Tigray Update

Tigray Update


ወቅታዊ የትግራይ ሁኔታ ፦

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት በትላንትናው ዕለት የተናጠል በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም ካወጀ በኃላ የተለያዩ ሀገራት አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

#Britain

ብሪታንያ የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ የአንድ ወገን/ የተናጠል በሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ማድረጉን በደስታ እንቀበላለን ብላለች::

ለዚህም ሁሉም ወገኖች ዕውቅና እንዲሰጡ ፣ ግጭት ለማቆም እና ሕይወት አድን ሰብዓዊ ዕርዳታ በክልሉ በፍጥነት እንዲያደርስ ጠይቃለች::

#China

የቻይና የኢትዮጵያን የተናጥል ተኩስ አቁም ጥሪ እንደምትደግፍ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን አማካኝነት አስታወቃለች፡፡

ቃል አቀባዩ “እኛ አትዮጰያዊያን የውስጥ ችግራቸውን በራሳቸው አቅም የመፍታት ጥበብ እንዳላቸው እናምናለን” ብለዋል፡፡ 

#UAE

የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ ማቆም ማወጁ ተቀባይነት ያለው ውሳኔ ነው ብላለች።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ግጭትን ለማቆም እና ፖለቲካዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ ብቸኛው አማራጭ ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው ነው ብሏል። 

ቀጣይነት ያለው ሰላም እና መረጋገት ለማረጋገጥ በሕግ የበላይነት እና ሕገ-መንግሥታዊ ማዕቀፍ ውስጥ ገንቢ የሆኑ ውይይቶች ማድረግ ብቸኛው መንገድ ነው ሲል አክሏል።

#QATAR 

 ኳታር የፌዴራል መንግስት ያወጀውን የተኩስ አቁም ስምምነት እደግፋለሁ ስትል አሳውቃለች። ይህ ውሳኔ በሰላም ሂደቱ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብላለች።


UNICEF ያሰማው በመከላከያ ላይ ያሰማው ክስ :

በትላንትናው ዕለት UNICEF ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በመቐለ ወደ ሚገኘው ቢሮ በመግባት የተቋሙን የሳተላይት መገናኛ ቁሳቁሶች በታትነዋል ብሏል።

የድርጅቱ ኃላፊ ሔንሪየታ ፎረ ይህ ድርጊት የተመድ ያለውን ያለመነካት መብት፣ ልዩ ጥበቃ እና ለሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውሉ ቁሳቁሶች በዓለም አቀፍ ህግ የሚሰጣቸውን ጥበቃ ይጥሳል በማለት ኮንነዋል።

ሔንሪየታ ፎረ በትግራይ ግጭት ውስጥ የሚሳተፉ ወገኖች ለጦርነት ወቅት ሕግጋት እንዲገዙ እንዲሁም የግብረ ሰናይ ተቋማትን እንዲያከብሩ ጠይቀዋል።

እስካሁን ድረስ በUNICEF ለቀረበው ክስ የኢትዮጵያ መከላከያ የሰጠው መልስ የለም።


የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወላጆች እና ከትግራይ ውጭ ያሉ ቤተሰቦች ጭንቀት :

በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ልጆቻቸውን ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች በክልሉ እየሆነ ስላለው ጉዳይ በእጅጉ ተጨንቀዋል።

በመቐለ ጨምሮ በሌሎችም የትግራይ ክልል ከተሞች ሙሉ በሙሉ ኔትዎርክ ተቋርጧል።

የልጆቻቸውን ድምፅ መስማት ፣ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አልቻሉም።

በሚመለከተው የመንግስት አካላት እስካሁን የተባለ ነገር የለም፤ ቲክቫህ ኢትጵያ ተማሪዎች ስላሉበት ሁኔታ በቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገፁ አማካኝነት ለማጣራት ስራዎችን እየሰራ ነው።

በሌላ በኩል ከትግራይ ውጪ የሚኖሩ ትግራይ ክልል የሚኖሩ ቤተሰቦቻቸውን ግኘት እንዳልቻሉ ጠቁመዋል። ይህም ከፍተኛ ጭንቀት እንዳሳደረባቸው ገልፀዋል።

