Tikvah Ethiopia

Tikvah Ethiopia


“ 10 ቤቶች ሀሰተኛ የስጋ ምርመራ ሰነድ ይዘው ህብረተሰቡን እያታለሉ ስጋ ሲሸጡ የነበሩበት ሁኔታ መኖሩን ያዬንበት ሂደት አለ ” - አቶ ሰይድ እንድሪስ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰይድ እንድሪስ የ2016 ዓ/ም የገና በዓል ዝግጅትን በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት ገለጻ፣ “ሉካንዳ ቤት ሂደው ከሚገዙት በተጨማሪ እንስሳትን በራሳቸው ይዘው ለሚመጡ የግል ተጠቃሚዎች የበዓሉ ጠዋት ከ12፡00 ጀምሮ እንስሳቱን እየተቀበልን አገልግሎት እንሰጣለን” ብለዋል።

“ በማታው ጊዜ የምንሰጠው ለሉኳንዳ ቤቶች፣ ለሆቴሎች፣ ለሬስቶራንቶች ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ “በዓል ላይ የሚያሰጋው ሕገ ወጥ የእንስሳት እርድ ነው። ይሄ ሕገ ወጥ የእንስሳት እርድ በሕገ ወጥ መልኩ ለሕዝብ እየቀረበ ያለበት ሁኔታ አለ” ሲሉ አስረድተዋል።

ማንኛውም ለግብይት (ለሽያጭ) የሚቀርብ ስጋ በቄራ የታረደ በቄራ ፍቃድ የተሰጣቸው ተሽከርካሪዎች መጓጓዝ እንዳለበት፤ ሰው በየቤቱ ቢያርድ ሕገ ወጥ ነው ባይባልም ያልተመረመረ እንደሆነ ለልጆቹ የሚያበላው ችግር እንዳለው አስረድተዋል።

አቶ ሰይድ እንድሪስ በዝርዝር ምን አሉ?

* ሰሞኑን የተለያዩ ኦፕሬሽኖች ሰርተናል። 200 ቤቶች አካበቢ ለማየት ሞክረን ከዛ ውስጥ በ30 ቤቶች ሕገ ወጥ ስጋ የተገኘበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው።

* 15 ቤቶች ሙሉ ለሙሉ አንዲታሸጉ ያደረግንበት፣ ሌላ ተጨማሪ 10 ቤቶች ደግሞ ሕገ ወጥ (ሀሰተኛ) የስጋ ምርመራ ሰነድ ይዘው ህብረተሰቡን እያታለሉ ሥጋ ሲሸጡ የነበሩበት ሁኔታ መኖሩን ያዬንበት ሂደት አለ።

* አጠቃላይ ባደረግነው ሂደት 1,500 ኪ.ግ ሕገ ወጥ በሦስት ቀናት ውስጥ ተሰብስቦ እዚህ መጥቶ እንዲወገድ የተደረገበት ሂደት አለ። 

* ባደረግነው ዳሰሳ የሕገ ወጥ እንስሳት እርድ አለ። ከዚያ ውጪ ግን በእምነትም ይሁን በባህላችን ባዕድ የሆኑ እንስሳት ታርደው ወደ ገበያ የቀረቡበት ሂደት የለም። የተያዘው ሥጋ የበሬ፣ የፍዬልና የበግ፣ ግን በሕገ ወጥ መንገድ የታረደ ነው።

* የበሬ ስጋ የአንድ ኪሎ ዋጋ ከ550 እስከ 570 ብር በዕለቱ ሽያጭ ይከናወናል። በአራት መስኮቶች የበግና የፍየል ስጋ ሽያጭ ይከናወናል። የበግ ስጋ በ500 ብር፣ የፍየል በ510 ብር በኪ.ግ ለበዓሉም ለመደበኛ ቀናትም የሚያቀርቡበት በዚህ ደረጃ ተዘጋጅቷል።

ለ2016 ዓ/ም የገና በዓል 3,000 በሬዎችን፤ 5,000 በግና ፍየሎችን ለማረድ ዝግጅት መደረጉን፣ 35 የስጋ ማሰራጫ ተሽከርካሪዎች፣ 40 የሥጋ መርማሪ ባለሙያዎች እንደተዘጋጁም አስረድተዋል።

“ ግለሰቦቹም ተይዘው በሕግ ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ያለው” - አቶ አየለ ሳህሌ

“ ይህንን ሲያወሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ውለው በምርመራ ውስጥ መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲያውቅ እንፈልጋለን ” - አቶ ሰይድ እንድሪስ

የአዲስ አበባ ሉኳንዳ ቤት ነጋዴዎች ማኀበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ፣ ከዚህ በፊት ‘የባዕድ እንስሳት ስጋ እየተሸጠ ነው’ ብለው ሲናገሩ የነበሩ ሰዎችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ ግለሰቦቹም ተይዘው በሕግ ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ያለው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“ በባለፈው የዚህ አለቧልታ መነሻ የሆኑትን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅና የዛው ባልደረባ የሆነች ሴት ለሕግ እንድትቀርብ ጥያቄ አቅርበን የምስክር ቃላችንንም የማኀበሩ የቦርድ ፕሬዝዳንት፣ እኔም ሥራ አስኪያጁ፣ ከሉኳንዳ ቤት ነጋዴ አንድ ምስክር፣ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ተገኝተን ቃላችንን የሰጠንበት ሁኔታ አለ ” ነው ያሉት።

