያለባቸው ልጆች ስናይ አካላዊ ምልክቶቾን እናያለን ትልቁ ልዩነት ከኦቲዝም ጋር አንደኛው ይኼ ነው። በአካል ኦቲዝም ልጅችን አይተን ልናውቅ አንችልም። ዳውንሲንድረም ልጆችን ግን አካላቸውን አይተን የምናውቅበት ሁኔታ አለ” ያሉት የሥነ ልቦና ባለሙያው አክለውም፦


*“አሁን አሁን በአደጉት አገሮች ላይ ከሦስት ወራት ጀምሮ ፅንስ ውስጥ እያለም መታወቅ ተጀምሯል። ከተወለዱ በኋላም ይታወቃል። ዳውንሲንድረም ልጆች ብዙ ጊዜ ከተወለዱ በኋላ ሜዲካል የሆኑ ትሪትመንቶችም ያስፈልጓቸዋል። በተለይ ከልብ ኬዝ ጋር በተያያዘ ብዙ ጊዜ #የልብ ቀዳዳ ይኖራል። አንዳንዴ ሰርጀሪ ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በክትትልና በመድኃኒት የሚያገግሙበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል።


*ዳውንሲንድረም ብቻውን ሳይሆን የአዕምሮ እድገት ውስንነት ሌላ ደግሞ አለ። የአዕምሮ እድገት ውስንነት ማንኛውንም ሰው እስከ 18 ዓመቱ ድረስ ሊያጋጥመው የሚችል ጤና ጋር የተያያዘ ችግር ነው (የመማር፣ የመቀበል፣ ነገሮቹን የመረዳት አቅምን የማዳከም ማለት ነው)።


*ስለዚህ ከዳውንሲንድረም ጋር ሲመጣ ነገሩን ትንሽ ከበድ የሚያደርገው የአዕምሮ እድገት ውስንነት አብሮ ይመጣል። ኦቲዝም ጋርም አብሮ ሊመጣ ይችላል። ተባባሪ/ተደራራቢ የሆኑ ችግሮች አብረው ሊከሰቱ ይችላሉ። በአጭሩ ልዩነታቸው ይህን ይመስላል” ሲሉ አስረድተዋል።



ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ/ም


“ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም!” - በመማሯ ማንበብ የቻለች የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባት ብላቴናዋ ቅድስት አበበ።


12 የሚሆኑ በዲውንሲንድረምና የአዕምሮ እድገት ውስንነት ዘርፍ ተሰማርተው ለልጆች ትምህርትና ሌሎች ስልጠናዎች እያደረጉ የሚገኙ ማኀበራት “በጋራ ድምጻችንን” እናሰማ በሚል ኀብረት የፈጠሩ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ/ም የሚከበረውን የዲውንሲንድረም ዓመታዊ በዓል አስመልክተው ከኀብረቱ መካከል የተገኙት አምስት ማኀበራት ዓርብ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።


በዚሁ መርሀ ግብር ከተገኙት ማኀበራት መካከል አኔዱ የሆነው ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ብሔራዊ ማኀበር የትምህርት አገልግሎት የሰጣትና ማንበብ መጻፍ የቻለችው ብላቴና ቅድስት አበበ ዳውንሲንድረም ያለባቸውን ኢትዮጵያዊያን ወክላ ለማህበረሰቡ በንባብ ባስተላለፈችሁ መልዕክት ተከታዩን ስትል ተደምጣለች።


“ይህ ቀን በዓለም አቀፍ የዳውንሲንድረም ቀን ሲባል፣ በዓለም ለ13ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል” ብላ፣ ዋና ዓላማው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኝ የዳውን ሲንድረም ማኀበራት አንድ ላይ በመሰባሰብ ድምጻቸውን በጋራ የሚያሰሙበት መሆኑን አስረድታለች።


“ፍቅር ኢትዮጵያ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ማኅበር ላለፉት 28 ዓመታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ለማህበረሰቡ ስለዳውን ሲንድረም ብሎም የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ግንዛቤ እያስጨበጠ ቆይቷል” ብላለች።


“ዘንድሮ #ፍረጃ ይቁም! በሚል መሪ ቃል እያከበረ ይገኛል” ያለችው ብላቴናዋ ቅድስት፣ ፍረጃ በአብዛኛው የተዛባ አመለካከት ዳውንሲንድረም ያለባቸውን ልጆች ሰዎች በዓይን እይታ የተዛባ በሆነ መንገድ “አይችሉም” የሚሉበት መንገድ መሆኑን አስረድታ፣ “ነገር ግን ሁላችንም የተለያዩ አቅሞችና ፍላጎቶች ያሉን ሰዎች ነን ስለዚህ ከመፈረጅ እንዲቆጠቡ” ስትል አሳስባለች።


“እኔና ጓደኞቼ መማር፣ መሰልጠን፣ መብታችን ተከብሮ ከሌሎች እኩል በልማት ሥራዎችን ተካፋይ ለመሆን የበኩላችንን ማድረግ እንችላለን። በዓሉ ግንዛቤ የምትጨብጡበት፣ የምትደሰቱበት እንዲሆንላችሀ አመኛለሁ። ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም! ፍረጃ ይቁም!” በማለት አሳስባለች።


ሌላኛ ከኒያ ፋውንዴሽን የመጣው የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለበት ወጣት በበኩሉ፣ ባገኘው ስልጠና ሌሎች የአዕም እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች ለመርዳት ደረጃ እንደደረሰ ንግግር አድርጓል።


የዘርፉ ኃላፊዎች በበኩላቸው፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች “መማር አይችሉም፣ ቤተሰብ መመስረት አይችሉም” በሚል የሚሰነዘረው ፍረጃ ልጆቹ ወደ ኋላ እንዲቀሩ እያደረጋቸው መሆኑ ተነግሯል። 


በዚህም አገልግሎት መስጫ ቦታ መኖሩን ካለማወቅና የፍረጃን ጉዳት ካለመገንዘብ አንጻር ብዙ ውስንነቱ ያለባቸውን ልጆች ወላጆቻቸው ቤት ዘግተው አስቀምጠዋቸው እንደሚገኙ፣ ነገር ግን ልጆቹ ወደ ማፈበራት ሂደው አገልግሎት ቢያገኙ እንደማንኛውም ሰው ሁሉን መድረግ እንደሚችሉ ማወቅ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።


ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

Report Page