ቤተሰቦቻቸው ስላሉበት ሁኔታ በተደጋጋሚ ስልክ ቢሞክሩም አይሰራም።

ከዚህ ቀድም የትግራይ ግጭት ሲጀመር ኔትዎርክ ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ ግንኙነት ማድረግ አልተቻለም በኃላም የፌዴራል መንግስት ትግራይን ሲቆጣጠር ተመልሶ ነበር።


አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስጋት :

አምነስቲ ኢንተርናሽና የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሳራ ጃክሰ አምነሲቲ ኢንተርናሽናል በትግራይ ያሉ ሲቫ ዜጎችን ደህንነት እንደማያሳስበው ገልፀዋል።

ላለፉት ወራት በትግራይ በነበረው ውጊያ፣ በሁሉም ወገኖች በተፈፀሙ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣ የጦር ወንጀሎችን በመቋቋም ያሳለፉ የትግራይ ሲቪል ዜጎች ደህንነት አሁንም አምነስቲን እንደማያሳስበው አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ ጦር የያዛቸውን ቦታዎች እየለቀቀ መሆኑን እና የትግራይ ክልል ኃይሎች ቦታዎችን እየተቆጣጠሩ መሆኑን ያነሱት ሳራ ጃክሰን በዚህ ወቅት ለዜጎች የሚደረገው ጥበቃ ከሁሉም በላይ መሆን አለበት ብለዋል።

አክለውም ፥ “ሁሉም ወገኖች ተጨማሪ የጭፍጨፋ እና የጦር ወንጀሎች እንዳይፈፀም እንዲከላከሉ ጥሪ እናቀርባለን" ብለዋል። በወታደሮች እና ሚሊሻዎች የበቀል ጥቃቶች እንዳይፈፀሙ በማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪ ፥ ሁሉም ወገኖች ለሲቪል ዜጎች ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን ማረጋገጥ አለባቸው እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የኢንተርኔት ፣ የህትመት ወይም የብሮድካስት ሚዲያ ስለሌለ ሙሉ የግንኙነት ተደራሽነትን ለመመለስ መስራት አለባቸው ብለዋል።

አምነስቲ በሁሉም ወገኖች በትግራይ ሲቪል ዜጎች ላይ የበቀል የበቀል እርምጃ ሊወሰድ ይችላል የሚል ስጋት አለ ብሏል ( - ወደ ኋላ የሚመለሱ የመከላከያ ወታደሮች ፣ በአጎራባች አማራ ክልል እና በኤርትራ ኃይሎች እና በTDF (የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች)ን በማንሳት።


የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ፦

የአሜሪካ ትግራይ ክልል ያለድን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች እንደምትገኝ ገልፃለች።

ይህን የገለፀችው ዛሬ በአዲስ አበባ ኤምባሲዋ ባወጣችው መግለጫ ነው

አሜሪካ በአሁን ሰዓት ከመቐለ የሚነሱና ወደ ከተማዋ የሚደረጉ በረራዎች ቆመዋል፣ በረራዎች መቼ እንደሚጀምር አይታወቅም ብሏለች።

በተጨማሪ ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል፣ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም፣ ስልክ ግንኙነት ተቋርጧል ሲል ሁኔታውን አስረድታለች።

ቅድሚያ ለዜጎቿ እንደምትሰጥ የገለፀችው አሜሪካ በትግራይ የሚገኙ ዜጎቿ የአካባቢ ሚዲያዎችን እንዲከታተሉ ፣ የቆንጽላ መልዕክቶችን እና የኤምባሲዉን ማህበራዊ ሚዲያ አንዲከታተሉ መልዕክት አስተላልፋለች።

ዜጎቿ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አንዲያደርጉ አሳስባለች።


የህወሓት ኃይሎች ከተሞችን ስለመያዛቸው ፦

የፌዴራል መንግስቱ ስለትግራይ ክልል ከተሞች አሁናዊ ሁኔታ /በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የተለያዩ ከተሞች ግን በህወሓት ኃይሎች ስር ስለመውደቃቸው ተሰምቷል። 

ዛሬ ሮይተርስ ባወጣው ዘበባ የሽረ ከተማ ነዋሪዎች የኤርትራ ጦር ከተማውን ለቆ መውጣቱንና የህወሓት ኃይሎች ከተማውን መቆጣጠራቸውን ገልፀዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለሌሎች የትግራይ ከተሞች የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ቢሆን በክልሉ ሙሉ በሙሉ ኔትዎርክ በመቋረጡ ማረጋገጥ አልተቻለም።


