Tex nib3 10000

Tex nib3 10000


የጨረታ ማስታወቂያ( በድጋሚ የወጣ)

የጨረታ መለያ ቁጥር ንብ/06/2012

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸሚዞች ባንኩ ባዘጋጀው የፍላጎት ዝርዝር መግለጫ/ Specification/ መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ጨረታው በባንኩ የግዢ መምሪያ ላይ በተጠቀሰው የግልጽ ጨረታ ሂደት መሰረት ይከናወናል::
ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ፣ የግብር ከፋይነት ሠርቲፍኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋናው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00/ ብር አንድ መቶ/ በመክፈል ከግንቦት 18, 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡ 00-6፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 25,000.00( ብር ሀያ አምስት ሺህ ) ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ባላካተተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ይህም ከዋናው የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ ይቻላል::
አድራሻ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ቦሌ መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር 4ኛ ፎቅ ግዢ ዋና ክፍል:: ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115504452/5580651 መጠየቅ ይችላሉ::
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሸሚዞች ናሙና/Sample/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማምጣት አለባቸው::
ተጫራቶች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተካተቱትን መመሪያዎች በጥንቃቄ ማንበብና ማሟላት ይገባቸዋል:: ይህንን ሳይከተል የተዘጋጀ ሰነድ ውድቅ ሊደረግ ይችላል::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ዋናውን እና አንድ ኮፒ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ስር በተጠቀሰው አድራሻ እስከ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. 9፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ. ም ከሰዓት 9 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ. ም ከሰዓት 9 ፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 5 ስር በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል:: ዘግይቶ የደረሰ መወዳደሪያ ተቀባይነት አይኖረውም::
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ. ማ.


Posted: ሪፖርተር ግንቦት 17 ቀን 2012
Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page