Textile 17 geological..

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2012
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሠርቬይ ለ2012 በጀት ዓመት ሦስት አይነት ግዥዎች ለመፈፀም ከዚህ በታች በተገፀው የጨረታ ዓይነት ዝርዝር መስፈርቱን የምታሟሉ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የልብስ ስፌት አገልግሎት ፧ ለሙሉ ልብስ፣ ቱታ፣ ጋወን፣ የጂኦሎጂስቶች የመስክ ልብስ የምናቀርበውን ብትን ጨርቅ ሰፍቶ የሚያስረክብ ሲሆን ለነዚህ ለዘረዘርናቸው ግዥዎች ለመወዳደር በዚህም መሠረት በጨረታ ተሳታፊ መሆን የሚፈልጉ መወዳደር እንዲችሉ ፤
ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣
ህጋዊ የካሽ ሬጅስተር ማሽን ደረሰኝ ወይም ህጋዊ በገቢዎች ፈቃድ የታተመ የእጅ ለእጅ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
ለመንግሥት መ/ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ (WWW.ppa.gov.et) ላይ የተመዘገቡ፣
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣
የግብር ከፋይ ቁጥር (TIN) ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና
ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አባሪ የተደረገውን የፀረ-ሙስና ቅጽ በድርጅቱ ኃላፊ ተሞልቶ ተፈርሞና ማህተም ተደርጎበት ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የተዘጋጁትን የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ዓይነት የማይመለስ ብር 50 / ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው ጎዳና ከሚገኘው መ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 108 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስላቸው የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ላሉት ለእያንዳንዳቸው ብር 5,000.00 / አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ / ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይቻላል ጨረታው የሚከፈተው ከተከታታይ 30 ቀናት በኋላ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል 11 ኛው ቀን በዓል ወይም በሥራ ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ :- በስልክ ቁጥር፡- 011 646 33 35 በውስጥ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ጂቮስጂካል ሠርቬይ
Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 08 ቀን 2012
Deadline: May 26, 2020
© walia tender