Tikvah-Ethiopia

Tikvah-Ethiopia


- የማይደፈር ሲደፈር አይተናል ፤ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ዝም አንልም።


- " ፖለቲካው የፖለቲካው መስመር ሲደፈር ዝም እንደማይል ሁሉ እኔም ደግሞ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ህይወቴም ማንነቴም ክብሬም ቤተክርስቲያኔ ስለሆናች እሷ ስትደፈር ዝም አልልም። እናገራለሁ ፤ የመጣውን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ "


- ከዚህ በፊት ለመንግሥት ችግር ካለ እዚህ ጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ንገሩን ብለናቸዋል። እኛ እናርማለን፣ እኛው እናስተካክላለን ፣ አላስፈላጊ እርምጃ አትውሰዱ ብለናቸዋል። ትላንት ግን ከቤተክህነት የሚወጣው በሙሉ ይፈተሻል ዛሬም ፣ የሚወጣ መኪና በሙሉ ይፋተሻል ፤ የሚገባው ግን አይፈተሽም። የሚገባውን የኛ ዘበኞች ይፈትሹ ይሆናል፤ የመንግሥት ወታደሮች ግን አይፈትሹም። አንዱ ሌላ ነገር ይዞ ገብቶ ሲወጣ ፈታሹ ሌላ ነገር ይዟ ተብሎ የቤተክርስቲያን ስም እና ክብር ቢዋረድ ማነው ኃላፊው ?


- ምንድነው የተፈለገው ? ከቤተክርስቲያን ምንድነው የሚወጣው ? መድፍ ነው ? መሳሪያ ነው ? አከፋፋይ ናት ቤተክርስቲያኒቱ ? አትታመንም ? መንግሥትን ያስጮኸ ነገር አለ እኛም የጮህንበት ከመንግስት በፊት ፤ ግለሰቦችን ስለተናገሩት ንግግር የማይባል ተብሏል እያልን እኛ ነን የጮህን ይሄ የቤተክርስቲያን ቋንቋ አይደለም ብለን ነበር ፤ መግለጫ ለመስጠት ተዘጋጅተን ነበር መንገዱን ስናየው መጠላለፊያ ስለሄነ እንጂ ከፅድቅ ስላልሆነ ነው ዝም ያለነው። የፅድቅ ሲሆን ገፍተን ነው የምንወጣው።


- ከቤተክህነት ምንድነው የሚወጣው ? ከተፈለገ መባል ያለበት ጥርጣሬ አለን ቤተክህነት ውስጥ ይባላል ፤ እንዲህ አይነት ነገር ቢወጣ ኃላፊነቱ የናተ ነው ጠብቁ ነው ልንባል የሚገባው ወይም ሰው እንሥጣችሁ የሚያንሳችሁ ከሆነ ቤተክርስቲያኒቱን እንዳያስወቅስ ነው መባል ያለበት እንጂ ቤተክርስቲያን የማትታመን ሆነ ከትላንት ጀምሮ እስካሁን እኛ መሪዎቹ በማናውቀው ፈታሽ በር ላይ ቆሞ መፈተሽ ድፍረት ነው። ቤተክርስቲያኒቱን ህልውናዋን መፈታተን ነው። አቅሟንም መፈትን ነው ተገቢ አይደለም።


- መደፋፈሩ በዝቷል፤ መንግስትም ቤተክርስቲያኒቱን ይደፍራል አልፎ ይሄዳል። ጠቅላይ ቤተክህነት / ቤተክርስቲያን እንደ ተቋም ደፍራ አላስፈላጊ ነገር ባትደርስም የደረሰችበት ባለፈው ህገወጥ ሲመት ሲፈፀም ተንቀሳቅሳለች ከዚያ ወዲህ ሰላምን ለማስፈን እየጣረች ነው።


- እንደ ግለሰብ በስሜት የሚናገሩ ሰዎች ይኖራሉ። ቤተክርስቲያኒቱን መድፈር አዳጋ ነው። ለሃይማኖቱ የማይሞት የለም፣ ከዚህ በፊት ብዙዎች ሞተዋል ፤ ተከባብረን እንኑር ለሰላም እንኑር።


