Tikvah Ethiopia

Tikvah Ethiopia


27/ 6 /16 

ትግራይ _ኢትዮጵያ 

በጦርነቱ ምክንያት የ 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የሚገመት የንብረት ውድመት የደረሰው የዓዲግራት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሃገረ ስብከት ተራድኦ ድርጅት ለ364 ሺህ 311 የጦርነት ተፈናቃዮች : የድርቅና ረሃብ ተጠቂዎች በመርዳት ላይ እንደሚገኝ ገለፀ።


ከፓለቲካ ነፃ መሆኑ የሚጠቅሰው የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተራድኦ ድርጅት በትግራይ ጦርነት ጊዜ ለሰብአዊ አገልግሎት ስራ ሲጠቅምባቸው የነበሩ 14 መኪኖች መዘረፉ አስታውሶ : ዘራፊዎቹ ለሰብአዊ አገልግሎት መኪኖቹ እንዲመልሱ "በፈጣሪ ስም እማፀናሎህ " ብለዋል።


የምግባረ ሰናይ ድርጅቲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተወልደ ሃይለስላሴ ወደ ዓዲግራት ለተጓዘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በሰጡት ቃለመጠይቅ እንደገለፁት : ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ባለፈው 2023 የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ 433 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ 364 ሺህ 311 ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ አቅርበዋል።


ከተረጂዎቹ 50 በመቶ በላይ ሴቶች መሆናቸው ያብራሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አገዛው በመላ ትግራይና ዓፋር ዞን 2 እንደተከናወነ አብራርተዋል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ በዓዲግራት : በመቐለ : በእንዳስላሰ ሽረ እንዲሁም በዓፋር ዞን 2 ባሉት ዋናና ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች በኩል ብንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት : የጊዚያዊ መጠለያ ግንባታ : የተበላሹ የውሃ ጉድጓዶች ጥገናና ቁፋሮ : የፈረሱና አዳዲስ ትምህርት ቤቶች ጥገናና ግንባታ እንዲሁም ለተማሪዎች የምግብ አገልግሎት ማቅረብ : በጦርነቱ የተጎዱ ወገኖች መልሶ ማቋቋም : የጦርነት የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶች ህክምናና ሌሎች ሰብአዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። 



በጦርነቱ ወቅት ሳይቀር ወዳጅ ጠላት ሳይል በቦቴ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ያቀርብ እንደነበረ የጠቀሱት አቶ ተወልደ : አሁንም በኤርትራ ሰራዊት ስር ባሉት የዛላኣምበሳና የኢሮብ ወረዳ ቀበሌዎች ለሚኖሩ ወገኖች የንፁሃ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል። 


የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ አጋዦች አብዛኞቹ በአውሮፓ : በአሜሪካ : በጀርመን : በስዊዘርላንድ : በእንግሊዝ : በአየርላንድ : በስኮትላንድ : የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእርዳታ ድርጅቶችና ዩኒሴፍ እንደሆኑ የጠቀሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ : ድርጅቶቹ ለቀደመው ደጋፋቸው በማመስግን : በአሁኑ ጊዜ በትግራይና በዓፈር ዞን 2 የሚታየው የንፁህ የመጠጥ ውሃ : የምርጥ ዘርና የምግብ አቅርቦት እጥረት ለማቃለል ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እገዛቸው እንደሚሹ ተማፅነዋል።


ከ179 ዓመታት በፊት በ1832 ዓ.ም በምስራቅ ትግራይ ኢትዮጵያ የተመሰረተችው የዓዲግራት ካቶሊክ ቤተክርስትያን ከመዋእለ ህፃናት እስከ 12ኛ ክፍልና ኮሌጅ የሚያስተምሩ በስርዋ የሚተዳደሩ 53 ትምህርት ቤቶች አሉዋት።


በቤተክርስትያንዋ ተፅፈው የታተሙ የታሪክና የሃይማኖት መፃህፍት እንደሚያመለክቱትና እንደሚያስረዱት : ቤተክርስትያንዋ በ1837 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት ከተማ ልዩ ቦታ ጎልዓ የግብረገብና የሳይንስ ትምህርቶች የሚያስተምር ትምህርት ቤት ከፍታለች የሚል ዘገባ ያደረሰን ቦታው ደረስ የተጓዘው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

           ***               

@tikvahethiopia       

Report Page