Tex amhara proc 34

Tex amhara proc 34


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ አብክመ/ መግንምአ/ ድ/ ብግጨ/ ዕግ/02/09/2012

በአብክመ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ለፖሊስና የሚሊሻ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አባላት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ደንብ ልብሶች (ዩኒፎርም) ግዥ በ2012 በጀት ዓመት በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም አገልግሎቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶችን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማየት ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር/ ለግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 25 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከመንግስት ንብረት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ሎቶች ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሠረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (Bid bond) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የገንዘብ መጠን ብር


8. ማንኛውም ተጫራች ህጋዊነት የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን እና ፋይናንሽያል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በመንግስት ንብረት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከግንቦት 10 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ. ም 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው ግንቦት 25 ቀን 2012 ዓ. ም 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾችን ወይም ህጋዊ ኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4 ፡30 ሰዓት በአብክመ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አዳራሽ ቁጥር 9 ይከፈታል፡፡

11. በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽንና ሚሊሻ ጽ/ቤት መጋዘን ማቅረብ አለባቸው፡፡

12. አገልግሎቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. በጨረው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቀጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 29 58 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 12 68/45 09/ 058 320 98 41 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 10 ቀን 2012
Deadline: June 2, 2020


© walia tender

Report Page