Tex wolaita damot pulsa1

Tex wolaita damot pulsa1


ኢድ ሙባረክ!

በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም ከህብረተሰብ ተሳትፎ በተሰበሰበው በጀት በዳሞት ፑላሳ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አማካይኝነት በወረዳ ውስጥ ላሉት ሚሊሻ(የአካባቢ ጥበቃ መከላከያ) ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የንግድ የሥራ ድርጅቶች

በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል ፤
የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
የቲን ተመዝጋቢ የሆነ፤
የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 16 መዉሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ዕቃውን እስከ አጫራች መስሪያ ቤት ድረስ አምጥቶ ለማስረከብ ፍቃደኛ የሆነ፤
ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና የኦርጅናሉ አንድ(1) ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል ፤
የጨረታ ማስከበር ያ ብር 15000 ( አስራ አምስት ሺህ ብር) በማንኛውም ባንክ የተመሰከረለት CPO በኦርጅናል ሠነድ ውስጥ ታሽጎ ማቅረብ የሚችል ፡፡
በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፣
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አሥራ አምስት) በተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው በ16 ኛው የሥራ ቀን 2/10/2012 በ4 ፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት 4 ፡30 በዳ/ ፑ/ ወፋ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች በሚያቀርቡት በነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበቡና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ እና ቢድ ቦንድ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስ. ቁ 0468932510 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ ::

በወላይታ ዞን ዳሞት ፑላሳ ወረዳ ፋ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 14 ቀን 2012

Deadline: June 9, 2020


© walia tender

Report Page