- በየትኛውም አቅጣጫ አዛዣችን በዝቷል፤ ላዘዘን ሁሉ አጎንብሰን እንችላለን ? ሃይማኖታችን ከሚፈቅደው ውጭ ? በሉ የሚሉንም ሁሉ ማለት እንችላለን እንዴ ? በሉ የሚለን ሃይማኖታችን ብቻ ነው።


- ካህን ነው ሲሉት ሌላ ነጭ ለባሽ ይሆናል፣ ነጭ ለባሽ ነው ሲሉት ካህን ሆኖ ይገኛል፤ የቤተክርስቲያን መሪ ነው ሲሉት ሌላ የፖለቲካ መሪ ሆኖ ይገኛል፤ የፖለቲካ መሪ ሲሉት ቀዳሽ ሆኖ ይገኛል ምን አመጣው ይሄን ቀጥ ብለን እንቁም። ደሃ ሲበደል ተበደለ እንበል ሲታሰር ፍቱ እንበል ፤ እያልን ነው እኮ ፤ መንግሥትን ፍቱ እያልን እንመካከራለን ይፈታል ለዚህ ደግሞ እናመሰግናለን።


- በሃይማኖት ጉዳይ አንደራደርም።


- ካህን ካህን ይሁን ፣ ወታደርም ወታደር ይሁን ሌላውም እራሱን ይሁን በሚያስተሳስረን ነገር ተሳስረን ጥላቻና ሁከትን፣ ሽብርና አላስፈላጊ ነገርን እናርቅ።


- ካላስፈላጊ #ጎጠኝነት፣ #ዘረኝነት እንራቅ።


- የጎጠኝነት ምንጩ ቤተክርስቲያን ሆናለች። ከሃይማኖቴ ቋንቋዬ ይበልጣል የሚሉ ሰዎች የተነሱበት ጊዜ ነው። ስወለድ ቋንቋዬን ይዤ ነው የተወለድኩት ሃማኖት በኃላ የመጣ ነው የሚሉ ካህነት የተፈጠሩበት ወቅት ነው። ይሄን ሁሉ ተሸክመን አጎንብሰን ቤተክርስቲያንን ለማሻገር እየሰራን ነው ምዕመናን ተረዱን !


- ምዕመናን ሁከት ከሚያመጣ ነገር እራሳችሁን ጠብቁ። በጥምቀት በዓላችን እራሳችሁ አስተናጋጅ እራሳችሁ ተስተገናጋጅ ሆችሁ ደስ በሚያሰኝ ክብርና ሞገስ ፣ የአለባበስ ስርዓት ከማንኛውም የፖለቲካ አመለካከት የራቀ ቤተክርስቲያን ብቻ ተወከለ አከባበር እንድታደርጉ ይሁን።



- ነገር የሚጭሩትን አላስፈላጊ ነገር የሚያደርጉትን በህግ እና ስርዓት ፤ ቤተክርስቲያን ህጓ በሚፈቅደው ፤ መንግሥትም ህጉ በሚፈቅደው እየተናበብን እንስራ ለዚህ በራችን ክፍት ነው።


- ገዢ ሰላምና ፍቅር ብቻ ነው አመፅ ፣ ኃይል፣ ጉልበት፣ ጦር የተወሰነ ጊዜ ነው የሚገዛው ከተወሰነ ጊዜ በኃላ በራሱ ይወድቃል። ፍቅርን የሚገዛውን ያህል ማንም ገዝቶ አያውቅም።


- ሀገራችን ሰላም ትሁን የሃማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው። አላስፈላጊ ሙገሳንም እንርሳው። ካላስፈላጊ ሙገሳ አስፈላጊ በሆነ ወቀሳና ለመጨረሻው መከራ እራሳችንን እናዘጋጅ።


@tikvahethiopia

Report Page