Tex print print sale fsc2

Tex print print sale fsc2

Walia Tender ADMIN2

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ፌ/ ከ/ ፍ/ ግ/ ጨ/005/2012

1.የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለው በጀት

ሎት 1 የደንብ ልብስ
ሎት 2 የጥገና እቃዎች
ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 4 ቋሚ እቃ
ሎት 5 ህትመት

2. ከላይ የተጠቀሰውን ግዥ ለማቅረብ ብቃት ያላቸው ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ስለሚፈልግ በታሸገ የጨረታ ሰነድ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን ልደታ ምድብ ችሎት (ዋናው መ/ቤት) እንድታቀርቡ ትጋበዛላችሁ፡፡ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት የመንግሥት ግዥ አዋጅ በተገለጸው ግልጽ የጨረታ ሥነ ሥርዓት መሠረት ይፈጸማል:: ከላይ የተጠቀሱት ግዥዎች ጨረታው የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ አቅራቢዎች ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ

የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ
በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት፣
የተፈረመ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል መግቢያ ቅፅ
የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሠርተፍኬት
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት
የአገር ውስጥ ገቢ የታክስ ክሊራንስ ይሆናል፡፡
3 ፍላጐት ያላቸው ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በቁጥር 7 (ሀ) በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር / በየሎቱ ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡

4. የጨረታው ሰነድ የሚላከው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን ልደታ ምድብ ችሎት (ዋናው መ/ቤት) ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 «ለ» በተገለጸው አድራሻ ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ. ም. እስከ 11 ፡00 ሰዓት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ማስገባት ይሆናል።

5. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1 የደንብ ልብስ ብር 5000.00
ሎት 2 ጥገና አቃዎች ብር 5000.00
ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 6000.00
ሎት 4 ቋሚ እቃ ብር 7000.00
ሎት 5 ህትመት 4000.00

6.በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ተቋማቱን ካደራጃቸው አካል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስም እና የጨረታው አይነት ተጠቅሶ የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በጨረታው ላይ ለመገኘት ስፈለጉ ተጫራቾች ወይም የተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ቁጥር 7«ሐ» በተጠቀሰው አድራሻ ሰኔ 9 ቀን 2012 ዓ. ም በ3 ፡00 ሰዓት ይከፈታል።

7.ሀ. ሰነዱ የሚሸጥበት አድራሻ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን (ዋናው መ/ቤት) ቢሮ ቁጥር 507

ለ/ ጨረታው የሚቀርብበት አድራሻ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 507

ሐ/ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 507

8. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡

መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 251-112765286 ፖስታ ሳጥን ቁጥር 3483 አ/ አበባ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 23 ቀን 2012

Deadline: June 15, 2020


© walia tender

Report Page