“ ግለሰቦቹም ተይዘው በሕግ ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው ያለው። በሰፊው ምናልባት የምርመራ ጉዳይ ስለሆነ ሕጉም ስለማይፈቅድ፣ የት ደረሱ? ምን ላይ ነው? የሚለውን ነገር ማብራራት ዛሬ ላይ ባይቻልም ወደፊት በሚዲያ ጭምር የምንገልጸው ጉዳይ ነው ” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እንድሪስ በበኩላቸው ጉዳዩን በተመለከተ ባስረዱበት ዓውድ፣ “ይህንን ሲያወሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ውለው በምርመራ ውስጥ መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲያውቅ እንፈልጋለን” ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሉኳንዳ ቤት ነጋዴዎች ማኀበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አየለ ሳህሌ በዝርዝር ምኑ አሉ ?

* ማስረጃና መረጃ ካለ የእኛም ቢሮ ስልክ ክፍት ነው። አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትም ደንብ ማስከበርና ሕግን ሊያስከብሩ የሚንቀሳቀሱ በከተማዋ ላይ ያሉ አካላት ዝግጁ መሆናቸውን መግለጽ እንፈልጋለን። 

* ይሄ አሉባልታ በመነዛቱ ምክንያት በርካቶች በፊት ሲያቀርቡት የነበረው የእርድ አገልግሎት በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትና በቅርንጫፉም እያልተጠቀሙም እንዳልነበረ መገንዘብ ይቻላል።

* ከዛ አልፎ ተርፎ ሠራተኞቻቸውን እስከመቀነስ መድረሳቸው የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ቢያንስ በሉኳንዳ ቤት ከአምስት እስከ 50 ሠራተኛ የሚይዙ በስፋት የሚሰሩበት ሁኔታ ነው ያለው።

* ነገር ግን ያን ሁሉ ሠራተኛ ማስተናገድ የሚቻለው ሥራው በሕይወት ሲቀጥል ነው። ያ ባለመሆኑ ምክንያት ሠራተኞቻቸውን የመቀነስና የተለያዩ ጉዳዮችም እንደነበሩ በዚያ ሰዓት ሲታይ የቆየ ጉዳይ ነው።

* በዚህ ቄራ (በአ/አ) የሚታረደው የቁም እንስሳትና የአነስተኛ እንስሳት (በግና ፍየል) ሌጧቸው ተደራጅቶ በተገቢው ፋብሪካዎች የሚሄዱበት ሁኔታ አለ። 

* እንደዚሁም ደግሞ ተረፈ ምርትና የተለያዩ እኛ የማንመገባቸው ወደ ውጪ ገበያ የሚቀርቡ የተለያዩ ምርቶችን ጭምር እያደራጀ የሚልክበት ሁኔታ እንዳለም ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህ ይኼም ከአገራዊ የኢኮኖሚ ፋይዳ አንጻርም ሊታይ ይገባል።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እንድሪስ በበኩላቸው ጉዳዩን በተመለከተ ባስረዱበት ዓውድ ምን አሉ?

- ይህንን ሲያወሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ውለው በምርመራ ውስጥ መሆኑን ህብረተሰቡ እንዲያውቅ እንፈልጋለን። ፓሊስ ለማህበረሰቡ ማብራሪያ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን።

- በዋናነት ሲነሳ የነበረው #የአህያ ስጋ ጋር በተገናኘ ነው። በዛ መሠረት ህብረተሰቡ አለመተማመን ውስጥ የገባበት ነገር ነበር። አለመተማመኑ ብቻ ሳይሆን የስጋ ፍላጎት በጣም የቀነሰበት፣ አፕታይት የተዘጋበት፣ በዛን ጊዜ አብዛኛዎቹ ሉኳንዳ ቤቶች ገበያ የላቸውም ነበር።

- ሉኳንዳ ቤቶች ገበያ ከሌላቸው ደግሞ አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አያሳርዱም ማለት ነው። እኛም ላይ የእርድ መጠኑ ቀንሷል። ሉኳንዳ ቤቶች አካባቢ የሽያጭ መጠኑ የቀነሰበት ነበር።


በአሰላ በሚገኙ ስጋ ቤቶች የአህያ ስጋ ከሌላ ስጋ ጋር ተቀላቅሎ ሲሸጥ መያዙን የብሩክ ኢትዮጵያ በእንስሳት ጤና አጠባበቅ ጥበቃና ደኅንነት አለም ዓቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የማማከር ልማት ባለሙያ መናገራቸውን፣ ድርጅቱ በሰጠን ማብራሪያ ወሬው ከእውነት የራቀ መሆኑን፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ ነጋዴዎች ኪሳራ እንደደረሰባቸው፣ ምግብ ሆቴል ተጠቃሚዎች ፍላጎታቸው እንደተዘጋ መናገራቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia

Report Page