አነጋጋሪ የሆነው የአቶ ጌታቸው ረዳ አስተያየት ፦

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እጅግ በጥብቅ ከሚፈልጋቸው የቀድሞ የትግራይ ገዢ ፓርቲ ህወሓት አመራሮች መካከል አንዱና ዋነኛው የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ ዜና ወኪል በሰጡት ቃል ፥ መቐለ 100% በቁጥጥራችን ስር ነች ብለዋል። የቀድሞው መንግስት ወደስራው ተመልሷልም ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ መረጃ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ኃይል ፥ ኤርትራ እና አማራ ክልል ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ዛሬ ከሰዓት ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ፥ "አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የ “ጠላት” ኃይሎችን ለማሳደድ/የውጊያ አቅም ለማዳከም ወደ ኤርትራ እና አማራ ክልል እንገባለን" ብለዋል። 


የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጠንከር ያለመግለጫ ፦

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል ላይ አፀፋ እርምጃ እንወስዳለን፣ መሬታችንም ሳይመልሰ አንተኛም ብለዋል በሚል ከሰሞኑ የተለያየ መረጃ ተሰራጭቷል።

ዛሬ ደግሞ አቶ ጌታቸው ረዳ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ጠላቶቻችንን ለማሳደድ እና አቅም ለማዳከም አስፈላጊ ከሆነ አማራ ክልል እንገባለን ማለታቸው በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከሰሞኑን ሲሰራጩ የነበሩ መረጃዎችን ይደግፋል እየተባለ ነው።

ይህ የአቶ ጌታቸው ንግግር ከተሰማ ከሰዓታት በኃላ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ መግለጫ አውጥቷል። 

መግለጫው የወጣው በቀጥታ ለሰሞኑ አስተያየቶች እና መረጃዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ይጠቁማል።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ፥ "የአማራ ህዝብ በሽብርተኞች ሂሳብ እንዲወራረድበት አይፈቅድም" በሚል ነው መግለጫውን ያወጣው።

ህወሓትን "አሸባሪው ትህነግ" እያለ የሚጠራው የአማራ ብልፅግና የህወሓት አመራሮች በተደጋጋሚ ለደረሰባቸው አሳፋሪ ሽንፈት የአማራን "ኢሊት" ተጠያቂ በማድረግ ሂሳብ እንደሚያወራርዱ ነግረውናል ብሏል።

ፓርቲው "ሂሳብ እናወራርዳለን" ባዮችን በዝምታ እንደማይታገስ አሥጠንቅቋል።

የአማራ ህዝብ ከዳተኛና ጸረ-ሕዝብ የሆኑ የትኞቹንም ጠላቶቹን ያለ ምህረት ይታገላልም ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው ስለወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ያነሳ ሲሆን አካባቢዎቹ በራሳቸው መስዋትነት ነፃነታቸውን ያስከበሩ የአማራ አካባቢዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናሳውቃለን ብሏል።

"እነዚህን አካባቢዎች ደግሞ ከህግ ውጭ በጉልበት ወስዶ ለመጠቅለል ፍላጎት ካለ፣ ለነፃነቱ ሲል ዋጋ የማይከፍል አማራ የሌለ መሆኑን ደግመን ደጋግመን እናረጋግጥላችኋለን" ሲል ገልጿል።

መሉ መግለጫው ; https://www.facebook.com/1558764601027533/posts/3164527367117907/


የፀጥታው ም/ቤት በትግራይ ጉዳይ :

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጥሪ ቀርቦለታል።

የጸጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ የጠየቁት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አየርላንድ መሆናቸውን AFPን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።

ለAFP ቃላቸውን የሰጡ ዲፕሎማቶች እንዳሉት ከሆነ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ጉዳይ የፊታችን አርብ ሊወያይ ይችላል።

አገራቱ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲካሄድ የጠየቁት የፌደራሉ መንግሥት ጦር መቀለን ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ የትግራይ ኃይሎች የክልሉን መዲና መቆጣጠራቸው ከተሰማ በኋላ ነው።


[በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ፣ ሮይተርስ፣ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ፣ የቲክቫህ አባላት፣ UNICEF ፣ ኢዜአ፣ የUK ኤምባሲ፣ አኳታር መንግስት፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ AFP፣ BBC)

@tikvahethiopia

Report Page