Tex vic used 9

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት እና UIIDP ለ2012 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
ሎት 1፡- የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች
ሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ሎት 3፡- የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ
ሎት 4፡- የደንብ ልብስ ሸሚዝ እና
ሎት 5፡- የመኪና ታፕሰሪና ጌጣጌጥ በመደበኛ በካፒታል እና በዓለም ባንክ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በየዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ሰላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 28 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ገንዘብ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮው ገ/ያዥ ገቢ አድርገው ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከተማ ልማት ቢሮግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16 ኛ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3 ፡30 ታሽጎ 4 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205000/0582266180 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ
Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 07 ቀን 2012
Deadline: May 30, 2020
© walia tendee